Category: Uncategorized
-

የጋና ፓርላማ ከተመሳሳይ ፆታ ግንኙነቶች እና በዚህ ዙሪያ ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ በሚከሰሱ ሰዎች ላይ ጠንከር ባለ እስር የሚቀጣ ሕግ አጸደቀ።
አዲሱ ሕግ በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ውስጥ መሆናቸውን የሚገልጹ እንዲሁም ሆነው የተገኙ ሰዎችን እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ እስር፣ ቡድኖችን የሚያቋቁሙ እና በገንዘብ የሚደግፉ እስከ አምስት ዓመት እስር እንዲቀጡ ያደርጋል። የአገሪቱ ሕግ አውጪዎች የእስር ቅጣቱ ወደ ማኅበረሰብ አገልግሎት እና የምክር ድጋፍ እንዲቀየር የተደረገውን ጥረት ተቃውመው ውድቅ አድርገውታል። በአገሪቱ ሁለት ዋነኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተደገፈው እና ፓርላማው ያጸደቀው ይህ…
-

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጋምቤላ ክልል ካለፈው ዓመት ጀምሮ በተለያዩ ወረዳዎች በተነሱ ግጭቶች ስደተኞችን ጨምሮ 138 ሠዎች መገደላቸውን ገለጸ።
ኮሚሽኑ ከመስከረም 20 እስከ መስከረም 30/ 2016 ዓ.ም ድረስ አከናውኘዋለሁ ባለው ምርመራ ግጭቶቹ በኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ በጋምቤላና ጉግ ወረዳዎች እንዲሁም በክልሉ ዋና ከተማ ጋምቤላ ተከስተዋል ብሏል። ለምርመራው 93 ሠዎችን ማነጋገሩን የገለጸው ኮሚሽኑ፤ 113 ሠዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱንም አሳውቋል። ግንቦት 2015 ዓ.ም ለእንጨት ለቀማ ወጥቶ በጠፋ ሠው ምክንያት በፒኝዋ እና ሌር ቀበሌ ነዋሪዎች…
-

በሶማሊያ አየር ክልል ውስጥ ሲበሩ የነበሩት የኢትዮጵያ እና የኳታር አየር መንገድ አውሮፕላኖች በሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስህተት ምክንያት ሊጋጩ ተቃርበው ነበር በተባለው ክስተት ዙሪያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምላሽ ሰጠ።
ቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ ሲጓዝ የነበረው የበረራ ቁጥር 602 አውሮፕላኑ በነበረበት ከፍታ ላይ የኳታር አውሮፕላን እየቀረበው እንደነበር መረጃ እንደተቀበለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቢቢሲ ሶማሊ በሰጠው ምላሽ ገልጿል። ክስተቱን በተመለከተ ለተጨማሪ ምርመራ እንዲሁም የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ለኢትዮጵያ እንዲሁም ለሶማሊያ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣናት ሪፖርት መደረጉንም አየር መንገዱ አመልክቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሶማሊላንድ አቪዬሽን…
-

እስራኤል በጋዛ ላይ እያካሄደችው ባለው ወታደራዊ ዘመቻ ምክንያት የአሕመድ አል-ጉፈሪ ቤተሰቦች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አልቀዋል።
በጋዛ ከተማ በቤተሰቦቹ ላይ በተፈጸመ ጥቃት 103 ዘመዶቹ ተገድለዋል። እሱ የተረፈው 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በዌስት ባንኳ ኢያሪኮ ከተማ ስለነበረ ነው። መስከረም 26 ሐማስ ወደ እስራኤል ድንበር ዘልቆ ጥቃት ሲፈጸም አሕመድ ቴል አቪቭ ውስጥ በግንባታ ሥራ ላይ ነበር። ጥቃቱን ተከከትሎ ጦርነት ተከፈተ። በእስራኤል ጦርም እገዳ ተጣለ። ይህም ወደ ሚስቱ እና ሦስት ሴት ልጆቹ…
-

ቡርኪና ፋሶ ውስጥ በአንድ መስጂድ እና ቤተክርስቲያን ላይ በተመሳሳይ ቀን በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸው የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።
ናቲያቦአኒ በተባለችው ከተማ ውስጥ ለፀሎት መስጂድ ውስጥ በማለዳ የተሰበሰቡ ሰዎችን በመክበብ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች ገድለዋል። አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ እንደተናገሩት “የጥቃቱ ሰለባዎች አብዛኞቹ ወንዶች ሲሆኑ ሁሉም ሙስሊሞች ናቸው” ብሏል። ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ቡርኪና ፋሶ ካላት ግዛት ውስጥ ከአንድ ሦስተኛ የሚልቀው በእስላማዊ አማጺያን ቁጥጥር ሥር የሚገኝ ነው። ጥቃት ፈጻሚዎቹ…
-

ለ68 ህጻናት ሞት ምክንያት ነው ከተባለው የተመረዘ የሳል ሽሮፕ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 23 ሰዎች ኡዝቤክስታን ውስጥ ተፈረደባቸው።
ከመድኃኒቱ ጋር በተያያዘ ተከሰው ፍርድ ቤት የቀረቡት ግለሰቦች ታክስ በማጭበርበር፣ ደረጃውን ያልጠበቀ ወይም ሐሰተኛ መድኃኒት በመሸጥ፣ ኃላፊነትን አላግባብ በመጠቀም፣ በግድየለሽነት፣ ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም እና ጉቦ በመቀበል ጥፋተኛ ተብለዋል። ለእነዚህ ጥፋቶችም የኡዝቤክስታን ፍርድ ቤት በተከሳሾቹ ላይ ከሁለት አስከ 20 ዓመት የሚደርስ እስር ፈርዶባቸዋል። በዋና ከተማዋ ታሽኬንት ባለ ፍርድ ቤት ጉዳዩ በተሰማበት ጊዜ በመርዛመው ሽሮፕ የሞቱት ህጻናት…
-

ካለፈው ሳምንት መገባደጃ አንስቶ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ማገርሸቱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
በጎጃም፣ በሰሜን ሸዋ፣ሰሜን ወሎ እና ጎንደር አካባቢዎች በሚገኙ በርካታ ስፍራዎች ጠንከር ያሉ ግጭቶች እየተካሄዱ ነው ያሉ ነዋሪዎች መንገዶችም መዘጋታቸውን ገልጸዋል። ከሳምንቱ መገባደጃ ቀናት አንስቶ በመርዓዊ፣ ደቡብ ሜጫ፣ ቋሪት፣ ሰከላ፣ ደጋ ዳሞት፣ አንጾኪያ ገምዛ ወረዳ፣ ሸዋ ሮቢት አካባቢ፣ ላሊበላ ዙሪያ ባሉ ቀበሌዎች ከባድ ውጊያዎች እየተካሄዱ መሆናቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከደብረ ብርሃን ወደ ደሴ የሚወስደው መንገድ ከቅዳሜ፣…
-

ሁለት ዓመት ባስቆጠረው የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በአጠቃላይ 31 ሺህ ወታደሮች እንደተገደሉባት የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚይር ዘለንስኪ አስታወቁ።
ፕሬዚዳንቱ የሟቾችን አኃዝ ቢያስታውቁም በቀጣዩ ሩሲያ ለምታደርገው ወታደራዊ ዕቅድ ሊጠቅም ይችላል በሚል የቆሰሉትን ወታደሮች ቁጥር ይፋ አላደርግም ብለዋል። በዩክሬን ባለስልጣናት ዘንድ የሟቾችን ቁጥር ይፋ ማድረግ ያልተለመደ ሲሆን ሌሎች አካላት የሚሰጧቸው ግምቶች ከዚህ በጣም ከፍ ያሉ ናቸው። የዩክሬን መከላከያ ሚኒስትር ምዕራባውያን ለአገራቸው የሚሰጡት ዕርዳታ በመዘግየቱ ህይወት እና ግዛት እያስከፈሉ ነው ካሉ በኋላም ነው ዩክሬን የሟቾችን ቁጥር…
-

የአሜሪካ የአየር ኃይል አባል የሆነ ግለሰብ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ፊት ለፊት ራሱን በእሳት ማቃጠሉን የአሜሪካ የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት አስታወቀ።
ክስተቱ የተከሰተው እሑድ እኩለ ቀን ላይ መሆኑ ተነግሯል። ግለሰቡ ሲቃጠል “ፍልስጤም ነፃ ትውጣ” እያለ ሲጮህ የሚያሳይ ነው የተባለ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ መውጣቱን የአሜሪካ ሚዲያዎች ዘግበዋል። የአሜሪካ የደህንነት አገልግሎት መኮንኖች ከግለሰቡ ላይ እሳቱን ማጥፋታቸው ታውቋል። ግለሰቡ ከባድ እና ለሕይወት አስጊ የሆኑ ጉዳቶች አጋጥመውት ወደ ሆስፒታል መወሰዱን የከተማው የእሳት አደጋ መከላከያ ዘግቧል። የዩናይትድ ስቴትስ አየር ኃይል ቃል…
-

የአሜሪካ እና የዩናይትድ ኪንግደም ተዋጊ አውሮፕላኖች በየመን ውስጥ በሚገኙ 18 የሁቲ ይዞታዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር ፔንታገን አስታወቀ።
ሁለቱ አገራት በጋራ ተመሳሳይ ጥቃት ሲፈጽሙ ይህ ለአራተኛ ጊዜ ሲሆን፣ ኢላማ ያደረጉትም የሁቲ መጋዘኖችን፣ የድሮን እና የአየር ጥቃት መከላከያ መዋቅሮችን እንዲሁም ታጣቂዎቹ የሚንቀሳቀሱበትን ሄሊኮፕተር መሆኑን አሜሪካ አሳውቃለች። ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በበኩሏ የምዕራባውያን አገራቱ እርምጃውን የወሰዱት የሁቲ ታጣቂዎችን ጥቃት የፈጸም አቅምን “የበለጠ ለማዳከም” ነው ብላለች። በኢራን የሚደገፉት ሁቲዎች ለባሕር ንግድ እንቅስቃሴ ወሳኝ በሆነው በቀይ ባሕር በሚንቀሳቀሱ…