Category: Uncategorized
-

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ውሳኔ አስተላለፈ። በውሳኔው ላይ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷን ያልተጠቀመችው አሜሪካ በቀደመ አቋሟ አለመቀጠሏ ታይቷል።
ውሳኔው ታጋቾች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እና በፍጥነት እንዲለቀቁም ጠይቋል። መስከረም ማብቂያ ላይ ከተጀመረው ጦርነት በኋላ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሲወሰን ይህ የመጀመሪያው ነው። አሜሪካ ያሳየችው አቋም ከእስራኤል ጋር ያላትን ልዩነት እየሰፋ መምጣቱን ያሳየ ነው ተብሏል። የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት አሜሪካ ቀደም ሲል የተኩስ አቁሙን ከታጋቾች መለቀቅ ጋር ያስቀመጠችበትን አቋም “የቀየረ” ብሎታል። “በሚያሳዝን ሁኔታ አሜሪካ…
-

አሜሪካ በአማራ ክልል ተጎራባች ዞኖች ውስጥ በሚፈጸሙ ጥቃቶች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት እንደሚያሳስባት ገለጸች።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር አወርቪን ማሲንጋ በአማራ ክልል ውስጥ ባለፉት ሳምንታት የተፈጸሙትን ጥቃቶች በተመለከተ የአገራቸውን ስጋት በኤምባሲያቸው የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ይፋ አድርገዋል። በዚህም “በአማራ ክልል የኦሮሞ ልዩ ዞን እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች ውስጥ የሚፈጸሙ. . . ጥቃቶችን በተመለከተ የሚወጡ ዘገባዎች ዩናይትድ ስቴትስን ያሳስቧታል” ብለዋል አምባሳደሩ። ከአንድ ሳምንት በፊት በአማራ ክልል ውስጥ በሚገኙት በተጎራባቾቹ የኦሮሞ ብሔረሰብ…
-

በደቡብ አፍሪካዋ ጆሃንስበርግ ከተማ ነዋሪ የሆነው ምሎትሽዋ ፔንሰን ላለፉት ስድስት ዓመታት የትም ቦታ ሲሄድ ሽጉጡ ተለይቶች አያወቅም። ወደ ሱቆች፣ ምግብ ቤቶች እና ጂም ሲሄድ ሁሉ ታጥቆ ነው።
በየዕለቱ ከፍተኛ ወንጀል በሚፈጸምባት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሚታጠቀው ሽጉጥ የዩቲዩብ ቪዲዮዎችን ለሚያዘጋጀው ለፔንሰን ወሳኝ የሆነ ነገር ነው። “ጠንቋይ ስላልሆንኩ መቼ ጥቃት እንደሚፈጸምብኝ አላውቅም” በማለት እራሱን ለመከላከል ሽጉጡን ዘወትር ታጥቆ እንደሚንቀሳቀስ ፔንሰን ለቢቢሲ ተናግሯል። “እራሴን ለመከላከል ሽጉጤን ለመጠቀም የተገደድኩባቸው ጊዜያት በርካታ ናቸው” በማለትም አንድ ምሽት ከእራት ሲመለስ በስለት አስፈራርቶ የኪስ ቦርሳውን ለመውሰድ ስለተደረገበት ሙከራ ያስታውሳል። በዚህ…
-

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ የአማራ ክልል በመማሪያ መጽሐፍት ላይ ያውጣ ካርታ ላይ በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ አስጠነቀቀ።
ካቢኔው እንዳለው የአማራ ክልል የተቆጣጠራቸውን አካባቢዎች የሚያካትተው ካርታን የማያርም ከሆነ ለሚፈጠረው ችግር ኃላፊነቱን ይወስዳል ሲል አስጠንቅቋል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ መግለጫውን ያወጣው ሁለቱ ክልሎች ይገባናል የሚሏቸው እና በአማራ ክልል ቁጥጥር ስር የሚገኙ አወዛጋቢ ቦታዎችን ያካተተ ካርታ የአማራ ክልል በማውጣቱ ነው። እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት በአማራ ክልል ውስጥ እየተሰራጩ ባሉ የመማሪያ መጽሐፍት ላይ ሁለቱ ክልሎች የሚወዛገቡባቸው አካባቢዎች…
-

እንግሊዛዊቷ ጃስሚን ፓሪስ ከዓለማችን ከባድ የሩጫ ውድድሮች ቀዳሚው ነው የሚባለውን በመጨረስ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነች።
ይህ 160 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍነውን እና 18 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ተራራን መውጣት እና መውረድ የሚጠይቀውን ውድድር ከ60 ሰዓት ባነሰ ግዜ ውስጥ መጨረስ ችላለች። ጃስሚን በርክሌይ ማራቶንስ የተባለውን ውድድር በ60 ሰዓታት ውስጥ የመጨረስ ግዴት የነበረባት ሲሆን ይህን ከባድ ሩጫ ለመጨረስ ከተሰጣት 60 ሰዓታት፤ 1 ደቂቃ ከ 39 ሴኮንዶች ብቻ ሲቀራት ውድድሩን ጨርሳለች። በውድድሩ መጨረሻ ላይ…
-

የዩክሬን መዲና ኪዬቭ በድንገተኛ የሩሲያ የአየር ጥቃቶች ድብደባ ደረሰባት።
ድንገተኛውን የሩሲያ ድብደባ ተከትሎ በመላ ዩክሬን የአገሪቱ ጦር በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል። የሩሲያ የአየር ድብደባ ከፖላንድ የምትዋሰነው ሊቪቭ ግዛትን መምታቱን ተከትሎ ፖላንድ የአየር ኃይሏ በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን አዛለች። በመዲናዋ ኪዬቭ ላይ የአየር ድብደባው የጀመረው በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር እሑድ ንጋት 11 ሰዓት አካባቢ ነው። የዩክሬን ጦር አየር ኃይሉ የሩሲያን ጥቃት በመከላከል ተጠምዷል ብሏል። የጦሩ ዋና አስተዳዳሪ ሴርሂይ…
-

የአሜሪካ ምክር ቤት (ሴኔት) መንግሥት እስከ መጪው መስከረም ድረስ ወጪውን የሚሸፍንበትን የ1.2 ትሪሊዮን ዶላር ገንዘብ ለመመደብ ከስምምነት ላይ በመድረሱ መንግሥታዊ እቅስቃሴዎችን ከመዝጋት ታደገ።
ባለፉት ቀናት ዋነኛ መነጋገሪያ የነበረው የበጀት ጉዳይ ለአገሪቱ እንደራሴዎች ቀርቦ ከአርብ እኩለ ሌሊት በፊት ተቀባይነት ባያገኝ ኖሮ በመላው አገሪቱ ያሉ የፌደራል እና የግዛት መንግሥታዊ አገልግሎቶች በከፊል ሥራ ለማቆም ይገደዱ ነበር። የቀረበው የበጀት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ ወሳኝ ከሆኑት መንግሥታዊ ሥራዎች ውጪ ላሉ እንቅስቃሴዎች የሚያስፈልገው ገንዘብ ስለሚገኝ የመንግሥት ተቋማት ሥራቸውን ሳያቋርጡ ይቀጥላሉ። ሕግ አውጪዎቹ በአስፈላጊው ገንዘብ ላይ…
-

አሜሪካ የታጋቾችን መለቀቅ ከጋዛ ተኩስ አቁም ጋር በማያያዝ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ያቀረበችውን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ሩሲያ እና ቻይና ውድቅ አደረጉት።
ሩሲያ እና ቻይና ይህንን የአሜሪካ የውሳኔ ሃሳብ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸውንም በመጠቀም ነው ተቀባይነት እንደሌለው ያሳወቁት። ቀደም ሲል ሌሎች አገራት በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስ የተለያዩ የውሳኔ ሃሳቦች ለፀጥታው ምክር ቤት ቢቀርቡም ሊሳኩ አልቻሉም። አሜሪካ ከዚህ ቀደም ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የጋዛ ተኩስ አቁም ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷን ጭምር…
-

ዕውቁ የብራዚል ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን የቀድሞ ተጫዋች ሮቢንሆ በመድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ የዓመታት አስር ተፈረደበት።
ከብራዚል ኮከብ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረው ሮቢንሆ በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በጣልያን ፍርድ ቤት የዘጠኝ ዓመት እስር ተፈርዶበታል። ሮቢኒሆ እንደ አውሮፓውያኑ በ2013 በጣልያን ሚላን ከተማ በሚገኝ የምሽት የመዝናኛ ክበብ ውስጥ የአልቤኒያ ዜግነት ያላት ሴት በቡድን ስትደፈር ተሳታፊ ነበር ተብሏል። አሁን የ40 ዓመት ጎልማሳ የሆነው ሮቢንሆ በብራዚል ሳንቶስ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ውስጥ የቁም እስረኛ ሆኖ…
-

የፌደራል ዐቃቤ ሕግ፣ ኤሪክ ታባሮ ሺሚዬ የተባለውን ግለሰብ ሰዎች እንዲገደሉ ማድረግን ጨምሮ በጅምላ ግድያ የነበረውን ተሳትፎ በመደበቅ ከሶታል። ሺሚዬ በአሜሪካ በሐሰት ስደተኛ ሆኖ እንዲቆይ ፈቃድ በማግኘቱ ከአውሮፓውያኑ 1995 ጀምሮ በኦሃዮ ኑሮውን ማድረጉን ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል። ግለሰቡ ቀደም ብሎም በዘር ማጥፋት መሳተፉን አስተባብሏል። ቦስተን በሚገኘው የፌደራል ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። የአገር ውስጥ የወንጀል ምርመራ ልዩ…