Category: Uncategorized
-

የወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ አቶ ታዬ ደንደአ “ጠበቆቼ ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው” ሲሉ ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ።
አቶ ታዬ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም. ችሎት ሲቀርቡ ከአምስቱ ጠበቆቻቸው አንዳቸውም ሳይገኙ ቀርተዋል። የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል ፀረ ሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት በሚሉ ወንጀሎች ተከሰው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥት እና የሽብር ወንጀል ችሎት ጉዳያቸው እየታየ እንደሚገኝ ይታወቃል። ችሎቱ ሐሙስ…
-

እስራኤል በጋዛ በአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ማዕከል አቅራቢያ በፈጸመችው ጥቃት 22 ፍልስጤማውያን ተገደሉ።
የቀይ መስቀል ቢሮዎችም በጥቃቱ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተቋሙ ያስታወቀ ሲሆን በግቢው ዙሪያ ተጠልለው የነበሩ 22 ሰዎችም ተገድለዋል። አርብ ከሰዓት በኋላ የተፈጸመው ጥቃት ከአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ቢሮ እንዲሁም መኖሪያ ቤቶች በሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኝ ነው። ቀይ መስቀል ጥቃቱን አውግዞ በሰላማዊ ሰዎች እና በረድዔት ተቋማት ማዕከላት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ሁሉም አካላት ጥንቃቄዎችን የማድረግ ግዴታ አለባቸው ብሏል።…
-

ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢንዶኔዢያ አየር መንገድ በሆኑ ቦይንግ ማክስ 737 አውሮፕላኖች አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ቦይንግ የ24.8 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት እንዲጣልበት ጠየቁ።
የአደጋው ሰለባዎች ቤተሰቦች ጠበቃ ቦይንግ በአሜሪካ ኩባንያዎች ታሪክ ከፍተኛውን ወንጀል የፈጸመ ነው ሲል ገልጾታል። የቤተሰቦቹ ጠበቃ ፖል ካሴል ቦይንግ ውድ በሆነው የሰው ልጆች ሕይወት ላይ ጥፋት በማድረስ ለፈጸመው ወንጀል የተጠየቀው የገንዘቡ መጠን “ተገቢ እና ትክክል ነው” ብለዋል። ቢቢሲ በተመለከተው ባለ 32 ገጽ ደብዳቤ ላይ ጠበቃው የአሜሪካ መንግሥት በ2010 እና 2011 ዓ.ም. በደረሱት እና የ346 ሰዎችን…
-

የኬንያ መንግሥት በተለያዩ ምርቶች ላይ ሊጥል የነበረው ቀረጥ ከሕዝብ በገጠመው ከፍተኛ ተቃውሞ ምክንያት በመንግሥት እንዲቀር ተደረገ።
መንግሥት ተግባራዊ ሊያደርገው የነበረው የፋይናንስ ሕግ እንደ ዳቦ ባሉ ምርቶች ላይ እስከ 16 በመቶ ጭማሪን የሚያደርግ ነበር። ረቂቅ ሕጉ ለአገሪቱ የተወካዮች ምክር ቤት ከተላከ በኋላ ኬንያውያን ወደ ምክር ቤቱ በማቅናት ጠንካራ የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል። ማክሰኞ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም. ፖሊስ ከፓርላማው ደጃፍ የተሰበሰቡ ተቃዋሚዎችን በአስለቃሽ ጭስ ሲበትን የምክር ቤት አባላት በረቂቅ አዋጁ ላይ ውይይት ሲያደርጉ ነበር።…
-

የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት “ሥልጣን ሳይኖረው” የቅጣት የክፍያ ተመን መመሪያ በማውጣት፤ በግለሰቦች ስም በተከፈተ የባንክ ሂሳብ 17.9 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት አስታወቀ።
ተቋሙ ከነሐሴ 2015 ዓ.ም እስከ ጥር 2016 ዓ.ም. ከሰበሰበው 17.9 ሚሊዮን ብር ውስጥ 9.3 ሚሊዮን ብር “ለትርፍ ሰዓት ክፍያ እና ለበዓል ለሠራተኞች ስጦታ” ወጪ መደረጉን ኦዲተር መሥሪያ ቤቱ ይፋ አድርጓል። የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ይህን ይፋ ያደረገው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው የ2015 ዓ.ም. በጀት ዓመት የፋይናንስ እና ሕጋዊነት ኦዲተር እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ…
-

በገዢው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ወሳኝ የተባለውን የአንድነት መንግሥት ለመመሥረት ስምምነት ከተደረሰ በኋላ የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ በድጋሚ ሲሪል ራማ ፎሳን ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ።
አዲሱ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት የአንድነት መንግሥት ከዚህ ቀደም ከነበረው በተለየ ሁኔታ የራማፎሳን ኤኤንሲ፣ መሃል-ቀኝ ዘመሙን ዲሞክራቲክ አሊያንስን እና ሌሎች ትንንሽ ፓርቲዎችን ያቀፈ ነው። ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ከተመረጡ በኋላ ባደረጉት ንግግር ፓርቲዎች በጋራ መንግሥት መመሥረታቸውን አድንቀው፣ መራጮች ከመሪዎቻቸው “ለአገሪቱ ዜጎች በሙሉ መልካም ነገር በጋራ እንዲሠሩ እንደሚጠብቁ” ተናግረዋል። ከሳምንት በፊት በተካሄደው ምርጫ ኤኤንሲ በአገሪቱ ፓርላማ ለ30 ዓመታት የነበረውን…
-

የቡድን 7 አባል አገራት በዕግድ ላይ ያሉ የሩሲያ ንብረቶችን በመጠቀም ለዩክሬን የ50 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማቅረብ ተስማሙ።
ዩክሬን የሚቀርብላትን ብድር ከሩሲያ ጋር ለምታደርገው ጦርነት ትጠቀምበታለች። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህ ለሩሲያ “መቼም እንደማንመለስ” ሌላ ማስታወሻ ነው ሲሉ፤ ሞስኮ በበኩሏ “እጅግ መራር” አጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች። ዩክሬን ይህንን ገንዘብ ለመቀበል 6 ወራት ያህል መጠበቅ የግድ የሚላት ቢሆንም፣ በጦርነት የደቀቀ ኢኮኖሚያዋ እንዲያንሰራራ መፍትሔ ይሆናል ተብሎ ታምኖበታል። ከዚህ በተጨማሪ በጣልያን በተካሄደው የቡድን 7 ጉባዔ ላይ…
-

ባለቤትነቷ የግሪክ የሆነች መርከብ የቀይ ባሕርን ስታቋርጥ በየመን ሁቲ አማጽያን በሰው አልባ የጦር ጀልባ በተፈጸመባት ጥቃት በውሃ ክፉኛ እንደተጥለቀለቀች እና የሞተር ክፍሏ እንደተጎዳ አሜሪካ ገልጻለች።
የዩናየትድ ኪንግደም ንጉሣዊ ባሕር ኃይል የማሪታየም ንግድ ጽህፈት ቤት የሁቲ አማጽያን ከተቆጣጠሩት የሆዴይዳ ወደብ ደቡባዊ ምዕራብ አቅጣጫ አንዲት መርከብ ከበስተጀርባዋ ጥቃት እንደደረሰባት ጥቆማ ደርሶኛል ብሏል። መርከቧ ውስጥ ውሃ ዘልቆ እንደገባ እና ክስተቱም ከቁጥጥር ውጪ እንደሆነ ጽህፈት ቤቱ ጨምሮ ገልጿል። በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማጺያን ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስደዋል። የላይበሪያ ሰንደቅ ዓላማን ስታውለበልብ የነበረችው ቱቶር የተሰኘችውን መርከብ የባሕር…
-

የኩዌት ከተማ በሆነችው ማንጋፍ ውስጥ በሚገኝ አንድ የመኖሪያ ሕንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ቢያንስ 41 ሰዎች መሞታቸውን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋሩ ቪዲዮዎች የሕንጻው የታችኛ ክፍሎች በእሳት ነበልባል ሲቃጠሉ፣ ከላይኛው ክፍሎች ደግሞ ጥቁር ጭስ ሲወጣ አሳይተዋል። ባለሥልጣናት እንዳሉት ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች 15 ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። በእሳት ቃጠሎው ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በሕንጻው ውስጥ የሚኖሩ ከውጭ አገራት የመጡ ሠራተኞች ናቸው። የኩዌት የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እሳቱ በቁጥጥር ስር…
-

አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ከየመን የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ ተገልብጣ ቢያንስ 38 ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ።
ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ለነፍስ አድን ሠራተኞች እንደተናገሩት ጀልባዋ 250 የሚጠጉ ሰዎችን አሳፍራ የነበረ ሲሆን፣ ለመገልበጥ የበቃችውም በካባድ ነፋስ ምክንያት ነው ተብሏል። መሞታቸው ከታወቀው 38 ሰዎች ውጪ ሌሎች 100 ሰዎች የደረሱበት ያልታወቀ ሲሆን፣ እነሱን ለማግኘት ፍለጋ እየተደረገ ነው። ከየመን ዋና ከተማ አደን በስተምሥራቅ የምትገኘው የሩደም አካባቢ ባለሥልጣናት እንዳሉት አደጋው በደረሰባት ጀልባ ላይ ተሳፈረው ከነበሩት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን…