Category: Uncategorized
-

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋ ሮቢት ከተማ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሰው ሕይወት የጠፋበት ከባድ ግጭት መካሄዱን ነዋሪዎች ተናገሩ።
ከአዲስ አበባ በስተ ሰሜን ምሥራቅ 220 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሸዋሮቢት ከተማ ትናንት እሁድ የካቲት 24/2016 ዓ.ም. የተከሰተው ከባድ በግጭት ለሰዓታት የቆየ ነበር። ከዕኩለ ቀን በኋላ 7፡00 ሰዓት አካባቢ ተጀምሯል የተባለው ውጊያው እስከ ምሽት 4፡00 ሰዓት ገደማ ድረስ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች እንደዘለቀ ለደኅንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አራት የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል። በሸዋ ሮቢት በመከላከያ…
-

የካቲት 1966 ዓ.ም. የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ፀሐይ መጥለቅ የጀመረችበት ጊዜ ነበር።
ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከተሜ ኢትዮጵያውያን ወደ አደባባይ ወጡ። ይዘው በወጧቸው ጥያቄዎች የአጼውን ፀሐይ ቀስ በቀስ ማክሰም ጀመሩ። የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የኃይለ ሥላሴ መንግሥት ያስተዋወቀውን የትምህርት ዘርፍ ማሻሻያ በመቃወም ማስተማር አቆሙ። የሁለተኛ ደረጃ እና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “መሬት ላራሹ”፣ “የብሔር መብት ይከበር”፣ “ድህነት ወንጀል አይደለም” የሚሉ መፈክሮችን አንግበው አደባባይ ወጡ። ታክሲ ነጂዎች አድማ…
-

አምስት ወራት ያስቆጠረውን የእስራኤል ጋዛ ጦርነትን ጋብ ለማድረግ በሚያስችል ንግግር ላይ ለመሳተፍ የሐማስ ልዑካን ግብፅ ካይሮ መግባታቸውን ተከትሎ አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ይደረሳል የሚል ተስፋ ተፈጥሯል።
ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን እስራኤል “ከሞላ ጎደል” የተኩስ አቁም ስምምነቱን መቀበሏን ገልጸዋል። አሁን ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የስድስት ሳምንታት የተኩስ አቁም ስምምነት ተጨማሪ እስራኤላውያን ታጋቾች እና ፍልስጤማውያን አስረኞች ይለቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሁለቱ ወገኖች ተኩስ እንዲያቆሙ የሚደረገው ግፊት የተጠናከረው ባለፈው ሐሙስ ጋዛ ውስጥ እርዳታ በጫኑ ተሽከርካሪዎች ዙሪያ ከተሰበሰቡ ሰዎች መካከል ቢያንስ 112 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ ነው።…
-

የመን ሁቲዎች አማጺያን በቀይ ባሕር በኩል በሚያቋርጡ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸም ከመጀመሩ ከወራት በኋላ የመጀመሪያዋ ግዙፍ መርከብ ሰመጠች።
በብሪታኒያ የተመዘገበችው የጭነት መርከብ ማዳበሪያ ጭና በቀይ ባሕር በኩል ለማቋረጥ ስትሞክር ነበር ከሁለት ሳምንት በፊት በኤደን ባሕረ ሰላጤ ላይ በሁቲ ታጣቂዎች ሚሳኤል ተመትታ የቆመችው። የየመን መንግሥት ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ሪቢይማር የተባለችው መርከብ ጥቃት ከተፈጸመባት በኋላ ውሃ ወደ ውስጧ እየገባ ለቀናት በባሕሩ ላይ ስትዋልል ቆይታ ሰምጣለች። በኢራን የሚደገፉት ሁቲ አማጺያን ካለፈው ኅዳር አንስቶ በቀይ ባሕር የሚያቋርጡ መርከቦችን…
-

ቅዳሜ ዕለት ተከታታይ የሪፐብሊካን ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ውድድርን ያሸነፉት ዶናልድ ትራምፕ፣ የፓርቲው ዕጩ ለመሆን ተቃርበዋል።
ከድላቸው በኋላም ተቀናቃኛቸውን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን ስደተኞች ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ እንዲገቡ መንገድ ከፍተዋል ሲሉ ከሰዋቸዋል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሚዙሪ፣ ሚቺጋን እና አይዳሆ የውክልና ድምጽ ሰጪዎችን [ካውከስ] ድጋፍ ሙሉ በሙሉ በማግኘት አሸነፈዋል። የ77 ዓመቱ ትራምፕ በቨርጂኒያ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ለደጋፊዎቻቸው እንደተናገሩት “ለሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ሆነው ለመቅረብ እንደሮኬት እየተተኮስኩ ነው” ብለዋል። በሚቀጥለው ሳምንት ዕጩ መሆናቸውን እንደሚያረጋግጡም…
-

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስያ አገራት ለሚያደርጋቸው በረራዎች ይጠቀምበት በነበረው የሶማሊያ የአየር ክልል በኩል መብረር ማቆሙን አስታወቀ።
አየር መንገዱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከሶማሊያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች “አስተማማኝ የአየር ትራፊክ አገልግሎት” ባለማግኘቱ እንደሆነ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ለቢቢሲ አማርኛ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስያ ለሚደርጋቸው በረራዎች “ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ” ይጠቀምበት በነበረው የሶማሊያ አየር ክልል መብረር ያቆመው፤ የአየር መንገዱ አውሮፕላን ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓ.ም. በአገሪቱ የአየር ክልል…
-
-

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ባልተካሄደባቸው እና በሚደግምባቸው በአራት ክልሎች በመጪው ሰኔ ወር መጀመሪያ ምርጫ ሊያካሂድ ነው።
ሰኔ 6፤ 2016 ዓ.ም. በሚካሄደው ምርጫ በ29 ምርጫ ክልሎች ውስጥ ለሚገኙ ዘጠኝ የህዝብ ተወካዮች እና 26 የክልል ምክር ቤቶች ወንበር ነው። ቦርዱ ይህንን የጊዜ ሰሌዳ በተመለከተ ዛሬ አርብ የካቲት 22፤ 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባው ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በጊዜ ሰሌዳው ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው። በቦርዱ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ካለፈው ጥር ወር መጨረሻ ጀምሮ…
-

በኢትዮጵያ ምርጫ በየአምስት ዓመቱ እንደሚካሄድ በሕግ የተደነገገ ሲሆን፣ እስካሁንም ስድስት ጠቅላላ ምርጫዎች ተካሂደዋል።
ስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ ሁለት ጊዜ ከተራዘመ በኋላ በ2013 ዓ.ም. ተካሂዷል። አብላጫውን ድምጽ ያሸነፈው ብልጽግና ፓርቲም መንግሥት ከመሠረተ ሁለት ዓመት አልፎታል። ምርጫው በሁለት ዙሮች ቢካሄድም፤ ጥቂት በማይባሉ [የምርጫ] ክልሎች ግን እስካሁን አልተካሄደም። ለዚህም በዋናነት የደኅንነት ስጋት እና ሌሎች ምክንያቶች ይነሳሉ። ሰኔ 14/2013 ዓ.ም. እና መስከረም 20/2014 ዓ.ም. የተካሄደው ስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ የአማራ፣ የአፋር፣ የኦሮሚያ፣ የቀድሞው ደቡብ…
-

እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ባለው የማያባራ ጥቃት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ከ30 ሺህ በላይ መድረሱን በሃማስ አስተዳደር ስር ያለው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ከተገደሉት መካከል አብዛኛዎቹ ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸውንም ከጤና ሚኒስትሩ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ከመስከረም መጨረሻ በኋላ የተገደሉት ፍልስጤማውያን ቁጥር ጋዛ ካላት 2.3 ሚሊዮን ያህል ህዝብ 1.3 በመቶው ነው ተብሏል። የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ጦርነቱ ምን ያህል አስከፊ መሆኑንም አመላካች ነው ተብሏል። የተገደሉት ሰዎች አኃዝ ምን ያህሉ ሰላማዊ ዜጎች ምን ያህሉ ታጋዮች እንደሆኑ አይገልጽም። ሚኒስቴሩ በባለፉት 24 ሰዓታት…