Category: Uncategorized
-

የእስራኤል ጦር ኃይል ለሁለት ሳምንታት ያህል በጋዛው አል-ሺፋ ሆስፒታል ላይ ወረራ ካካሄደ በኋላ አብዛኛውን የህክምና ተቋሙን ክፍል ለቆ መውጣቱ ተገለጸ።
በሆስፒታሉ ላይ ከተካሄደው ወረራ እና ጥቃት በኋላ የጋዛው ሆስፒታል ሕንፃ አፅሙ ቀርቶ ታይቷል። የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት እንደገለጸው ወታደሮቹ በመቶዎች የሚቆጠሩ “ሽብርተኞችን” ገድለዋል እንዲሁም በቁጥጥር ሥር አውለዋል። ሠራዊቱ “በሆስፒታሉ ዙሪያ” የጦር መሣሪያዎች እና የደኅንነት መረጃዎች ማግኘቱን ገልጧል። በሐማስ የሚመራው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር በርካታ ሬሳዎችን ጥሎ ለመሄድ መገገዱን አሳውቋል። የአካባቢው ሰዎች ደግሞ ሥፍራው መውደሙን ይናገራሉ። የእስራኤል ጦር፤…
-

በደቡባዊ ሊባኖስ በተፈጸመ ጥቃት ለሥራ የተንቀሳቀሱ ሦስት የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኞች እና አስተርጓሚያቸው ጉዳት ደረሰባቸው።
የሊባኖስ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኞች ጉዳት የደረሰባቸው የእስራኤል የድሮን ጥቃት በፈጠረው ፍንዳታ ነው ሲል ዘግቧል። እስራኤል ግን ጥቃቱን እኔ አልፈጸምኩም ብላለች። የተባበሩት መንግሥት ጉዳት የደረሰባቸው ሠራተኞቹ የሕክምና እርዳታ እያገኙ መሆኑን እና የፍንዳታውን ምንጭ እያጣራ መሆኑን ገልጿል። ፍንዳታው ያጋጠመው የተመድ ሠራተኞች በእስራኤል እና ሊባኖስ ድንበር ላይ በእግር እየተጓዙ የቅኝት ስራ እየሰሩ በነበሩበት ወቅት መሆኑ…
-

የጆ ባይደን የምርጫ ቅስቀሳ ቡደን ዶናልድ ትራምፕ በማሕበራዊ ሚድያ ገፃቸው የለጠፉትን ቪድዮ ተከትሎ ትችት እየሰነዘሩ ነው።
ትራምፕ ያጋሩት ቪድዮ ፕሬዝደንት ባይደን እጅና እግራቸው ተጠፍሮ የጭነት መኪና ላይ ተጭነው ያሳያል። ትራምፕ ከመጪው ኅዳር ምርጫ በፊት “በተደጋጋሚ ፖለቲካዊ አመፅ ለማስነሳት እየሞከሩ ነው” የሚል ትችት ደርሶባቸዋል። የትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ቡደን ቃል አቀባይ በበኩላቸው ዲሞክራቶች ትራምፕ ላይ “አመፅ ሲጠሩ ነው የቆዩት” ብለዋል። ትራምፕ አርብ ዕለት ነው ቪድዮውን ትሩዝ በተሰኘው ማሕበራዊ ሚደያቸው ላይ የለጠፉት። ከቪድዮው ጋር…
-

ከለንደን የሚተላለፈው የኢራን ቴሌቪዢን አቅራቢ ለንደን ከሚገኘው ቤቱ ውጪ በተደጋጋሚ በስለት መወጋቱን ጣቢያው አስታወቀ። ከአንድ ዓመት በፊት በኢራን ውስጥ የተቀሰቀሰውን ፀረ መንግሥት ተቃውሞ በስፋት ሲዘግብ የነበረው ‘ኢራን ኢንተርናሽናል’ የተባለው ቴሌቪዢን አቅራቢ ፑሪያ ዜራቲ ጥቃቱ የተፈጸመበት በቡድን ነው ተብሏል። የለንደን ፖሊስ የፀረ ሽብርተኝነት መኮንኖች ቡድን በቴሌቪዥን አቅራቢው ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ምርመራ እየመራው መሆኑ ተገልጿል። ጥቃቱ የተፈጸመበት…
-

በደቡብ አፍሪካ ለፋሲካ በዓል መንገደኞችን ከጎረቤት አገር ቦትስዋና አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ ተገልብጦ የ45 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት ከድልድልይ ላይ ወደ 50 ሜትር ገደል በወደቀው አውቶብስ ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች የ8 ዓመት ሴት ልጅ ብቻ በሕይወት መገኘቷን አስታውቀዋል። ከሞት የተረፈችው ብቸኛዋ የስምንት ዓመት ልጅ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባትም ተገልጿል። በሰሜን ምሥራቅ ሊምፖፖ ግዛት አደጋው የደረሰበት አውቶብስ የድልድዩን መከላከያ ጥሶ ቁልቁል ወርዶ ከመሬት ጋር ሲጋጭ በእሳት መያያዙ ተነግሯል። ተሳፋሪዎቹ ከቦትስዋና ዋና ከተማ ጋቦሮኔ…
-

የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ፍርድ ቤት እስራኤል ሊከሰት የሚችለውን ረሃብ ለማስወገድ ምግብ እና መድሃኒት ጋዛ እንዲገባ እንድትፈቅድ አዘዘ።
የተመድ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እስራኤል “በአስቸኳይ የሚፈለጉ አገልግሎቶች እና ሰብዓዊ እርዳታዎች” እንዲገቡ “ያለመዘግየት” መፍቀድ አለባት ሲል ወስኗል። የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የተሰማው በሳምንታት ውስጥ ጋዛ በረሃብ ልትመታ ትችላለች የሚል ማስጠንቀቂያ ከወጣ በኋላ ነው። የተመድ ፍርድ ቤት ውሳኔዎች በሕግ አሳሪ ቢሆኑም ፍርድ ቤቱ ግን የሚያስተላልፈውን ትዕዛዝ ተፈጻሚ የማድረግ አቅም የለውም። እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች እስራኤል ሆነ ብላ…
-

የአማራ ክልል መንግሥት ከቀናት በፊት በክልሉ የመማሪያ መጽሐፍት ላይ ያለውን ካርታ በተመለከተ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለወጣው ማስጠንቀቂያ ምላሽ ሰጠ።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ሰኞ መጋቢት 16/2016 ዓ.ም. ሁለቱ ክልሎች በይገባኛል የሚወዛገቡባቸው አካባቢዎችን ወደ አማራ ክልል ያካተተ ካርታ በመማሪያ መጽሐፍት ላይ መታተሙን በተመለከተ መግለጫ አውጥቶ ነበር። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ በዚህ መግለጫው የአማራ ክልል በመማሪያ መጽሐፍት ላይ ያውጣው ካርታ በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ ማስጠንቀቁ ይታወሳል። የአማራ ክልል በበኩሉ ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 19/2016 ዓ.ም.…
-

በአዲስ አበባ በፒያሳ እና አካባቢው ከሳምንታት በፊት በተጀመረው ግንባታ ምክንያት ወደ 11 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መነሳታቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ ይህንን ያሉት በመንግስት መገናኛ ብዙኃን ትናንት ረቡዕ መጋቢት 18/2016 ዓ.ም ምሽት ላይ በተላለፈ ውይይት ላይ ነው። በዚህ ውይይት ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ሲያቀርቡ የታዩት ከንቲባዋ “በድምሩ ወደ 11 ሺህ ሰው ይሆናል ከዛ አካባቢ [ከፒያሳ] ወደተሻለ ቦታ የወሰድነው” ብለዋል። ነዋሪዎቹ ራስ መኮንን ድልድይ፣ ማህሙድ ሙዚቃ ቤት፣ አዲሱ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ፣ አራት ኪሎ የሚገኘው…
-

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ እና ምሥራቅ አርሲ ዞኖች ታጣቂዎች በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀሳውስት እና ምዕመናን ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና የቤተክርስቲያኗ ምንጭ ገለጹ።
በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በዶዶላ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው ሰኞ መጋቢት 16/2016 ዓ.ም. ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን የቤተክርስቲያኗ ምንጮች ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪም ባለፈው እሁድ መጋቢት 15/2016 ዓ.ም. አንድ የ80 ዓመት ሴት አዛውንት እና ሌላ ወጣት ምሥራቅ አርሲ ውስጥ በአስቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን በደኅንነት ስጋት ምክንያት ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አባት ለቢቢሲ ተናግረዋል።…
-

የኢትዮጵያ እና የኤምሬትስ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ባለፈው እሁድ በሶማሊያ የአየር ክልል ላይ ከመጋጨት ለጥቂት መትረፋቸው ተገለጸ።
ነጻ አገርነቷን ያወጀችው የሶማሊላንድ ሲቪል አቪዬሽን እና ኤርፖርቶች ባለሥልጣን ሁለቱ አውሮፕላኖች አየር ላይ ሊጋጩ ተቃርበው የነበረው በሶማሊያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አሻሚ እና የተሳሳተ ትዕዛዝ ነው ብሏል። እንደ ባለሥልጣኑ መግለጫ እሁድ መጋቢት 15/2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ በሶማሊያ የአየር ክልል ውስጥ ሲበሩ የነበሩት አውሮፕላኖች ሳይጋጩ የቀሩት የሶማሊላንድ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎች በወሰዱት “ፈጣን…