በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ውጥረት ወደ ከፍተኛ ደረጃ በወሰደ ጥቃት ኢራን በእስራኤል ላይ የሰው አልባ አውሮፕላን እና የሚሳኤል ጥቃቶችን ፈጸመች።

ኢራን ጠላቷ አድርጋ በምትቆጥራት እስራኤል ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ስትፈጽም ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ኢራን በጋዛ እስራኤልን እየተዋጋ ያለውን ሐማስን እንዲሁም በቀጠናው የእስራኤል ጠላት የሆኑትን ሄዝቦላህ እና የየመን ሁቲ አማጺያንን በመደገፍ እስራኤል ላይ በእጅ አዙር ጥቃት ስትፈጽም ቆይታለች።

ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት የመክፈቷ ዜና ኢራናውያን ወደ አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን አንዲገልጹ አድርጓቸዋል።

ይህ የኢራን ጥቃት ድንገት የተከሰተ አይደለም። ኢራን ከ11 ቀናት በፊት በሶሪያ ዋና ከተማዋ በሚገኘው ቆንስላ ጽህፈት ቤቷ ላይ በተፈጸመው ጥቃት እስራኤልን ተጠያቂ አድርጋ የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ ስትዝት ቆይታለች።

ቴህራን በቴል አቪቭ ላይ ጥቃት የምትከፍት ከሆነ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ይባባሳል በሚል አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ጀርመን ለኢራን ማሳሰቢያዎችን ሲሰጡ ቆይተዋል።

ኢራን እራሳቸውን እያጋዩ ዒላማቸውን የሚመቱ ድሮኖችን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሚሳኤሎችን እስራኤል ላይ መተኮሷ ተዘግቧል።

እስራኤል ሚሳኤሎቹን እና ድሮኖቹን የአየር ክልሏ ውስጥ ሳይገቡ መትታ መጣሏን ገልጻለች።

In an attack that escalated tensions in the Middle East, Iran carried out drone and missile attacks on Israel.

This is the first time Iran has directly attacked Israel, which it considers its enemy. Iran has been supporting Hamas, which is fighting Israel in Gaza, as well as Israel’s enemies in the region, Hezbollah and Yemen’s Houthi rebels, and has been carrying out hand-to-hand attacks against Israel.

The news that Iran launched an attack on Israel caused Iranians to go out and express their joy.

This Iranian attack did not happen suddenly. Iran has blamed Israel for the attack on its consulate in the Syrian capital 11 days ago and has threatened to retaliate.

The United States, the United Kingdom and Germany have been warning Iran that if Tehran launches an attack on Tel Aviv, tensions in the Middle East will escalate.

Iran has reportedly fired homing drones and hundreds of missiles at Israel.

Israel said it shot down the missiles and drones without entering its airspace.

Design a site like this with WordPress.com
Get started