Category: Uncategorized
-

ለሁለት ሳምንት ያህል ታግተው የነበሩ አምስት የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ተገድለው መገኘታቸውን የፋብሪካውን አንድ ኃላፊ ለቢቢሲ ገለጹ።
ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁት የስኳር ፋብሪካው ኃላፊ የአምስቱ ሠራተኞች አስከሬን ዛሬ ጠዋት መጋቢት 6/2016 ዓ.ም. መገኘቱን ገልጸዋል። አስከሬናቸው ከፋብሪካው ማሳ ወጣ ብሎ ጨካ በሚባል የገጠር አካባቢ ነው የተገኘው። ከተገደሉት መካከል ሦስቱ ሠራተኞች ከወንጂ አካባቢ ሲሆኑ፣ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም በዛሬው ዕለት መፈጸሙ ተገልጿል። ሌሎቹ ሁለቱ ሠራተኞች አንደኛው ከአዳማ የመጣው ቀብሩ ዛሬ የሚፈጸም ሲሆን፣ እንዲሁም ሌላኛው ከደሴ የመጣው…
-

የኢትዮጵያ መንግሥት የፍትህ ሚኒስቴር በእነ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው መዝገብ ቀርበው የነበሩ ክሶች ለሕዝብ ጥቅም ሲባል እንዲቋረጡ መወሰኑን አስታወቀ።
በተመሳሳይ በቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) መዝገብ የነበሩ ክሶች እንዲቋረጡ መደረጋቸውም ይፋ ተደርጓል። በቀድሞ ርዕሰ መስተዳደር ላይ ተመስርቶ የነበረው ክስ መቋረጡ ከተገለጸ በኋላ ከእስር መፈታታቸውን ጠበቃቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በአቶ አብዲ መሐመድ ኡመር የክስ መዝገብ በ1ኛ የሕገ-መንግሥትና የሽብር ወንጀል ጉዳዮች ችሎት የክርክር ሂደት ላይ መቆየቱ የሚታወስ ነው። በእነ ሜ/ጄኔራል ክንፈ…
-

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ከእስር መፈታታቸውን ጠበቃቸው ለቢቢሲ ተናገሩ።
ከስድስት ዓመት በፊት ነሐሴ 21/2010 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለው አስካሁን በእስር ላይ የቆዩት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር ከእስር የተለቀቁት ዐቃቤ ሕግ ክሱን በማንሳቱ መሆኑን ጠበቃቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ጠበቃ እና የሕግ አማካሪው እስክንድር ገዛኸኝ እንደተናገሩት የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክሳቸው ተነስቶ የተለቀቁት ዛሬ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም. መሆኑን አመልክተዋል። ከአቶ አብዲ በተጨማሪም በተመሳሳይ…
-

የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ራፋህ የሚገኘው የዕርዳታ ማዕከሉ ላይ ጥቃት እንዳደረሰበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።
በዚህም ጥቃት አንድ የማዕከሉ ሰራተኛ መገደሉን እንዲሁም 22 ሰዎች መቁሰላቸውን የተመድ የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ አክሎ አስታውቋል። በተመድ ተቋማት ላይ የሚደርሰው ጥቃት “ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ህግጋትን ግልጽ በሆነ መንገድ በጣሰ መልኩ” ተደጋጋሚ እየሆነ እንደመጣ የኤጀንሲው ኃላፊ ፊሊፕ ላዛራኒ ገልጸዋል። በሐማስ አስተዳደር ስር ያለው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በበኩሉ እስራኤል በማዕከሉ ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት አምስት ሰዎች ተገድለዋል…
-

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም.ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካይ የሆኑትን የአቶ ክርስቲያን ታደለ ያለመከሰስ መብት አነሳ።
የፍትህ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዴዮን ጢሞቲዎስ የአቶ ክርስቲያን ያለመከሰስ መብት መነሳት አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ ማቅረባቸው ተዘግቧል። “አቶ ክርስቲያን በአማራ ክልል ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር አብረው ሲሰሩ እንደነበር” የፌደራል ፖሊስ መርምሮ ለአቃቤ ሕግ መላኩንም ዶ/ር ጌዲዮን ገልጸዋል። አቶ ክርስቲያን ታደለ ፓርላማ የገቡት በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ምርጫ ክልል የአማራ ብሔራዊ…
-

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ሐሙስ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም. በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካይ የሆኑትን የአቶ ክርስቲያን ታደለ ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ ነው።
አቶ ክርስቲያን ታደለ ፓርላማ የገቡት በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ምርጫ ክልል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)ን ወክለው ተወዳድረው ነው። አቶ ክርስቲያን ፓርላማ ከገቡ በኋላ በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነዋል። ሆኖም በአማራ ክልል የተፈጠረውን የፀጥታ መደፍረስ ተከትሎ ባለፈው ሐምሌ ወር በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት ላላፉት ሰባት ወራት…
-

ሦስት የግብፅ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መነኮሳት በደቡብ አፍሪካ በሚገኝ ገዳም ውስጥ “ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ” መገደላቸው ተገለጸ።
አባ ታክላ ሙሳ፣ አባ ሚናህ አቫ ማርከስ እና አባ ዮስቶስ አቫ ማርከስ ትናንት ማክሰኞ መጋቢት 3/2016 ዓ.ም. መገደላቸውን የግብፅ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያ የደቡብ አፍሪካ አገረ ስብከት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ከሦስቱ መነኮሳት ግድያ ጋር በተያያዘ አንድ የግብፅ ዜግነት ያለው የቤተክስቲያኗ አባል በቁጥጥር ስር መዋሉም ተገልጿል። የመነኮሳቱ ግድያ በደቡብ አፍሪካ እና በመላው የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሯል። “ሐዘናችንን…
-

የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥለው ምርጫ ለመፎካከር የሚያስችላቸውን ድምፅ አገኙ።
የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ከ8 ወራት በኋላ ኅዳር 2017 ዓ.ም. ይካሄዳል። አራት ግዛቶች፣ አንድ የአሜሪካ ክፍል እና በመላው ዓለም የሚኖሩ ዴሞክራቶች ማክሰኞ ዕለት ዕጯቸውን መርጠዋል። ይህ ማለት በአውሮፓውያኑ 2020 የተመለከትነው የባይደን እና ትራምፕ ፍጥጫ በ8 ወራት ውስጥ ይደገማል። ሁለቱ ቁንጮ ፓርቲዎች በቅርቡ በየፊናቸው በሚያደርጉት ስብሰባ ዕጩዎቻቸውን በይፋዊ መንገድ ያስተዋውቃሉ። የ81 ዓመቱ ፕሬዝንት ማክሰኞ አመሻሹን በሰጡት ቃል…
-

ለሳምንታት የዘለቀውን ከፍተኛ ጫና እና በአገሪቱ እየጨመረ ያለውን የከፋ ነውጥ ተከትሎ የሄይቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሪየል ሄንሪ ከስልጣን ለመልቀቅ መስማማታቸውን የካሪቢያን አገራት ቡድን ሊቀ መንበር አስታወቁ።
የቀጣናው መሪዎች በሄይቲ የፖለቲካ ሽግግር ላይ ለመምከር ሰኞ ዕለት በጃማይካ መገናኘታቸውንም ተከትሎ ነው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ለመልቀቅ መስማማታቸው የተነገረው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሁኑ ወቅት በታጠቁ ቡድኖች ወደ አገራቸው እንዳይመለሱ በመከልከላቸው በፖርቶ ሪኮ ውስጥ ይገኛሉ። ከቀድሞው የሄይቲ ፕሬዚዳንት ግድያ፣ ከአውሮፓውያኑ 2021 ጀምሮም አገሪቱን ሲመሩ ቆይተዋል። በጃማይካ መዲና ኪንግስተን የተካሄደውንም ስብሰባ ተከትሎ የካሪቢያን አገራት ማህበረሰብ ሊቀመንበር እና የጋያና…
-

የካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ሊቀ-ጳጳስ ፍራንሲስ ዩክሬን “ነጭ ባንዲራ የማንሳት ድፍረት ሊኖራት ይገባል” ማለታቸውን ተከትሎ ኪዬቭ የቫቲካን ተወካይዋን ጠርታለች።
የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ሊቀ-ጳጳሱ በሰጡት አስተያየት ኪዬቭ “መከፋቷን” ለተወካዩ ኑንሲዮ ቮሎድሚር ኩልቦካስ ነግረናቸዋል ብሏል። በተያያዘ ዜና ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ዩክሬን ከሰሞኑ ከገጠማት ሽንፈት “አገግማ አሁን መረጋጋት ላይ ትገኛለች” ብለዋል። ነገር ግን የዩክሬን አጋሮች ለሀገሪቱ የሚያደርጉት እርዳታ “እጅጉን ቀንሷል።” ሊቀ-ጳጳስ ፍራንሲስ ከስዊትዘርላንዱ አርኤስአይ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ በፅሑፍ ከወጣ በኋላ ነው ጉዳዩ ዩክሬንን ያስቆጣው። ሮይተርስ የዜና…