Category: Uncategorized
-

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ “ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ስጋት” መሆኗን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረግ ድርድር እንደማይኖር እና ሶማሊያ ሉዓላዊነቷን ለድርድር እንደማታቀርብም ተናግረዋል።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼህ ሞሐመድ ይህንን ያሉት የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ ትናንት ረቡዕ ሚያዝያ 2/2016 ዓ.ም. ለአገሪቱ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር ነው። 24 ደቂቃ ገደማ የቆየው የፕሬዝዳንቱ ንግግር የአገር ውስጥ እና ቀጣናዊ ጉዳዮችን የዳሰሰ ነበር። የባሕር በር ለማገኘት ከሶማሊላንድ ጋር በተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት ምክንያት ከሶማሊያ ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባችው እና አምባሳደሯን እንድታስወጣ የተደረገችው የኢትዮጵያ ጉዳይም በፕሬዝዳንቱ…
-

በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ የሚገኘው የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ባልደረባ በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ ያላቸው በርካታ የህክምና መሳርያዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃ ገብረግዚአብሄር ለቢቢሲ ተናገሩ።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ውድ በሆኑ የሆስፒታሉ የህክምና መሳሪያዎች ላይ በሠራተኛው አማካይነት የተፈፀመው ድርጊት ያጋጠመው ቅዳሜ መጋቢት 21/2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ ነው። ከሰሞኑ አንድ ግለሰብ ፊቱ በካርቶን ተሸፍኖ የህክምና መሳሪያዎችን ሲያወድም የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጭ ሰንብቷል። የሆስፒታሉ ሠራተኛ በህክምና መሳሪያዎቹ ላይ ለምን ጉዳት እንዳደረሰ የታወቀ ነገር የሌለ ሲሆን፣ የፖሊስ የምርመራ ውጤት እየተጠበቀ ነው።…
-

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ በትውልድ ከተማቸው መቂ ውስጥ ተገድለው አስክሬናቸው ተገኘ።
ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈቀዱ የአቶ በቴ ኡርጌሳ የቅርብ ጓደኛ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አቶ በቴ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን በምትገኘው መቂ ከተማ የተገደሉት ትናንት ማክሰኞ ሚያዚያ 1/2016 ዓ.ም. እኩለ ሌሊት ላይ ነው። ፓርቲያቸው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ ኦፊሰሩን ግድያን በተመለከተ እስካሁን ያለው ነገር ባይኖርም የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ “በቴ…
-

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጋዛ አያያዝ ላይ “ስህተት” እየሠራ ነው ብለው እንደሚያምኑ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተናገሩ።
“እሱ የሚያደርገው ነገር ስህተት ነው ብዬ አስባለሁ። በእሱ አካሄድ አልስማማም” ሲሉ ባይደን ተናግረዋል። ጋዛ ለሚቀጥሉት ስድስት እና ስምንት ሳምንታት “ምግብ እና መድሃኒት ማግኘት አለባት” ብለዋል። አሜሪካ ለጦርነቱ ቀጣይነት ያላት ድጋፍ የሚወሰነው እስራኤል ተጨማሪ ምግብ እና መድኃኒት እንዲገባ በመፍቀዷ ላይ ነው ሲሉ ባለፈው ሳምንት አስጠንቅቀዋል። እስራኤል ወደ ጋዛ እርዳታ እንዳይገባም ሆነ እንዳይሰራጭ እንቅፋት ሆናለች መባሏን አስተባብላ…
-

የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጀርመን ለእስራኤል የምታደርገውን የጦር መሳሪያ ሽያጭ እንዲያስቆማት ኒካራጓ ጠየቀች።
ጀርመን የተባበሩት መንግሥታት የዘር ማጥፋትን ለመከላከል የተደረገውን ስምምነት በመጣስ መሳሪያ ለእስራኤል የጦር መሳሪያ በመሸጥ እንዲሁም ለተመድ የእርዳታ ኤጀንሲ ድጋፍ በመከልከልም ነው የተከሰሰችው። ክሱን ውድቅ ያደረገችው ጀርመን መከላከያዋን ለአለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት (አይሲጄ) ማክሰኞ ታቀርባለች። ባለፈው ዓመት 30 በመቶ የሚሆነው የእስራኤል የጦር መሳሪያ ከጀርመን የተሸመተ ሲሆን በአጠቃላይም 326 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደተደረገበትም ተገልጿል። እስራኤል ባለፈው…
-

በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ይዛ ከጂቡቲ ወደ የመን በማቅናት ላይ የነበረች ጀልባ ኤደን ባሕረ ሰላጤ ውስጥ ሰጥማ የ38 ሕይወት አለፈ።
አደጋው የደረሰው ትናንት ሰኞ መጋቢት 30/2016 ዓ.ም. ኢትዮጵያውያኑን አሳፍራ ከጅቡቲ ወደ የመን ስትጓዝ ነው ጀልባዋ የመስመጥ አደጋ ያጋጠማት። በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሰሜን ምሥራቅ ከሚገኘው የአገሪቱ ክፍል ተነስታ ጉዞዋን ወደ የመን አቅጣጫ አድርጋ የነበረችው ጅልባ 60 ኢትዮጵያውያንን አሳፍራ ነበር ብሏል። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት በአደጋው ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎችን ዜግነትን በተመለከተ ያለው ነገር ባይኖርም፤ ከሟቾቹ መካከል…
-

የአሜሪካው ሳውዝዌስት አየር መንገድ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ለበረራ እየተነሳ ሳለ የሞተሩ ሽፋን ከወደቀ በኋላ ምርመራ ተጀመረ።
ከቴክሳስ ሂዩስተን እየተነሳ የነበረው አውሮፕላን የሞተር ሽፋን ሲገነጠል የአውሮፕላኑን ክንፍ መትቷል። 135 መንገደኞችን እና 6 የአውሮፕላኑ ሠራተኞችን ይዞ የነበረው አውሮፕላን ተጨማሪ ችግር ሳይደርስበት ዴንቨር አየር ማረፊያ ማረፍ ችሏል። በዚህ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ላይ የተፈጠረው ክስተት ያጋጠመው ግዙፉ አውሮፕላን አምራች ቦይንግ ላይ የደኅንነት ጥያቄ እየተነሳበት ባለበት ወቅት ነው። ሳውዝዌስት አየር መንገድ ተገንጥሎ የወደቀው የሞተር መሸፈኛ በአየር…
-

በሰሜናዊ ሞዛምቢክ የመጓጓዣ አገልግሎት እየሰጠች የነበረች ጀልባ ሰጥማ አብዛኞቹ ሕጻናት የሆኑ ቢያንስ የ90 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
አደጋው ያጋጠመባት የናምፑላ ግዛት ኃላፊዎች በመርከቧ ተሳፍረው ከነበሩት 130 ሰዎች እስካሁን በሕይወት የተገኙ ሰዎች አምስት ናቸው ብለዋል። የናፑላ ግዛት ዋና ፀሐፊ ጄይሚ ኔቶ ተጓዦቹ አደጋው የገጠማቸው በአካባቢያቸው የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ ሲሸሹ ነው ብለዋል። ኔቶ “ጀልባዋ ከአቅሟ በላይ በመጫኗ እንዲሁም ሰዎችን ለማጓጓዝ የተሠራች ባለመሆኗ ሰጥማለች” ብለዋል። ቢቢሲ ማረጋገጥ ያልቻለው ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት የተጋራ ተንቀሳቃሽ ምስል…
-

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን በጋዛ ታግተው የሚገኙ ሰዎችን እንዲለቀቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ለመጠየቅ አደባባይ ወጡ።
ይህ ሰልፍ በእስራኤል መዲና ቴል አቪቭ እና በሌሎች ከተሞች የተደረው የአገሪቱ ጦር ኤልዳ ካትዚር የተባለ ታጋች አስክሬንን ማግኘቱን ተከትሎ ነው። አደባባይ የወጡ ሰዎች “አሁኑኑ ምርጫ ይካሄድ” እንዲሁም “ኤልዳ እናዝናለን” ሲሉ ደምጻቸውን አስተጋብተዋል። ፖሊስ በቴል አቪቭ ተሰባስበው የነበሩትን ተቃዋሚዎች በኃይል ለመበተን ተገዷል። ተቃዋሚዎቹ ሐማስ እና አጋሮቹ በጋዛ የያዟቸውን 130 ታጋቾች የእስራኤል መንግሥት ማስለቀቅ አለመቻሉ እንዳበሳጫቸው አስተያየት…
-

የሩሲያ ደጋፊ የሆኑት ፒተር ፔሌግሪኒ፤ ዙዛና ካፑቶቫን በመተካት አዲሱ የስሎቫኪያ ፕሬዝደንት ሆነው ተመረጡ።
48 ዓመቱ ፔልግሪኒ የምዕራባዊያን ደጋፊ የሆኑት ኢቫን ኮርኮክን 53 በመቶ በሆነ ድምፅ በመርታት ነው የስሎቫኪያ መሪ የሆኑት። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ለሩሲያ ጠንከር ያለ ድጋፍ እንዳላቸው ይነገራል። የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ፊኮም በተመሳሳይ የሩሲያ ደጋፊ ሲሆኑ የስሎቫኪያ ፓርላማ የሳቸውን ሐሳብ እንደሚያንፀባርቅ ይታመናል። ፓርላማው፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና አሁን ደግሞ የፕሬዝደንቱ ፅ/ቤት በሩሲያ ደጋፊ ፖለቲከኞች ተይዟል። ጠቅላይ…