Category: Uncategorized
-

በጥይት የተመቱት የስሎቫኪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ፊኮ ለሕይወታቸው የሚያሰጋ ሁኔታ አለመኖሩን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ቶማስ ታራባ፤ የፊኮ ቀዶ ሕክምና “በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን” እና “በመጨረሻም እንደሚተርፍ እገምታለሁ” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ፊኮ በሃንድሎቫ ከተማ በደረሰባቸው ጥቃት ከባድ ጉዳት ስላጋጠማቸው “በህይወት ለመቆየት እየታገሉ ነው” ሲሉ የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ቀደም ብለው ገልጸው ነበር። አንድ ተጠርጣሪ ተኩስ በተከፈተበት ቦታ በቁጥጥር ስር ውሏል። የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ማቱስ ሱታጅ ኢስቶካ ጥቃቱን ፖለቲካዊ የመግደል ሙከራ ሲሉ ገልጸውታል።…
-

በአዲግራት ሆስፒታል ነርስ የሆነችው ሲስተር ካህሳ ሀጎስ በትግራይ ጦርነት ወቅት ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች ላደረገችው ሙያዊና ሰብአዊ ድጋፍ ግሎባል አፌይርስ ከተባለው የካናዳ ድርጅት ሽልማት ተበርክቶላታል።
ድርጅቱ የካናዳ ዲፕሎማሲያዊ እና ቆንስላ ትብብሮችን የሚያስተዳድር ሲሆን የሀገሪቱን አለም አቀፍ ንግድ የሚያስፋፋ እና አለም አቀፍ ልማት እና ሰብአዊ እርዳታን የሚመራ መንግስታዊ ክፍል ነው። ሲስተር ካህሳ ሀጎስ፤ የካናዳ ድርጅት ከተባበሩት መንግስታት ጋር በመተባበር የሚያበረክተው “ሰላምና ደህንነት በሴቶች” የተሰኘው ሽልማት ተቀባይ ሆናለች። ካህሳ “ከ2013 ጀምሮ ላበረከትኩት አስተዋጽዖ የተሰጠኝ ነው። ለሁለት ዓመታት ያህል የፆታዊ ጥቃት ሰለባዎችን እንከባከብ…
-

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን፣ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ያወደሙትን ለመጠገን መክፈል አለባቸው አሉ።
በዩክሬን፣ ኪየቭ ውስጥ ባደረጉት ንግግር አሜሪካ በግዛቷ ያሉ የሩሲያ ኃብት ንብረቶች ላይ ማዕቀብ የመጣል አቅም እንዳላት ገልጸዋል። እነዚህን ኃብት ንብረቶች ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት እንደሚያውሉም አክለዋል። ዩክሬን “ለኔቶ እየቀረበች ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ለዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ወታደራዊ ዕርዳታ “መንገድ ላይ ነው” ብለዋል። “ፑቲን ያወደመውን ሩሲያ መክፈል አለባት። ዓለም አቀፍ ሕግ ያንን ያዛል። የዩክሬን ሕዝብም መልሶ ግንባታው…
-

ዋይት ሐውስ፤ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ የጦር መሣሪያ ለእስራኤል ለመለገስ ማቀዱን ለሕግ መወሰኛው ምክር ቤት አሳውቋል።
ምንም እንኳ እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ የምትገኘው ራፋህ ላይ ልታደርግ ያሰበችውን ወታደራዊ እርምጃ አሜሪካ ብትቃወምም ድጋፉን ለማድረግ ግን አስባለች። ዋይት ሐውስ ባለፈው ሳምንት ለእስራኤል ሊልካቸው ያሰባቸውን ቦምቦች ለጊዜው የገታው ቦምቦቹ በርካታ ሰዎች በተሰበሰቡበት ከተጣሉ ሰላማዊ ዜጎች ይገደላሉ በሚል ስጋት ነው። የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን እንደገለጡት አዲስ ዕቅድ በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት [ኮንግረስ] መፅደቅ አለበት። 700 ሚሊዮን ዶላር…
-

ለወራት እስራኤል በተቀናጀ ጥቃት እየፈጸመችባት ባለችው ጋዛ በተፈጸመ ጥቃት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኛ ተገደሉ።
በትናንትናው ዕለት ግንቦት 5/ 2016 ዓ.ም የመንግሥታቱ ድርጅት ሠራተኞች በደቡባዊቷ ጋዛ ራፋህ ከተማ ወደሚገኘው የአውሮፓ ሆስፒታል ጉዞ ላይ እያሉ በተፈጸመ ጥቃት አንድ የተቋሙ ሠራተኛ መገደሉ ይፋ ተደርጓል። ከሟቹ በተጨማሪ ሌላ አንድ ግለሰብም በጥቃቱ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት አስታውቋል። ጥቃቱ ሲፈጸም ተጎጅዎቹ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተሽከርካሪ ተሳፍረው እየተጓዙ ነበር። የመንግሥታቱ ድርጅት ጥቃቱ መፈጸሙን ይግለጽ እንጅ…
-

ለተቃውሞ የወጡ እስራኤላውያን ወደ ጋዛ የሚሄዱ የእርዳታ መኪኖችን በማገድ የተጫኑ ምግቦችን አውርደው መንድ ላይ በመወርወር እና የእህል ከረጢቶችን ቀደው በተኑ።
እስራኤላውያኑ ይህንን የፈጸሙት በትናትናው ዕለት እስራኤል በኃይል ተቆጣጥራት በምትገኘው ዌስት ባንክ ነው። ከዮርዳኖስ የመጡት እርዳታ የጫኑት መኪኖች ከኬብሮን በስተምዕራብ ታርኩሚያ የፍተሻ ጣቢያ እያቀኑ ነበር ተብሏል። እርዳታው በከፍተኛ የምግብ እጥረት እና ጠኔ ለተመቱ ፍልስጤማውያን የሚውል ነበር። ዋይት ሃውስ ይህንን ጥቃት አውግዞ የእርዳታ ጭነቶቹን መዘረፍ “አሳፋሪ ስራ” ሲል ገልጾታል። ከተቃውሞው ጀርባ ያለው ቡድን እስራኤላውያን ታጋቾች በጋዛ አለመለቀቃቸውን…
-
በዘረመል ምህንድስና የተሻሻለ የአሳማ ኩላሊት በንቅለ ተከላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለገሰው ግለሰብ ከህክምናው ሁለት ወራት በኋላ ህይወቱ ማለፉን ሆስፒታሉ አስታወቀ።
የ62 ዓመቱ ሪቻርድ “ሪክ” ስላይማን ቀዶ ህክምናውን በመጋቢት ወር ከማድረጉ በፊት በከፋ የኩላሊት ህመም ይሰቃይ ነበር። ህይወቱ ያለፈው በንቅለ ተከላው ምክንያት ስለመሆኑ ምንም ምልክት የለም ሲል የማሳቹሴትስ አጠቃላይ ሆስፒታል (ኤምጂኤች) እሑድ ዕለት አስታውቋል። በዘረመል ምህንድስና ከተሻሻሉ አሳማዎች የተገኙ ክፍሎችን ሌሎች የመተካት ሙከራ ቀደም ሲል አልተሳካም ነበር። የስላይማን ቀዶ ህክምና ግን ታሪካዊ ምዕራፍ ነው ተብሎ ተወድሷል።…
-

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪ የግል ጥበቃ የሚያደርግላቸውን ‘ሪፐብሊካን ጋርድ’ ኃላፊን አባረሩ።
ይህን እርምጃ የወሰዱት ሁለት ከፍተኛ የዩክሬን የጦር መኮንኖች እሳቸውን በማስገደል ሴራ ተጠርጥረው ከታሰሩ በኋላ ነው። የግል ጥበቃ የሚያደርግላቸውን ቡድን የሚመራው ሰው ሜጀር ጄኔራል ሰርሂ ረድ ይባላሉ። ከ2019 ጀምሮ በዚሁ የፕሬዝዳንቱ ጥበቃ ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል። ዜለንስኪ ኃላፊውን ካባረሩ በኋላ ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡም። ይሁንና ‘የሪፐብሊካን ጋርድ’ አስተዳደር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደረሰበት በተባለው የግድያ ሴራ ምክንያት የዜለንስኪም ሆነ…
-

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በአሜሪካ የሚኖሩ ‘ተፈላጊዎች’ ተላልፈው እንዲሰጡ ትብብር እንዲደረግ ለአሜሪካው አምባሳደር ጠየቀ።
የፌደራል ፖሊስ ጥያቄውን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ለሆኑት ኤርቪን ማሲንጋ ትናንትና ግንቦት 2/2016 ዓ.ም ማቅረቡን በዚያው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። ኢትዮጵያ “የአገሪቱን ሰላምና ደህንነት በማወክ እፈልጋቸዋለሁ” ያለቻቸውን ሰዎች ተላልፈው እንዲሰጧት ትብብር የተጠየቀውም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል እና አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በትናንትናው እለት ባደረጉት ውይይት መሆኑን መግለጫው ጠቁሟል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ…
-

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታንያሁ እስራኤል ‘ብቻዋን ፀንታ ትቆማለች’ አሉ።
ይህን ያሉት አሜሪካ የጦር መሣሪያ ለእስራኤል የመላኩን ጉዳይ አጤነዋለሁ ስትል መዛቷን ተከትሎ ነው። አሜሪካ ይህን አቋም ለመውሰድ እየተገደደች ያለችው ናታንያሁ በጋዛ ራፋህ አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ እንዳይከፍቱ ከባይደን የተላከላቸውን መልእክት ቸል በማለታቸው ነው። “ብቻችንን መቆም ካለብን ያን እናደርጋለን፤ አስፈላጊ ከሆነ በጨበጣም ቢሆን እንዋጋለን” ሲሉ ዝተዋል፣ ናታንያሁ። ባይደን በበኩላቸው ራፋህ ላይ እስራኤል ወረራ ከፈጸመች የተወሰኑ ጦር መሣሪያዎችን…