Category: Uncategorized
-

በእስራኤል መንግሥት ውስጥ ያለውን ጥልቅ ክፍፍል በግልጽ ያሳያል በተባለ ውሳኔ የአገሪቱ የጦር ካቢኔ ሚኒስትር ቤኒ ጋንትዝ የአስቸኳይ ጊዜ መንግስቱን ለቀቁ።
የሚንስትሩ ውሳኔ ከጋዛ ጦርንት በኋላ ባለው ዕቅድ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር የተፈጠረው ልዩነት ማሳያ ተደርጓል። ጋንትዝ እሑድ ዕለት በቴል አቪቭ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ሲያሳውቁ ውሳኔውን “ቀልል አልነበረም” ብለዋል። “እንደ አለመታደል ሆኖ ኔታንያሁ ወደ እውነተኛው ድል እንዳንቀርብ እየከለከለን ነው። ይህም ለቀጠለው ቀውስ ማሳያ ነው” ብለዋል። በአንዳንዶች የእስራኤል ቀጣዩ ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን…
-

የተባበሩት መንግሥታት በየመን በሁቲ አማጺያን የተያዙ 11 ሠራተኞቹ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠየቀ።
ሠራተኞቹ የጦርነት ቀጠና ከሆነችው የመን የተቀናጀ በሚመስል ሁኔታ ከተለያዩ አካባቢዎች መወሰዳቸውንም ድርጅቱ ገልጿል። የተባበሩት መንግሥታት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች እንዳሉት ድርጅቱ የሠራተኞቹን ደኅንነት ለማረጋገጥ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ለማድረግ የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው። ታጣቂው ቡድን ራሱን በኢራን የሚመራው የአማጺ ክንፍ አድርጎ የሚመለከት ሲሆን እስራኤልን ፣ አሜሪካን እና ምዕራባውያንን በመቃወም በጋዛ ለፍልስጤማውያን ድጋፍ እንደሚያደረግ…
-

አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ፣ የቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ ፈይሳ እና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ታዋቂ የሆነችው ፍላጎት አብርሃምን ጨምሮ 20 ግለሰቦች “ገንዘብ ለሽብር ቡድን ሎጂስቲክ መግዣ ለማዋል” እንዲሁም “ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን በትጥቅ ትግል ለመቀየር” በመንቀሳቀስ ተጠርጥረው ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት፤ በተጠርጣሪዎቹ ላይ 13 የምርመራ ቀናት እንደፈቀደ ጠበቃ አያሌው ቢታኔ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከ10 እስከ 70 ቀናት በእስር ላይ የቆዩት ተጠርጣሪዎቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት ትናንት ረቡዕ ግንቦት 28/2016 ዓ.ም. ከሰዓት እንደሆነ ጠበቃው አስረድተዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኘው ሦስተኛ ፖሊስ…
-

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ያለመ አዲስ እና መጠነ ሰፊ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ዛሬ ማክሰኞ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
አዲሱ የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት በየዕለቱ ከሚመለከቱት በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ የጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በላይ አመልካቾች ከቀረቡ ጥያቄያቸውን ሳይመለከቱ በቀጥታ ከአገር እንዲባረሩ ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን ይሰጣል ተብሏል። ይህም ድንበር ላይ ያሉ ባለሥልጣናት ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥርን እንዲገድቡ እንደሚያስችላቸው ሦስት ስማቸው ያልተጠቀሰ ምንጮች በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ለሆነው ሲቢኤስ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ባይደን በሥልጣን ላይ በቆዩባቸው…
-

ቻይና ሰው አልባ መንኮራኩሯ በተሳካ ሁኔታ ማንም ሞክሮ በማያውቀው የጨረቃ ክፍል ማረፍ መቻሉን ገለጸች።
ቻንግ 6 የተበለው መንኮራኩር እሑድ ጥዋት በደቡብ ዋልታ-አይትከን ማረፉን የቻይና ብሔራዊ የጠፈር አስተዳደር (ሲኤንኤ) አስታውቋል። የዛሬ ወር ገደማ ጉዞ የጀመረው መንኮራኩር ዓለማው በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ውድ ድንጋይ እና አፈርን ለመሰብሰብ ያለመ ነው ተብሏል። በዚህም በደቡብ ዋልታ ላይ ካለው ግዙፍ ጉድጓድ ውስጥ የተወሰኑትን የጨረቃን ጥንታዊ አለቶች ማውጣት ይችላል። የግንኙነት መስመር መቆራረጥ ያለበት ቦታ በመሆኑ መንኮራኩሩ ከመሬት…
-

የሚኒስትሮች ምክር ቤት “ከሕጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ” ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ቡድኖች መልሰው እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ለመመዝገብ የሚያስችላቸውን ድንጋጌ የያዘ የአዋጅ ማሻሻያን ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ።
በሥራ ላይ ባለው “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ” ላይ የተደረገው ይህ ማሻሻያ፤ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የተሰረዘበትን የፓርቲነት ሕጋዊ እውቅና መልሶ እንዳያገኝ ያደረገውን የሕግ ጥያቄ የሚመልስ ነው። የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአዋጅ ማሻሻያውን ተቀብሎ ወደ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመራው ዛሬ አርብ ግንቦት 23/2016 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር…
-

በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ በ‘ሎውረንስ ቴክኖሎጂካል ዩኒቨርስቲ’ የሚያዘጋጀውን የሮቦቲክስ ውድድር ያሸነፉ ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች የተለያዩ ሽልማቶችን አግኝተው ተመልሰዋል።
ታዳጊዎቹ ላለፉት ሁለት ዓመታት በአቦጊዳ ሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ማዕከል ውስጥ ሥልጠና ሲወስዱ እና የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ሲያቀርቡ የቆዩ። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ናቸው። እነዚህ ለውድድር የቀረቡ ተማሪዎች ከ12ኛ ክፍል በታች የሆኑ ኢትዮጵያውን ታዳጊዎች፣ በአምስት የተለያዩ መስኮች አገራቸውን መወከል ችለዋል። አሸናፊዎቹ በዩኒቨርስቲው መማር የሚያስችላቸውን ዕድል ያገኙ ሲሆን፣ በተጨማሪም ሜዳልያ እና ዋንጫም እንደተሸለሙ የአቦጊዳ ሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ዋና መሥራች ምህረት…
-

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አንዳንድ የአገሪቱ ግዛቶች በጫት ሽያጭ መጠቀም ላይ ያጣሉትን አወዛጋቢ ዕገዳ ውድቅ በማድረግ ምርቱ እንዲስፋፋ እንደሚያደርጉ አስታወቁ።
ኬንያ ውስጥ ጫት መቃም እየጨመረ ላለው የአእምሮ ጤና ችግር፣ ለወንጀልን መስፋፋት እንዲሁም ለተለያዩ ማኅበራዊ ችግሮች ምክንያት ነው ተብሎ ይታሰባል። በኬንያ የባሕር ዳርቻ አካባቢ የሚገኙ ሦስት ግዛቶች ባለፈው ሳምንት ጫት መሸጥ እና መቃምን ካገዱ በኋላ ጫት በሚያምርቱ አካባቢዎች ቁጣን ቀስቅሷል። የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ግን ጫት ሕጋዊ ምርት መሆኑን ጠቅሰው ሽያጩም መከልከል የለበትም በማለት የግዛቶቹን እርምጃ…
-

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለይ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ተበራክተው መቀጠላቸውን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ መንግሥት በሁለቱ ክልሎች ከሚንቀሳቃሱ ታጣቂ ቡድኖች ጋር በሚያደርገው ውጊያ መካከል እንዲሁም ከውጊያ አውድ ውጪ በሚፈጸሙ ጥቃቶች በዜጎች ላይ ሞት እና ከፍተኛ የመብት ጥሰት እየደረሰ ነው ብሏል። ኢሰመኮ ዛሬ ግንቦት 20/2016 ዓ.ም. ባወጠው መግለጫ እጅግ አሳሳቢ ሆነው ከቀጠሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መካከል ግድያ፣ የአካል ጉዳት፣ የዘፈቀደ እስር፣ ዘረፋ፣ እገታ እና መፈናቀል ዜጎችን እየገጠመ ነው ብሏል።…
-

በናይጄሪያ ማዕከላዊ ኒጀር ግዛት 10 ሰዎች መሞታቸውን እና ቢያንስ 160 የሚሆኑ የመንደሩ ነዋሪዎች ታግተው መወሰዳቸውን ባለስልጣናት ገለጹ።
ከናይጄሪያው አክራሪ እስላማዊ ቡድን ቦኮ ሃራም እንደሆኑ የተጠረጠሩ በርካታ ታጠቂ ኃይሎች አርብ ምሽት ኩቺ የምትባል መንደርን መውረራቸውን የአካባቢው ባለስልጣን አሚኑ አብዱልሀሚድ ናጁሜ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ታግተው የተወሰዱት አብዛኛዎቹ ሴቶች እና ህጻናት ሲሆኑ የተገደሉት ደግሞ ለአካባቢው ጥበቃ የሚያደርጉ አዳኞች መሆናቸውን ተናግረዋል። ታጣቂዎቹ በሞተር ሳይክሎች ወደ ኩቺ የገቡ ሲሆን ምግብ እያበሰሉ እና እየተመገቡ፤ ሻይ እያፈሉ እንዲሁም ቤቶችን እየዘረፉ…