የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የማስታወስ ችሎታቸው ‘በጉልህ’ ቀንሷል መባሉን ተከትሎ በብስጭት “የማስታወስ ችሎታዬ ምንም አልሆነም” ሲሉ መለሱ።

ባይደን ከዓመታት በፊት ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሉ ከወታደራዊ እና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ጋር የተያያዙ ምስጢራዊ ሠነዶች አያያዛቸውን በተመለከተ የወጣ የምርመራ ሪፖርት ላይ የ81 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ቁልፍ የሚባሉ ቀናትን ዘንግተዋል ብሏል።

የፍትሕ ቢሮ አማካሪ የሆኑት ሮበርት ሁር ፕሬዝዳንቱን ለአምስት ሰዓታት የዘለቀ ጥያቄዎችን ከጠየቋቸው በኋላ ባይደን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለገሉባቸውን ዓመታት፤ እንዲሁም ልጃቸው ሕይወቱ ያለፈበትን ዓመት ማስታወስ ተስኗቸዋል ብለዋል።

መርማሪው ይህን ካሉ በኋላ ባይደን ብስጩ ሆነው ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፤ “የማስታወስ ችሎታዬ ደህና ነው” ካሉ በኋላ ልጃቸው ሕይወቱ ያለፈበትን ቀን አያስታውሱም መባላቸው “በምን ድፍረቱ ነው ስለዚህ ጉዳይ የሚያወራው” ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ በመርማሪው የግል ሕይወታቸውን የተመለከቱ ጥያቄዎችን ሲጠየቁ፤ “ምን አግብቶት ነው ይህን የሚጠይቀኝ እያልኩ እራሴን ስጠይቅ ነበር” ካሉ በኋላ “ልጄ ሕይወቱ ያለፈበትን ጊዜ ማንም እንዲያስታውሰኝ አልፈልግም” ብለዋል

US President Joe Biden angrily replied, “My memory is fine” after being told that his memory has ‘significantly’ declined.

In an investigative report on Biden’s handling of classified documents related to the military and foreign policy while he was vice president years ago, the 81-year-old president said he forgot key dates.

After Justice Department counsel Robert Hurr questioned the president for five hours, Biden’s years as vice president; They also said that they could not remember the year of their son’s death.

After the detective said this, Biden was upset and told reporters; After saying, “My memory is fine,” they said that they do not remember the date of his son’s death.

When the President is asked questions about his personal life by the investigator; “I was asking myself, ‘Why did you marry him?’

Design a site like this with WordPress.com
Get started