Category: Uncategorized
-

ቦይንግ የተሰኘው አውሮፕላን አምራች ኩባንያ የቀድሞ ሠራተኛ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል።
የቀድሞው ሠራተኛው የድርጅቱን ምስጢር በማጋለጥ ይታወቅ ነበር። ጆን ባርኔት ለቦይንግ ፋብሪካ ለ32 ዓመታት የሠራ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2017 ነበር ጡረታ የወጣው። ከመሞቱ በፊት ባሉት ቀናት ቦይንግ በተመሠረተበት ክስ ላይ ምስጢር አሾላኪ ሆኖ ቀርቦ ምስክርነቱን እየሰጠ ነበር። ቦይንግ በቀድሞው ሠራተኛው ሞት የተሰማውን ሀዘን ገልጧል። የቻርልስተን ክፍለ-ግዛት ባለሥልጣናት የግለሰቡን መሞት ሰኞ ዕለት ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ባለሥልጣናቱ ግለሰቡ የሞተው ቅዳሜ…
-

የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላት አከባባርን ለመወሰን የወጣው ረቂቅ አዋጅ ሃይማኖታዊ እና ብሔራዊ የሕዝብ በዓላት ላይ የሚታዩ ሰንደቅ ዓላማዎችን ዓይነት በግልጽ እንዲያስቀምጥ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ተጠየቀ።
ጥያቄው የተነሳው የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባባር ለመወሰን ወጣው ረቂቅ አዋጅ ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 3/2016 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበበት ወቅት ነው። ረቂቁ ለምክር ቤቱ የቀረበው ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ ለመምራት ነው። በተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትሩ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ አዋጁ እና ማብራሪያ በንባብ ካሰሙ በኋላ አዋጁ የሚመራለት ቋሚ ኮሚቴ ሊመለከታቸው ይገባሉ…
-

ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥለው ምርጫ አሸንፈው ፕሬዝደንት ከሆኑ ለዩክሬን ምንም ድጋፍ አይሰጡም ሲሉ የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክተር ኦርባን ተናገሩ።
ወግ አጥባቂው ጠቅላይ ሚኒስትር በአሜሪካዋ ፍሎሪዳ ግዛት ከትራምፕ ጋር ከተወያዩ በኋላ “ለዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት አምስት ሳንቲም እርዳታ አያደርጉም። ለዚህ ነው ጦርነቱ ያበቃል የምንለው” ብለዋል። የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ከተመረጡ ጦርነቱን “በ24 ሰዓታት” እንደሚቋጩት ቢናገሩም እንዴት የሚለውን አላስረዱም። የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር በሚቀጥለው ምርጫ ወዳጃቸው ትራምፕ እንዲያሸንፉ በግልፅ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። “ዩክሬን በእግሯ መቆም እንደማትችል ግልፅ ነው” ይላሉ እሑድ…
-

የአፍሪካ ኅብረት ተወካዮች ባሉበት የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊዎች በፕሪቶሪያው ስምምነት አፈጻጸም መዘግየት ዙሪያ ውይይት ጀመሩ።
ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት ያስቆመው የፕሪቶሪያው ስምምነት ከተፈረመ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጥሯል። ምንም እንኳ ከስምምነቱ መፈረም በኋላ የተኩስ አቁም ተደርጎ ጦርነቱ ቢቆምም የስምምነቱ አካል የሆኑ ሌሎች ጉዳዮች ተፈጻሚነት መዘግየቶች ገጥመውታል። በስምምነቱ የተካተቱ በተለይም ከአገር መከላከያ ሠራዊት ውጪ ያሉ ኃይሎች ከትግራይ መውጣት፣ የትግራይ ሕገ-መንግሥታዊ አስተዳደር ወደነበረበት መመለስ፣ በጦርነቱ ሳቢያ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ነበሩበት…
-

የአሜሪካ ግዙፍ የጦር መርከብ በጋዛ ጊዜያዊ ወደብ ለመገንባት ወደ መካከለኛው ምስራቅ ጉዞ መጀመሯን የአገሪቱ ጦር አስታወቀ።
ለወደብ ግንባት ግብዓቶችን የጫነችው ጀነራል ፍራንስ ኤስ ቤሰን የተባለችው መርከብ ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ከአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ተነስታለች። የመርከቧ ጉዞ የተሰማው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሜሪካ ለጋዛ ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ ተንሳፋፊ የሆነ ጊዜያዊ ወደብ እንደምትገነባ ካስታወቁ በኋላ ነው። የተባበሩት መንግሥታት በእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት ምክንያት በጋዛ ሕጻናት በረሃብ እየሞቱ ነው ማለቱ ይታወሳል። ትናንት እሁድ አሜሪካ እና ጆርዳን…
-

የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተካሄዱ ባሉት ግጭቶች ውስጥ ሠራዊታቸው ነዋሪዎች ላይ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ፈጽሞ እንደማያውቅ ተናገሩ።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ይህንን ያሉት ከብሔራዊው የቴሌቭዥን ጣቢያ ጋር ከሁለት ሰዓት በላይ በቆየ ቃለ ምልልስ ላይ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ እየተካሄዱ ስላሉት ወታደራዊ ግጭቶች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት በግጭቶች አካባቢ በሚወስዳቸው እርምጃዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን መንግሥታዊውን የሰብአዊ መብት ድርጅት ጨምሮ በርካታ ዘገባዎች የወጡ ቢሆንም፣ ኤታማዦር…
-

በናይጄሪያ ከቀናት በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች በታጣቂዎች ከታገቱ በኋላ ቅዳሜ ዕለት ተጨማሪ በርካታ ተማሪዎች ተጠልፈው መወሰዳቸው ተዘገበ።
በአገሪቱ በተባባሰው የእገታ ድርጊት ሶኮቶ በተባለው ግዛት ውስጥ ከሚገኝ ጋዳ ከተባለ ትምህርት ቤት ወደ 20 የሚጠጉ ተማሪዎች እና ሴቶች ታግተው ተወስደዋል። የአካባቢው ምክር ቤት አባል የሆኑት ኡስማን ጎራው ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከታገቱት ውስጥ 15ቱ ቅዳሜ ጠዋት በታጣቂዎቹ የተወሰዱ ናቸው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የናይጄሪያ ሠራዊት ሐመስ ዕለት ከምዕራባዊቷ ኩሪጋ ከተማ በተመሳሳይ ታግተው የተወሰዱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታዳጊዎችን ለማግኘት…
-

አሜሪካ በዚምባብዌ የነበሩ የእርዳታ ሠራተኞቿ መዋከብ፣ መታሰር እንዲሁም ከአገር እንዲባረሩ ተደርገዋል ስትል ከሰሰች።
የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) እንዳለው በዚምባብዌ ያሉ የአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣናት እና ጊዜያዊ ሠራተኞች “በቃል እና በአካል ማስፈራሪያ ደርሶባቸዋል” ብሏል። እነዚህ አካላት በዚምባብዌ የተገኙት “የዜጎችን ተሳትፎ፣ የዲሞክራሲ ተቋማትን እና የሰብዓዊ መብቶችን ለመደገፍ ነበር” ሲልም ዩኤስኤአይዲ ባወጣው መግለጫ አክሏል። ነገር ግን ዚምባብዌ ዲሞክራሲዋን ለማሻሻል የነበራት ቁርጠኝነት “ባዶ ነው” ሲልም ተችቷል። የዚምባብዌ መንግሥት ዩኤስኤአይዲ በሰነዘረበት…
-

የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ፔንታጎን ለበርካታ ዓመታት በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ውስጥ ምንነታቸው ያልታወቁ በራሪ አካላትን (ዩፎ) መታየታቸውን በተመለከተ የማጠቃለያ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ።
በተለይ በአውሮፓውያኑ የ1950ዎቹ እና 60ዎቹ ውስጥ በከፍተኛ ቁጥር የታዩት እና ዩፎዎች ናቸው ተብለው የተደመደሙት በራሪ ነገሮች የአሜሪካ መንግሥት የሠራቸው የተራቀቁ የስለላ አውሮፕላኖች እና የህዋ ቴክኖሎጂ ሙከራ ውጤቶች ናቸው ብሏል። የመከላከያ ባለሥልጣናት አክለውም የአሜሪካ መንግሥት ከሌላ ዓለም የመጡ እንግዳ ፍጡራን ማጋጠማቸውን በሚመለከት “ምንም ዓይነት” ማስረጃ የለም ብለዋል። አርብ ዕለት ለአሜሪካ ምክር ቤት የቀረበው ሪፖርት እንዳመለከተው ዩፎ…
-

በናይጄሪያ ሰሜን ምዕራብ ክፍል ውስጥ በምትገኘው ኩሪጋ ከተማ ከ280 በላይ ተማሪዎች በታጠቁ ኃይሎች ታግተው መወሰዳቸውን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።
አንድ የዐይን እማኝ እንደተናገሩት ተማሪዎቹ ከመታገታቸው በፊት ከመማሪያ ክፍል ውጪ አንድ ላይ ተሰባስበው ነበር። በቅጽበት ግን የታጠቁ ኃይሎች በሞተር ሳይክል ወደ ግቢው በመግባት ከበባ ፈጽመው ወስደዋቸዋል። ታጋቾቹ ዕድሜያቸው ከስምንት እስከ 15 ዓመት የሚደርስ ሲሆን፣ አሰስተማሪዎቻቸውም አብረው የእገታው ሰለባ መሆናቸው ተነግሯል። በናይጄሪያ የታጠቁ ወንበዴዎች በተለይ በአገሪቱ ሰሜን ምዕራብ አካባቢ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አግተዋል። እስከዚህ ሳምንት ድረስ…