Category: Uncategorized
-

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማጭበርበር ክስ ለኒውዮርክ ግዛት 355 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ እንዲከፍሉ ተወሰነባቸው።
ትራምፕ ያላቸውን ንብረት በተመለከተ ለባንኮች ሐሰተኛ መረጃዎችን ሰጥተዋል የሚለውን ጨምሮ ሌሎች ክሶች ቀርበውባቸው ነበር። ብያኔውን ያስተላለፉት ዳኛ አርተር ኢንጎሮን ከገንዘብ ቅጣቱ በተጨማሪም ትራምፕም ሆነ ድርጅታቸው ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት በኒውዮርክ ከሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት ብድር እንዳይጠይቁ እንዲሁም በኒውዮርክ በሚገኙ ኩባንያዎቻቸው ዳይሬክተር ሆነው እንዳያገለግሉም እግድ አስተላልፈውባቸዋል። ከሳቸው በተጨማሪም ሁለቱ ልጆቻቸው ኤሪክ ትራምፕ እና ዶናልድ ትራምፕ ጁኒየር በኒውዮርክ በሚገኙ…
-

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለሩሲያዊው ተቃዋሚ አሌክሲ ናቫልኒ ሞት ፑቲን ተጠያቂ ስለመሆናቸው “ምንም ጥርጥር የለውም” ሲሉ ተናገሩ።
ከዋይት ሃውስ መግለጫ የሰጡት ባይደን አሜሪካ ሩሲያን ለመቅጣት “የተለያዩ አማራጮችን” እየተመለከተች ነው ብለዋል። የፑቲንን አገዛዝ በሰላ በመተቸት የሚታወቀው የ47 ዓመቱ ናቫልኒ በአርክቲክ ሰርክ እስር ቤት ሕይወቱ ማለፉን የሩሲያ የማረሚያ ቤት አገልግሎት አስታውቋል። ናቫልኒ በእስር በነበረበትም ወቅት በርካታ የአሜሪካ መንግሥት ባለስልጣናት እና ሕግ አውጪዎች ስጋታቸውን ሲገልጹም ነበር። ተቃዋሚው እና የፑቲን ቀንደኛ ተቺ የሆነው ናቫልኒ በበርካቶች ፖለቲካዊ…
-

በቻይና ከአህዮች ቆዳ የሚዘጋጀው እና ኢጂያዎ የሚሰኘው ባህላዊ መድኃኒት ፈላጊው ብዙ ነው። መድኃኒቱ ጤናን እንደሚያጎለበት እና ወጣት ሆኖ ለመቆየት እንደሚረዳ ይታመናል።
መድኃኒቱ ሚዘጋጀው የአህያ ቆዳው ተቀቅሎ ከሚወጣው ንጥረ ነገር ነው። ይህ ንጥረ ነገር በዱቄት፣ በእንክብል ወይም በፈሳሽ መልክ ይዘጋጃል። አሊያም ምግብ ውስጥ ሊጨመር ይችላል። ሆኖም የአህያ ቆዳ ገበያን ክፉኛ የሚቃወሙ ሰዎች አሉ። እነዚህ የመብት ተሟጋቾች እንደ ስቲቭ ያሉ ሰዎች እና ሕይወታቸውን የመሠረቱባቸው አህዮች ኢጂያዎ የተሰኘው ቅመም ላይ የሚፈጠረው ያልተረጋጋ ፍላጎት ተጠቂ ናቸው ይላሉ። በአውሮፓውያኑ 2017 የተመሠረተው…
-

በመቶዎች የሚቆጠሩ ከሰሜን ኮሪያ አገዛዝ አምልጠው የሸሹ ታዳጊዎችን በመታደግ ጀግና ተብለው የነበሩት የደቡብ ኮሪያው ፓስተር በታደጓቸው ለአካለ መጠን ባልደረሱ ታዳጊዎች ላይ ወሲባዊ ጥቃቶች ፈጽመዋል በሚል ለእስር ተዳረጉ።
የ67 ዓመቱ ቹን ኪዎን በሴኡል በሚገኘው ለታዳጊዎቹ በከፈቱት የአዳሪ ትምህርት ቤታቸው ውስጥ ባደረሱት ወሲባዊ ጥቃት የአምስት ዓመት እስር ተፈርዷባቸዋል። ፓስተሩ ለበርካታ አስርት ዓመታት እንደ አዳኝ ይቆጠሩ የነበሩ ሲሆን ከሰሜን ኮሪያ አገዛዝ ለሚያመልጡት በርካቶችንም መንገድ በማመቻቸት ይሞገሱም ነበር። ፓስተሩ ለእስር የተዳረጉት መስከረም ወር ላይ በደቡብ ኮሪያ መዲና ሴኡል ነበር። ፖሊስ እንደሚለው ፓስተሩ ከሰሜን ኮሪያ አገዛዝ ሸሽተው…
-

የሩሲያው ተቃዋሚ ፖለቲከኛ አሌክሲ ናቫልኒ በእስር ላይ ሳለ ሕይወቱ ማለፉን የሩሲያ መንግሥት ባለሥልጣናት አስታወቁ።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዋነኛ ተቺ የነበረው ፖለቲከኛ ናቫልኒ፣ እስር ቤት የገባው ከሁለት ዓመት በፊት በአውሮፓውያኑ 2021 ነው። ባለፈው ታኅሣሥ ወር በጣም አስቸጋሪ ወደሚባለው እና ከዋና ከተማዋ ሞስኮ ሰሜን ምሥራቅ ሳይቤሪያ ውስጥ ወደ ሚገኘው ቀዝቃዛው የግዞት እስር ቤት ተዛዋውሮ ነበር። Russian opposition politician Alexei Navalny has died while in prison, Russian government officials have announced.…
-

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐሙድ በ37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ አርብ የካቲት 8/2016 ዓ.ም. አዲስ አበባ ገቡ።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ወደ አዲስ አበባ የመጡት ኢትዮጵያ ነጻ አገርነቷን ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር በተፈራረመችው የመግባቢያ ሰነድ ምክንያት በሁለቱ አገራት መካከል ውዝግብ ከተፈጠረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ፕሬዝዳንቱ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲኤታዋ ብርቱካን አያኖ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ጽህፈት ቤታቸው…
-

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመርማሪ ቦርድ በሰሜን ጎጃም በመርዓዊ ከተማ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተፈጽሟል የተባለውን የሰላማዊ ዜጎች ግድያ ሊመረምር መሆኑን አስታወቀ።
መርማሪ ቦርዱ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ቢያንስ 45 ሲቪል ሰዎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን አስመልክቶ ያወጣውን ሪፖርት ተከትሎም ምርመራ ሊያደርግ መሆኑንም ምክትል ሰብሳቢዋ ዶ/ር ነጃት ግርማ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሰብሳቢዋ ሪፖርቱንም ተከትሎ ቦርዱ ባደረገው ስብሰባ ወደ መርዓዊ ከተማ አቅንቶ ምርመራ እንደሚያደርግ ገልጸው ጉዟቸው መቼ እንደሚሆን ከመግለጽ ተቆጥበዋል። ኢሰመኮ “ማንነታቸውን አረጋግጬያለሁ” ያላቸው ቢያንስ 45 ሰዎች “ለፋኖ ድጋፍ…
-

የሶማሊያ መንግሥት ባለሥልጣናት በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ውስጥ ባለ የደኅንነት ስጋት ምክንያት ማንም ሰው የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) እንዳያደርግ ክልከላ ጣሉ።
የዋና ከተማዋ አስተዳደር ቃል አቀባይ ሳልህ ዲሬ እገዳውን በተመለከተ እንደተናገሩት፣ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛው ጭምብልን ወንጀለኞች ማንነታቸውን በመሸፈን ሕገ ወጥ ድርጊቶችን ለመፈጸም እያዋሉት በመሆኑ ነው ጥቅም ላይ እንዳዕውል ክልከላ የተጣለው። ከሦስት ዓመት በፊት በመላው ዓለም ተከስቶ ዋነኛ የጤና ስጋት የነበረውን ኮቪድ 19 ተከትሎ ነበር ማስኮች በሁሉም ሰው በስፋት ጥቅም ላይ መዋል የጀመሩት። በሶማሊያ ዋና ከተማ…
-

ወረርቲ ካብ ትግራይ ይውፅኡ፤ ትግራይ ሓራ ትውፃእ፤ ሓገዝ ንዝጠመዩ ፤ ዝብሉ መልእኽታታት ዘጋወሐ ሰላማዊ ሰልፊ ተጋሩ ኣብ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ፊት ንፊት ስቴት ዲፓርትሜንት ይካየድ ኣሎ።
ወራሪዎች ትግራይን ለቀው ይውጡ; ትግራይ ነጻ ትወጣለች; ለተራቡ ሰዎች እርዳታ; በዋሽንግተን ዲሲ ከስቴት ዲፓርትመንት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው። Invaders leave Tigray; Tigray is a free youth; Help for the Talking People; A peaceful demonstration is being held in front of the State Department in Washington, DC.
-

ዲሞክራሲያዊ ምሕደራ ትግራይ ንምምሕያሽ ዝጠመተ መድረኽ ኣብ ከተማ መቐለ ይሳለጥ ኣሎ ፡፡
ግዝያዊ ምምሕዳር ትግራይ ጌታቸው ረዳ ሓዊሱ ብርክት ዝበሉ ላዕለዎት ኣመራርሓ ግዝያዊ ምምሕዳር ትግራይ ብፍልይቲ ልኡኽ ውድብ ሕቡራት ሃገራት ኣብ ቀርኒ ኣፍሪካ ኣና ቴተህ ዝተመረሐ ልኡኽ ጉጅለ ዉድብ ሕቡራት ሃገራት ፣ተነሓነሕቲ ዉድባት ትግራይን ፕሮፌሰር ዘርኢ ዘናይ ኣለም ሰገድ ሓዊሱ ብርክት ዝበሉ ሙሁራትን ኣብቲ መድረኽ ተረኺቦም ይሳተፉ ኣለው ፡፡ ኣብቲ መድረኽ መደረ ዘስምዓ ብፍልይቲ ልኡኽ ውድብ ሕቡራት…