Category: Uncategorized
-

በኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጥቃት እንደተፈጸመባቸው የተዘገበው የአፍሪካ ልማት ባንክ የምሥራቅ አፍሪካ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱል ካማራ፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተገናኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ዛሬ የካቲት 29/2016 ዓ.ም. ጠዋት ከአፍሪካ ልማት ባንክ ኃላፊው ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን ያስታወቁት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ከፎቶዎች ጋር አያይዘው በለጠፉት መልዕክት ነው። በመልዕክታቸው፤ “ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ያላት አጋርነት ውጤታማ ሆኖ ቀጥሏል” ያሉት ዐቢይ፤ ከዶ/ር አብዱል ጋር የነበራቸው ውይይት ባንኩ “በኢትዮጵያ በሚያካሂዳቸው ፕሮጀክቶች” ላይ ያተኮረ እንደሆነ ገልጸዋል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ…
-

ከእስራኤል ተወካዮች ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ የቀጥታ ድርድር ለማድረግ ግብፅ ካይሮ የነበሩት የሐማስ ልዑካን ውጤት ሳያገኙ ወደ መጡበት መመለሳቸው ተዘገበ።
በሁለቱ ወገኖች መካከል ላለፉት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የቀጥታ ንግግር ከስምምነት ላይ ሳይደረስበት ቢቋረጥም፣ በተዘዋዋሪ የሚደረገው ድርድር ግን እንዳላበቃ ሐማስ አስታውቋል። በሚቀጥለው ሳምንት ከሚጀመረው የረመዳን ጾም ጋር ተያይዞ ለ40 ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም ይደረጋል ተብሎ ቢጠበቅም ሳይሳካ ቀርቷል። ጋዛ ውስጥ በተከሰተ የምግብ እጥረት ምክንያት የረሃብ አደጋ እያንዣበበ መሆኑን ተከትሎ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ዓለም አቀፍ ግፊት…
-

የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሀገር ውስጥ የተመረቱ ምርቶችን ቅድሚያ ሰጥተው እንዲገዙ ውሳኔ መተላለፉን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ።
ውሳኔው የተላለፈው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ባካሄደው የ2016 ዓ.ም. የሁለተኛው ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ነው። ማክሰኞ የካቲት 26/2016 ዓ.ም. መካሄድ በጀመረው ግምገማ በሦስት ዘርፎች ሪፖርቶች መቅረባቸውን አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል። የሚኒስትር መሥሪያ ቤቶቹ ሪፖርቶች የቀረቡት በአስተዳደር እና ፍትሕ፣ በማኅበራዊ እና በኢኮኖሚ ዘርፎች ተከፋፍለው ነው። የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪን…
-

የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል በተደረሰው ስምምነት አፈጻፈም ግምገማ ላይ በመሳተፍ፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ስላሉ ግጭቶች ሊወያዩ ነው።
በትግራይ ሲካሄድ የነበረውን ጦርነት ለማስቆም በተደረገው ጥረት ውስጥ ጉልህ ሚና እንደነበራቸው የሚነገርላቸው አምባሳደር ሐመር፣ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሂደትን በተመለከተ በሚካሄደው ግምገማ ላይ መሳተፍ ዋነኛ የአዲስ አበባ ጉዟቸው ዓላማ መሆኑን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መግለጫ አመልክቷል። በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ በተባባሰው የአማራ ክልል ግጭት እና ዓመታትን ባስቆጠረው የኦሮሚያ ክልሉ አለመረጋጋት ዙሪያ ሰላም ለማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት…
-

ላለፉት ሁለት ሳምንታት ገደማ በእስር ላይ የቆዩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ በአንድ መቶ ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ወሰነላቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት ውሳኔውን ያስተላለፈው መርማሪ ፖሊስ የስልክ ምርመራ ውጤት ለማቅረብ ባለመቻሉ መሆኑን የፖለቲከኛው ጠበቃ አቶ ቦና ያዞ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱ አቶ በቴ በዋስትና እንዲለቀቁ የፈቀደው ዛሬ ረቡዕ የካቲት 27/2016 ዓ.ም. ረፋድ 4፡00 ገደማ ላይ በዋለው ችሎት ነው። ችሎቱ ዛሬ የተሰየመው ባለፈው ሳምንት አርብ ዕለት በሰጠው ቀጠሮ መሠረት…
-

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ አንድ የመለማመጃ አውሮፕላን ከመንገደኞች አውሮፕላን ጋር አየር ላይ ተጋጭቶ በደረሰ አደጋ የሁለት ሰው ሕይወት አለፈ።
በሁለቱ አውሮፕላኖች ግጭት ሕይወታቸው ያለፈው በበረራ መለማመጃው አውሮፕልን ውስጥ የነበሩት የበረራ አስተማሪ እና ተማሪው መሆናቸውን ፖሊስ አስታውቋል። አውሮፕላኖቹ አየር ላይ ከተጋጩ በኋላ የበረራ መለማመጃ የሆነው አውሮፕላን በናይሮቢ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ብሔራዊ ፓርክ ወድቆ ውስጥ ወድቆ በመከስከሱ ነው ሁለቱ ሰዎች የሞቱት። ከመለማመጃው አውሮፕላን ጋር የተጋጨው 44 ሰዎችን አሳፍሮ ተንደርድሮ ከተነሳ ንብረትነቱ ሳፋሪሊንክ ከተባለ አየር መንገድ አውሮፕላን…
-

በምሥራቅ ወለጋዋ ነጆ ከተማ ተወልዶ ያደገው ኦብሳ አባተ፣ አሁን በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዛይድ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሜታ ቨርስ እና አፕላይድ ኤአይ ረዳት ተመራማሪ ነው።
ኦብሳ ወላጆቹ ከሕጻንነቱ ጀምሮ የተሻለ ትምህርት እንዲያገኝ መጣራቸውን ያስታውሳል። አዳማ በሚገኘው የኦሮሚያ ልማት ማኅበር አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪ የነበረው ኦብሳ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በጥሩ ውጤት ሲያጠናቅቅ፣ እኤአ በ2019 ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የነጻ ትምህርት ዕድል አግኝቶ ሄደ። በኤምሬትስ ትምህርቱን በጥሩ ሁኔታ በማጠናቀቁ በተማረበት ዩኒቨርስቲ የተመራማሪነት ዕድል አግኝቷል። አገሪቱም ነጻ የመኖርያ ፈቃድ ሰጥታዋለች። ይህ ስኬት…
-

በሰሜናዊ ጋዛ ህጻናት በረሃብ እየሞቱ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አስታወቁ።
እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት ጋዛ ከጥቅምት በኋላ የመጀመሪያ ጉብኝቱን በአልአውዳ እና በከማል አድዋን ሆስፒታሎች ማድረጉንም ዶ/ር ቴድሮስ ገልጸዋል። የዓለም ጤና ድርጅት በሆስፒታሎቹ ቅዳሜና እሁድ ባደረገውም ጉብኝት ሁኔታው “አሳዛኝ እና አስከፊ” ሆነውም እንዳገኟቸው ዶ/ር ቴድሮስ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው አጋርተዋል። በምግብ እጦት ምክንያት አስር ህጻናት እንደሞቱ ገልጸው ከፍተኛ የሆነ የተመጣጠነ የምግብ እጥረትም ተከስቷልም ብለዋል። ህጻናቱም ሆነ…
-

በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ በዓመታት ውስጥ ጠንካራ የዋንጫ ፍክክር የታየበት ዓመት ያለንበት የውድድር ዘመን ነው።
ሊቨርፑል ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር በነበረው ጨዋታ በተጨማሪ ሰዓት መጠናቀቂያ ላይ ያስቆጠራት ግብ መሪነቱን እንዲያስጠብቅ አስችላዋለች። እሑድ ዕለት በኢቲሃድ ማንችስተር ዩናይትድን ያስተናገደው ማንችስተር ሲቲ ደግሞ ከመመራት ተነስቶ 3 -1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ከመሪው ጋር ያለውን ልዩነት በድጋሚ በአንድ ነጥብ ማጥበብ ችሏል። ሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አርሰናል ዛሬ [ሰኞ] ምሽት ከሜዳው ውጪ ወራጅ ቀጠና የሚገኘውን ሼፊልድ ዩናይትድን…
-

የሪፐብሊካን ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ለመሆን ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር እየተፎካከሩ ያሉት ኒኪ ሄሊ በዋሽንግተን በተካሄደው የውክልና ምርጫ ትራምፕን አሸነፉ።
ባለፉት ጥቂት ወራት የፓርቲውን ውክልና ለማግኘት እየተደረገ ባለው ምርጫ ትራምፕ አስካሁን ሲያሸንፉ የቆዩ ሲሆን፣ የዋሽንግተኑ ውጤት ለሄሊ የመጀመሪያው ድል ነው። ኒኪ ሄሊ በአሜሪካ ታሪክ በሪፐብሊካን ፓርቲ የመጀመሪያ ዙር የዕጩነት ምርጫ ሂደት በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነዋል። ነገር ግን አስካሁን በተካሄዱት የውክልና ምርጫዎች ትራምፕ ሄሊን በሰፊ ልዩነት እየመሩ በመሆናቸው በሚመጣው ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ከፕሬዝዳንት ባይደን ጋር እንደሚፎካካሩ…