Category: Uncategorized
-

እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ በፈጸመችው ጥቃት ከተገደለች ፍልስጤማዊት እናት ማህጸን በሕይወት መውጣት ችላ የነበረችው ጨቅላ ከቀናት በኋላ አረፈች።
ሳብሪን አል ሳካኒን ከሙት እናቷ ማህጸን እንድትወጣ ተደርጎ የነበረው በቀዶ ህክምና ነበር። የህክምና ባለሙያዎች እጃቸውን በመጠቀም አየር ወደ ሳንባዋ እንዲገባ ለማድረግ እና እንድትነቃም ለማድረግ ሞክረው ነበር። ጨቅላዋ በሕይወት ከወጣች ከቀናት በኋላ ዛሬ ሚያዝያ 18/ 2016 ዓ.ም. ሕይወቷ አልፏል። በሙት እናቷ ስም ተሰይማ የነበረችው ሳብሪና ከእናቷ አጠገብ ተቀብራለች። ህጻን ሳብሪና ባለፈው ሳምንት ማገባደጃ ላይ ራፋህ ላይ…
-

በታንዛንያ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት የ155 ሰዎች ህይወት መቀጠፉን የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቁ።
በዚህ ከባድ ዝናብ ምክንያት 200 ሺህ ሰዎች እና ከ51 ሺህ በላይ አባወራዎች የከፋ ችግር ላይ መውደቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። ታንዛንያን ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ አገራት መነሻው ከፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ በሆነው እና በአካባቢ በሚፈጠር የውኃ ሙቀት መጨመር በሚከሰተው ኤልኒኖ የአየር ክስተት ምክንያት በከፋ ዝናብ ተመትተዋል። በዚህም ምክንያት ታንዛንያን ጨምሮ ጎረቤቶቿ ቡሩንዲ እና ኬንያ ሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ ገብተዋል።…
-

ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት በመሞከር የተጠረጠሩት ቀሲስ በላይ መኮንን፤ ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ የተገኙት “ሰዎች አታልለዋቸው” እንደሆነ ለፍርድ ቤት መግለጻቸውን ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለቢቢሲ ተናገሩ።
በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የኦሮሚያ ቤተ ክህነትን ለመመሥረት በነበራቸው እንቅስቃሴ የሚታወቁት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን፤ ይህንን የተናገሩት ዛሬ ረቡዕ ሚያዝያ 16/2016 ዓ.ም. በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ነው። የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ዛሬ ረፋድ አራት ሰዓት የተሰየመው፤ ባለፈው ሳምንት…
-

በኬንያ መዲና ናይሮቢ በተከሰተ ከባድ ጎርፍ መንገዶች በውሃ ተጥለቅልቀው የታዩ ሲሆን የሀገሪቱ ባለስልጣን የጎርፉ መጠን “እጅግ በከፋ ደረጃ እየጨመረ ነው” ብለዋል።
ባለፉት ቀናት በኬንያ የጣለው ከፍተኛ ዝናብ መጠነ ሰፊ ውድመት እያስከተለ ነው። የመንግስታቱ ድርጅት ቢያንስ 32 ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ እና ከ40 ሺህ የሚበልጡት ደግሞ በዝናቡ እና ባስከተለው ጎርፍ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለመሸሽ መገደዳቸውን ገልጿል። በኬንያ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት የናይሮቢ ተወካይ የሆኑት ኤዲን ሲፉና ባጋሩት ቪዲዮ በጎርፍ የተጥለቀለቀ ሰፈርን አስመልክተዋል። በቪዲዮው ላይ መውጫ ያጡ ነዋሪዎች የቤታቸው…
-

በጋዛ ናስር እና አል-ሺፋ ሆስፒታሎች ላይ የደረሰው ውድመት እና ከእስራኤል ወረራ በኋላ በሆስፒታሎቹ “የጅምላ መቃብሮች” መገኘታቸው “አሰቃቂ” ነው ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኃላፊ ገለጹ።
ቮልከር ቱርክ በሟቾች ዙሪያ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግም ጠይቋል። የፍልስጤም ባለስልጣናት በናስር ሆስፒታል በጅምላ የተቀበሩ ወደ 300 የሚጠጉ ሰዎችን አስከሬን ማውጣታቸውን ተናግረዋል። ሰዎቹ እንዴት እንደሞቱ እና መቼ እንደተቀበሩ ግን ግልጽ አይደለም። የእስራኤል ጦር አስከሬኖቹን ቀብሯል መባሉን “መሰረተ ቢስ” ሲል አጣጥሎታል። ጦሩ በዃን ዮኒስ ከተማ በሚገኘው ሆስፒታል ለሁለት ሳምንታት በቆየ ዘመቻ ወቅት ታጋቾች ሊኖሩ እንደሚችሉ በመጠርጠሩ በፍልስጤማውያን…
-

በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ጠሮ መስጂድ በተባለ አካባቢ ለቤት ግንባታ የተከመረ ድንጋይ እና አፈር ተንዶ የሰባት ሠዎች ሕይወት አለፈ።
ረቡዕ ሚያዝያ 16/2016 ዓ.ም. ከሌሊት 11 ሰዓት ላይ የአደጋ ጥሪው እንደደረሰው ለቢቢሲ የተናገረው የአዲስ አበባ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን፤ ድንጋይ እና አፈሩ ተደርምሶ አደጋው ሦስት ክፍል ያለው ቤት ላይ መድረሱን አስታውቋል። የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ የኮሚሽኑ ባለሞያዎች ወደ ስፍራው “በፍጥነት” ቢደርሱም ሕይወት ለማዳን ያደረጉት ጥረት ግን አልተሳካም ብለዋል። “እተገነባ…
-

ግጭት ከተነሳባቸው የአላማጣ ከተማ፣ ዛታ እና ኦፍላ የራያ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ተፈናቃዮቹ የተጠለሉባቸውን የዞን ባለሥልጣናት ዋቢ አድርጎ ጽህፈት ቤቱ ሰኞ ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርት መሠረት ከተፈናቃዮቹ መካከል 42 ሺህ የሚሆኑ በሰሜን ወሎ በምትገኘው ቆቦ ከተማ እንዲሁም 8300 የሚሆኑት ደግሞ በሰቆጣ እና ዋግ ኽምራ ዞኖች ተጠልለዋል ብሏል። በአብዛኛው ሴቶች፣ ህጻናት፣ ታዳጊዎች እና አረጋውያንን ያሉበት ተፈናቃዮች በማኅበረሰቡ ባሉ ቤቶች ለመጠለል እየሞከሩ እንደሆነ ገልጾ፣ ሌሎች ደግሞ ከቆቦ ከተማ…
-

ሁለት የማሌዥያ አየር ኃይል ሄሊኮፕተሮች ለወታደራዊ ትዕይንት በልምምድ ላይ እያሉ መጋጨታቸውን ተከትሎ አስር ሰዎች ሞቱ።
በሄሊኮፕተሮቹ ውስጥ የነበሩት አስሩም ሰራተኞች ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል። አንደኛው ሄሊኮፕተር የሌላኛውን ሄሊኮፕተር የአናቱን ተሽከርካሪ ክፍል መምታቱን ተከትሎ በተፈጠረው ግጭትም ሁለቱም መሬት ላይ መውደቃቸውን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ያወጣው ቪዲዮ አሳይቷል። አደጋው የተፈጠረው የማሌዥያ የአየር ኃይል የጦር ሰፈር በሆነችው ሉሙት በተሰኘችው ከተማ በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 3፡30 ገደማ ነው። “በሄሊኮፕተሮቹ ውስጥ የነበሩ ሁሉም ሰዎች በስፍራው መሞታቸው…
-

የእስራኤል ወታደራዊ ደኅንነት ኃላፊ ሐማስ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. የፈጸመውን ጥቃት ቀድመው ባለማስቆማቸው ኃላፊነቱን ወስደው ከሥልጣናቸው ለቀቁ።
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት የባለሥልጣኑን ተተኪ ከተመረጠ በኋላ ሜጀር ጄኔራል አሮን ሃሊቫ ጡረታ እንደሚወጡ አስታውቋል። የወታደራዊ ደኅንነት ኃላፊው “የተሰጠንን አደራ በአግባቡ አልተወጣንም” ሲሉ በሥራ መልቀቂያ ደብዳቤያቸው አምነዋል። ሜጀር ጄኔራል አሮን ሃሊቫ በእስራኤል ታሪክ እጅግ አስከፊ በተባለው የሐማስ ጥቃት ምክንያት ከሥልጣን የለቀቁ የመጀመሪያው ከፍተኛ ባለሥልጣን ናቸው። Head of Israel’s Military Security, Hamas, September 26/2016. They took responsibility…
-

መስከረም 2016 ዓ.ም. ላይ በማይገመት ቦታ፣ ጨርሶ ሊገመቱ በማይችሉ ሁለት መሪዎች መካከል ስብሰባ ተደረገ።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቭሎድሚር ዜሌንስኪ ከሱዳኑ መሪ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ጋር በአየርላንድ በሚገኝ አየር ማረፊያ መገናኘታቸው ብዙዎችን አስደንቆ ነበር። ይህን የሁለቱን መሪዎች ውይይት በዩክሬን ጦር ውስጥ ያሉ የልዩ ኃይል አባላት እንዳመቻቹት ተገልጿል። ዜሌንስኪ በኒው ዮርክ የመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተሳትፈው ወደ ዩክሬን እየተመለሱ ሳለ አውሮፕላናቸው በአየርላንድ ሻነን አየር ማረፊያ ነዳጅ ለመሙላት በቆመበት ወቅት ነበር…