የአየርላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሲሞን ሃሪስ የአገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችል ሕግ አርቅቆ ለአገሪቱ ካቢኔ እንዲያቀርብ አዘዋል።
ዩናይትድ ኪንግደም በሕገ-ወጥ መልኩ ወደ አገሯ የሚገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እልካለሁ ማለቷን ተከትሎ ዩኬ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሩዋንዳ ላለመመለስ ሲሉ እንደ አየርላንድ ያሉ አገራትን አማራጭ መዳረሻቸው እያደረጉ ነው።
የአየርላንድ የፍትሕ ሚኒስትር ሄለን ማክኤንቲ በቅርቡ ወደ አየርላንድ ከተሻገሩ ስደተኞች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት መነሻቸው ዩኬ ነው ብለዋል።
የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማይክል ማርቲን የዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ እቅድ ገና ከአሁኑ በአየርላንድ ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ነው ብለዋል።
ከቀጥቂት ቀናት በፊት ለበርካታ ወራት ብዙ ሲያወዛግብ የቆየው ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በሕገ-ወጥ መንገድ የገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የሚያስችለውን ሕግ የአገሪቱ ፓርላማ ጸድቆ ሕግ ሆኗል።
ይህ ሕግ ኢንግሊሽ ቻናል ተብሎ በሚጠራው የውሃ አካል በኩል በጀልባ በሕገ-ወጥ መንገድ ዩኬ የደረሱ ስደተኞችን በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ሩዋንዳ የሚልክ ነው።
The Irish government has begun to develop a legal framework to allow migrants from the United Kingdom to return to the UK.
Irish Prime Minister Simon Harris has ordered the country’s Ministry of Justice to draw up a law to allow refugees to return to the UK and submit it to the country’s cabinet.
After the United Kingdom said it would send illegal immigrants to Rwanda, refugees in the UK are turning to countries like Ireland as their alternative destination to avoid returning to Rwanda.
Ireland’s Justice Minister Helen McEntee has said that 80 per cent of migrants who have recently crossed into Ireland are from the UK.
Deputy Prime Minister Michael Martin says plans to send UK refugees to Rwanda are already having an impact on Ireland.
A few days ago, the country’s parliament approved the law that allows for the deportation of illegal immigrants to the United Kingdom (UK), which has been debated for several months.
This law would force migrants who arrived illegally in the UK by boat across the English Channel to Rwanda.


Leave a comment