Category: Uncategorized
-

ኢንተርኔትን በመጠቀም ስለ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በመስበክ “የአምላክ ተጽእኖ ፈጣሪ” የሚል ስያሜ አግኝቶ ለነበረው ታዳጊ ቤተ ክርስቲያኗ የቅድስና ማእረግ ልስትሰጠው እንደሆነ ተገለጸ።
ቤተ ክርስቲያኗ ቅዱስ ብላ ልትጠራው የተዘጋጀችው ታዳጊ ካርሎ አኩቲስ በአውሮፓውያኑ 2006 በካንሰር ህይወቱ ያለፈ ሲሆን ገና የ15 ዓመት ታዳጊ ነበር። የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከአውሮፓውያኑ 1980 በኋላ ለተወለዱ፣ ‘ሚለኒያል’ ለሚባሉት ትውልድ የምትሰጠው የመጀመሪያ የቅድስና ማዕረግ ይሆናል። የቤተ ክርስቲያኗ ሊቃነ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ታዳጊው ያደረገውን ሁለተኛ ተአምር በቅርቡ እውቅና ሰጥተዋል። በፍሎረንስ የዩኒቨርስቲ ተማሪ በጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት…
-

የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑዔል ማክሮን የሀገራቸው ፖሊስ ኒው ካሌዶኒያ በተሰኘችው ግዛት “አስፈላጊውን ጊዜ ያክል” እንደሚቆይ ገለጡ።
ፕሬዝደንቱ በተቃውሞ እየታመሰች ወዳለችው ደሴት አቅንተዋል። ማክሮን እንዳሉት ቁጥራቸው 3000 ገደማ የሚሆኑ የፈረንሳይ ፖሊስ አባላት አስፈላጊ ከሆነ በፓሪስ ኦሊምፒክ ጊዜም ቢሆን በደሴቷ ይቆያሉ። ባለፈው ሳምንት የወጣ የምርጫ ሕግን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ ሁለት የፖሊስ መኮንኖችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ካናክ የተሰኙት የሀገሪቱ ጥንታዊ ሕዝቦች የፈረንሳይ ዜጋ የሆኑ ነዋሪዎች በምርጫው እንዲሳተፉ መፈቀዱ ትክልል አይደለም ሲሉ ድምፃቸውን…
-

በሰው ልጆች ተፈጥሮ ከተለመደው ውጪ የሰውነት ክፍሎቹ በተቃራኒው ለሚገኙት የዘጠኝ ዓመት ታዳጊ በኢትዮጵያ ውስጥ ውስብስብ እና የተሳካ የልብ ቀዶ ሕክምና ተደርጎለት በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል።
በኢትዮ-ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል ቀዶ ሕክምናውን የመሩት የሕጻናት እና የአዋቂዎች የልብ ሐኪም ዶ/ር ሺቢቆም ታምራት ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ በተለምዶ ከሚታወቀው አፈጣጠር በተቃራኒው ልቡ በቀኙ በኩል ለሚገኘው ታዳጊ ከአሥር ቀናት በፊት ቀዶ ሕክምና ማካሄድ ተችሏል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ቡርጂ ዞን፣ ሶያማ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የታዳጊው አባት አቶ ጂማ ሒዶ ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ የልጃቸው ችግር “በጣም ከባድ” እንደሆነና “በኢትዮጵያ ደረጃ…
-

በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ናይጄሪያ ቢያንስ ሰባት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በጄኔሬተር ጭስ ታፍነው መሞታቸው ተገለጸ።
በነዳጅ በበለፀገችው የናይጄሪያዋ ባይልሳ ግዛት በሚገኝ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ባለ የሙዚቃ ስቱድዮ ሳሉ ነው ተማሪዎቹ ከጄኔሬተር በሚወታ ጭስ ታፍነው ሕይወታቸው ያለፈው። ወጣቶቹ ወንዶች ሰኞ እስከ ምሽት ድረስ ሠርተው ስቱድዮውን ቆልፈው ተኝረው ነበር። ጄኔሬተሩን ሳያጠፉት እንደተኙም ተገልጿል። የፖሊስ ምርመራ እየተካሄደ ቢሆንም ከጄኔሬቴሩ በሚወጣ ካርቦን ሞኖክሳይድ ጭስ ሳይታፈኑ እንዳልቀረ ተገልጿል። በናይጄሪያ ባለው የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ምክንያት ብዙዎች በነዳጅ…
-

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እሳቸውን ጨምሮ የሐማስ መሪዎች በጋዛ ግጭት ፈጽመዋል በተባለው ወንጀል ምክንያት የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) የእስር ትዕዛዝ እንዲወጣባቸው መጠየቁን በቁጣ አውግዘዋል።
ኔታንያሁ “ዲሞክራሲያዊት እስራኤል” “ከጅምላ ገዳዮች” ካሏቸው ጋር እኩል መፈረጇን በመጸየፍ እንደማይቀበሉትም ገልጸዋል። የኔታንያሁን አስተያየት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተጋብተውታል። በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ምንም ዓይነት ተመሳሳይነት የለም ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ኔታንያሁ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ዮአቭ ጋላንት በጋዛ ለተፈጸሙ የጦር እና በሰው ልጆች ላይ ለተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂ ናቸው ብሎ ለማመን የሚበቁ ምክንያቶች አሉ ሲሉ የአይሲሲ…
-

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦር በፕሬዚዳንት ፊሊክስ ታሺኬዲ ላይ የተቃጣውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ማክሸፉን ገለጸ።
በዋና ከተማዋ ኪንሻሳ ሊደረግ የነበረው መፈንቅለ መንግሥት የውጭ ተዋጊዎችን እና የኮንጎ ዜጎችን ያሳተፈ እንደነበር ጦሩ አስታውቋል። የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦር ቃለ አቀባይ ብሪጋዲየር ጄኔራል ሲልቪን ኤኬንጌ በርካታ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና ሁኔታው መረጋጋቱን ለመንግሥታዊው አርቲኤንሲ ቴሌቪዥን ተናግረዋል። እሁድ ማለዳ ታጣቂዎች የቀድሞ ኢታማዦር ሹም እና የፕሬዚዳንቱ የቅርብ አጋር በሆኑት ቪታል ካመርሄ ቤት ላይ ጥቃት ካደረሱ…
-

የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ሩሲያ በቅርቡ የኻርኪቭ ከተማን መቆጣጠሯን ተከትሎ በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ጥቃቷን ልታጠናከር እንደምትችል አሳስበዋል።
የጦር መሣሪያ እጥረት ያጋጠማቸው የዩክሬን ወታደሮች እየገሰገሱ እየመጡ ያሉ የሩሲያ ወታደሮችን መቋቋም አቅቷቸዋል። ዜሌንስኪ፤ የጦር ሠራዊት ሞራል እና ቁሳቁስ እንዳጠረው አምነው በርካታ ብርጌዶች አሁን ባዶ ሆነዋል ብለዋል። ኤኤፍፒ ለተሰኘው የዜና ወኪል ድምፃቸውን የሰጡት ፕሬዝደንቱ የሀገሪቱ አየር ኃይል እንደተመናመነ አሳውቀው አጋር ሀገራት ተጨማሪ የአየር መከላከያ እና ተዋጊ ጄቶች እንዲልኩ ተማፅነዋል። “ዩክሬንን ለመከላከል ከሚያስፈልገን አቅም አሁን ያለን…
-

የጆርጂያዋ ፕሬዝደንት በሀገሪቱ ለሳምንታት ከፍተኛ ተቃውሞ ያሰነሳውን “የውጭ ኤጀንት” የተሰኘው ሕግ ውድቅ አደረጉት።
ባለፈው ማክሰኞ የጆርጂያ የሕዝብ እንደራሴዎች ያፀደቁት አወዛጋቢ አዋጅ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ገለልተኛ ሚድያዎች 20 በመቶ ገቢያቸውን የሚያገኙት ከሀገሪቱ ውጭ ከሆነ “የውጭ ኃይሎችን አቋም የሚያንፀባርቁ” ተብለው ይፈረጁ ይላል። ፕሬዝደንት ሳሎሜ ዞራቢቺቪሊ እንዳሉት አዋጁ “በመንፈስ እና በቅርፅ ሩሲያዊ ነው”፤ አልፎም ጆርጂያ የአውሮፓ ኅብረት አባል ለመሆን የምታደርገውን ሂደት የሚያደናቅፍ ነው። ፕሬዝደንቷ አዋጁን ውድቅ ቢያደርጉትም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጆርጂያን…
-

በሰሜናዊ ፈረንሳይ ሩየን ከተማ የሚገኝ ምኩራብ በማቃጠል የተጠረጠረው ግለሰብ በፖሊስ ጥይት መገደሉን የአገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።
የሩየን ከንቲባ ኒኮላስ ማየር ሮሲግኖል በበኩላቸው በምኩራቡ ላይ የተፈጸመው ጥቃት የአይሁድ ማህበረሰብን ብቻ ሳይሆን “መላውን የከተማዋ ነዋሪ ድንጋጤ ውስጥ የከተተ ክስተት ነው” ብለዋል። የፈረንሳይ ሚዲያዎች ተጠርጣሪው አልጀሪያዊ ዜግነት ያለው እንደሆነ እና ፈረንሳይን ለቆ እንዲወጣ ውሳኔ ተላልፎበት በዚህ ላይ ይግባኝ ብሎ እየተጠባበቀ እንደነበር ዘግበዋል። ከምኩራቡ ጢስ ሲወጣ በመታየቱ ፖሊስ ማለዳ 12፡45 ተጠርቷል። ጥቃት ፈጻሚው በትልቅ የቆሻሻ…
-

የቴክሳሱ ገዥ ግሬግ አቦት እአአ በ2020 የብላክ ላይቭስ ማተር ተቃዋሚውን በመግደል የተከሰሰውን ግለሰብ በይቅርታ ለቀቁት።
የቀድሞው የአሜሪካ ወታደር ሳጅን ዳንኤል ፔሪ በኦስቲን የኡበር ሹፌር ሆኖ ሲሠራ ነበር ተቃዋሚዎች ወደተሰበሰቡበት ጎዳና ያመራው። ከተቃዋሚዎቹ አንዱ የሆነው ጋሬት ፎስተር ጠመንጃ ይዞ ወደ መኪናው ሲቀርብ፤ ፔሪ ተኩሶ ይገድለዋል። ፔሪ እራሱን ለመከላከል ያደረገው መሆኑን ቢናገርም ፍርድ ቤት 25 ዓመት እስራት አስተላልፎበታል። 28 ዓመት ነበረው የቀድሞ የአሜሪካ አየር ኃይል መካኒክ ፎስተር፤ ህይወቱ ባለፈበት ወቅት ከፊል-አውቶማቲክ ኤኬ-47…