Category: Uncategorized
-

የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ቦላ ቱኒቡ ሚኒስትሮች እና ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት በአገሪቱ ገንዘብ የውጭ አገራት ጉዞዎችን እንዳያደርጉ የሶስት ወራት እገዳ ጣሉ።
ይህ እርምጃ ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ ላይ የተደረሰውም የመንግሥት ባለስልጣናቱ በውጭ የሚያደርጓቸው ጉዞዎች ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ስጋት መሆኑን ተከትሎ እንደሆነ የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ገልጸዋል። እግዱም ከአስር ቀናት በኋላ ተግባራዊ ይሆናል። ፕሬዚዳንት ቱኒቡ እና ባለስልጣኖቻቸው በተደጋጋሚ ወደ ውጭ አገራት በሚያደርጓቸው ተደጋጋሚ ጉዞዎች ትችቶች ሲቀርብባቸው ይሰማል። ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ዓመት ግንቦት ስልጣን ላይ ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ ከ15…
-

የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር በገዛ ፈቃዳቸው ከሥልጣን ሊለቁ መሆኑን አስታወቁ።
ከፓርቲ ሊቀ መንበርነታቸው ወዲያውኑ የሚነሱ ሲሆን ተተኪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከተመረጠ በኋላ ደግሞ ሥልጣናቸውን ይለቃሉ ተብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥልጣን መልቀቃቸውን ባስታወቁበት ወቅትም “አገራቸውን የመሩበት ዓመታት በሕይወታቸው የተሳካ ተግባር ያከናወኑበት” እንደሆነም ገልጸዋል። ከሥልጣን የለቀቁትም በ”ግላዊ እና ፖለቲካዊ” ምክንያቶች እንደሆነም ተናግረው “ለዚህ ኃላፊነት የተሻለው ሰው አይደለሁም” በማለት ተናግረዋል። በአውሮፓውያኑ 2017፣ በ38 ዓመታቸው የፓርቲያቸው ፋይን ጋኤል ሊቀ መንበር መሆን…
-

የኔዘርላንድስ ተመራማሪዎች በኤችአይቪ ከተበከለ ህዋስ ቫይረሱን ነጥለው ማስወገድ መቻላቸውን አስታወቁ።
ሳይንቲስቶቹ እንደሚሉት ቫይረሱን ቆርጠው ማውጣት የቻሉት የኖቤል ሽልማት ያገኘው ክሪስፕር የተሰኘውን ‘ጂን-ኤዲቲንግ’ መንገድ በመጠቀም ነው። ልክ እንደ መቀስ ከዘረ-መል ላይ “የማይፈለገውን” በመቁረጥ ማስገድ ወይም ‘ንቁ’ እንዳይሆን ማድረግ መቻላቸውን ተመራማሪዎች ገልጠዋል። ቀጣዩ እርምጃ ቫይረሱን ከሰው ልጅ ሰውነት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ቢሆንም ይህንን በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን ገና ብዙ ሥራ እንደሚጠብቃቸው ሳይንቲስቶቹ ይናገራሉ። አሁን ገበያ ላይ ያሉ…
-

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲስተም ችግር በገጠመው ወቅት ገንዘብ የወሰዱ ግለሰቦች እስከዚህ ሳምንት መጨረሻ ድረስ የማይመልሱ ከሆነ በሕግ ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው አስታወቀ።
የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ለቢቢሲ ኒውስ ዴይ ሲናገሩ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ደንበኞች እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ድረስ ካልመለሱ ማንነታቸውን ለፖሊስ እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል። “በዲጂታል ነው ዝውውር የፈጸሙት። ደንበኞቻችን ስለሆኑ እናውቃቸዋለን። የፈጸሙት ተግባር በሕግ ያስጠይቃቸዋል። ለፖሊስ ማንነታቸውን እናሳውቃለን” ብለዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከገንዘብ ዝውውር ሥርዓቱ ማሻሻያ ሂደት ጋር በተያያዘ አርብ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም. ምሽት ችግር ባጋጠመው ወቅት…
-

በቻይና ውስጥ የሚጋቡ ጥንዶች ቁጥር ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጭማሬ አሳየ።
ባለፈው ዓመት በአገሪቱ ውስጥ 7.68 ሚሊዮን አዳዲስ ተጋቢ ጥንዶች የነበሩ ሲሆን ይህም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ12.4 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑን መረጃዎች አሳይተዋል። የአገሪቱ የሲቪል ጉዳይ ሚኒስቴር ከአውሮፓውያኑ 2022 በበለጠ 845 ሺህ አዳዲስ ተጋቢዎች መመዝገባቸውንም አመላክቷል። በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የተጋቢዎች ቁጥር የታየው በአውሮፓውያኑ 2013 ፣ 13.47 ሚሊዮን ተጋቢዎች በተመዘገቡበት ወቅት ነው። የአገሪቱ መንግሥት በቻይና ውስጥ…
-

የሐማስ ከፍተኛ የጦር መሪ ማርዋን ኢሳ በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደሉን የዋይት ሃውስ ባለሥልጣን ጃክ ሱሊቫን ተናገሩ።
ምክትል የጦር አዛዡ ኢሳ በእስራኤልና በሐማስ መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ የተገደለ ከፍተኛው የጦር መሪ ነው። ጋዛን የተቆጣጠረው የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን የጦር መሪው ሞቷል ስለመባሉ በይፋ የሰጠው አስተያየት የለም። የእስራኤል የመገናኛ ብዙኃን ምንጮች ኢሳ ከአንድ ሳምንት በፊት እስራኤል በማዕከላዊ ጋዛ በሚገኘው ኑሴራት የስደተኞች ካምፕ የሚገኝ ዋሻን ኢላማ አድርጋ በፈፀመችው የአየር ጥቃት መገደሉን ዘግበዋል። የሐማስ የጦር ክንፍ…
-

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በሁለት ወራት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር ለሥራ ጉብኝት ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አሥመራ መግባታቸው ተገለጸ።
የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በኤክስ ገጻቸው ላይ እንደገለጹት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ዛሬ እሁድ መጋቢት 8/2016 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ አሥመራ ገብተዋል። የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ጉብኝት በኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተደረገላቸው ግብዣ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፣ አቀባበል ያደረጉላቸውም ራሳቸው ፕሬዝዳንቱ ናቸው። በግንቦት ወር 2014 ዓ.ም. ወደ ሶማሊያ የፕሬዝዳንትነት መንበር የተመለሱት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ባለፉት ሁለት…
-

ካለፈው ዓመት አጋማሽ ወዲህ በአማራ ክልል የተከሰተው አለመረጋጋት ተባብሶ ወደ ለየለት የትጥቅ ግጭት ካመራ ወራት ተቆጥረዋል። በበርካታ የክልሉ አካባቢዎች የሚካሄደው ግጭት በሕዝቡ የዕለት ከዕለት ሕይወት ላይ ከባድ ጫናን እያሳረፈ ነው።
በዚህም ሳቢያ የሕዝቡ መደበኛ እንቅስቃሴዎች የተስተጓጎሉ ሲሆን፣ የመንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች፣ የትራንስፖርት፣ የንግድ፣ የትምህርት እና የጤና አገልግሎቶች በጉልህ በሚታይ ሁኔታ መደናቀፍ እንደገጠማቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ። የሕይወት እና የሞት ጉዳይ የሆነው የጤና አገልግሎት የማግኘት ጉዳይ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎችን የሚያሳስብ ጉዳይ ሆኗል። ከእነዚህም መካከል መደበኛ ክትትል እና ህክምና የሚያስፈልጋቸው እናቶች እና ህጻናት እንዲሁም የተለያዩ ዘላቂ የጤና ችግር…
-

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወንበዴ ቡድኖች እየታመሰች ካለችው ሄይቲ ዜጎችን በልዩ በረራ እንደሚያስወጣ አስታወቀ።
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ መውጫ አጥተው በሄይቲ ለሚገኙ አሜሪካውያን ከመዲናዋ 200 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቃ ከምትገኘው ካፕ-ሄይሺየን ከተማ በረራ እንደሚደረግ ለዜጎቹ መልዕክት አስተላልፏል። ሚኒስቴሩ በመልዕክቱ በረራው የሚደረገው በካፕ-ሄይሺየን ያለው የጸጥታ ሁኔታ የተረጋጋ ከሆነ ብቻ መሆኑን እና አውሮፕላኑን መሳፈር የሚችሉት የአሜሪካ ዜጎች ብቻ መሆናቸውን አስታውቋል። አሜሪካ ቀደም ሲል መሠረታዊ ግልጋሎት ላይ ያልተሰማሩ የኤምባሲ ሠራተኞችን አስወጥታለች። የደቀቀ…
-

በሱዳን ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የጽንፈኛ እስላማዊ እንቅስቃሴ ወደ አካባቢው የሚመለስበትን ሁኔታን ሊያባብስ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው አዲሱ በሱዳን የአሜሪካ መልዕክተኛ ቶም ፔሪዬሎ ለቢቢሲ ተናገሩ።
መልዕክተኛው ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደተለያዩ የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት በመጓዝ በሱዳን እየተካሄደ ያለው ጦርነት የሚያበቃበትን እና አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ የሚቀርብበትን መንገድ ለመፈለግ በጉብኝት ላይ ናቸው። ከተጀመረ አንድ ዓመት ሊሞላው የተቃረበው የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት በዓለም ላይ ትልቁ የሚባል የመፈናቀል ቀውስ እና ረሃብን መጋረጡን የእርዳታ ሠራተኞች እያስጠነቀቁ ነው። በሱዳን ሠራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል የሚካሄደው…