Category: Uncategorized
-

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (አርኤስኤፍ) እንዲሁም አረብ አጋሮቻቸው በምዕራብ ዳርፉር በምትገኘው ኤል ጊኔያ በተባለች ከተማ የዘር ጭፍጨፋ መፈፀማቸውን የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ተቋም ሂውማን ራይትስ ዋች አስታወቀ።
ለተፈጠረው ቀውስ ተጠያቂ ናቸው ያላቸውን ሦስት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ኮማንደሮችም ይፋ አድርጓል። ይህም የቡድኑ መሪ ጀነራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎን (ሔሚቲ) ይጨምራል። አምና ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ባሉት ወራት እንዲሁም በያዝነው ዓመት ጥቅምት ላይ በኤል ጊኔያ ከተማ አረብ ያልሆኑ ማሳሊት የተባሉ መኖሪያ መንደሮች ውስጥ ስለሚደርሱ ጥቃቶች ብዙ ሪፖርቶች ሲወጡ ነበር። በሂውማን ራይትስ ዋች የወጣው ሪፖርት ግን እስካሁን…
-

በዐቃቤ ሕግ ሦስት ተደራራቢ ክሶች የቀረቡባቸው የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ በፍርድ ቤት ብይን ተሰጠ።
ብይኑን የሰጠው ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ. ም. የዋለው የፌራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የሕገ መንግሥት እና ሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት ነው። ችሎቱ ለዛሬ የተቀጠረው ለሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች መሆኑን የአቶ ታዬ ጠበቃ ቱሊ ባይሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱ ለዛሬ የተቀጠረበት አንደኛው ጉዳይ በተከሳሽ በኩል ለቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ የክስ…
-

በአስመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ ግንቦት 6፤ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለሰባት ዓመታት አቋርጦት የነበረውን የቪዛ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ኤምባሲው አስታወቀ።
ነገር ግን በኢሚግሬሽን እና ዜግነት ህጉ ክፍል 243(መ) ስር ባሉት ኦፊሴላዊ የኤርትራ ዜጎች ላይ ያለው የቪዛ እገዳ ባለበት እንደሚቀጥል አስመራ የሚገኘው ኤምባሲው በድረ ገጹ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። የቪዛ እገዳው ከዋና ዳይሬክተርነት ማዕረግ በላይ ላሉ የኤርትራ መንግሥት ባለስልጣናት፣ በገዢው ፓርቲ ህዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲ እና ፍትህ (ህግደፍ) ውስጥ በአመራርነት ላይ ያሉ የፓርቲ ኃላፊዎችን ይመለከታል። በተጨማሪም እነዚህ የመንግሥት…
-

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን፤ ሶስት ሬክተር ስኬል ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦፊዚክስ፣ ህዋ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የመሬት መንቀጥቀጡ በዞኑ በሚገኙ አስሩም ወረዳዎች እና ሁለት የከተማ መስተዳድሮች እንደተከሰተ የዳውሮ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ገልጿል። በዳውሮ ዞን የመሬት መንቀጥቀጡ የተመዘገበው ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 29፤ 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ከ24 ደቂቃ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሶሲሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የሶሲሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊው እንደሚያስረዱት፤ ተቋሙ ከዚህ ቀደም…
-

በሰሜናዊ አየርላንድ ቡሽሚልስ ግዛት በአንድ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ አንድ ግለሰብ በአጥር ላይ ሁለት እጆቹ በሚስማሮች ተቸንክረው ተገኙ።
ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት የተፈጸመበት በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኘው ይህ ግለሰብ ወደ ሆስፒታል መወሰዱም ተነግሯል። ጥቃቱ የተፈጸመው ቅዳሜ ከእኩለ ሌሊት በኋላ መሆኑ ተገልጿል። በዱንዳራቭ ፓርክ አቅራቢያ በሚገኘው የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ጥቃት የተፈጸመበት ግለሰብ ንብረት የሆነ አንድ መኪና እና ሌላ ተጨማሪ ተቃጥለው ተገኝተዋል። ፖሊስ የአየርላንድ ታጣቂ ቡድን ተሳትፎ ሊኖረው እንደሚችል በመጠርጠር ምርመራ መክፈቱን አስታውቋል። በአቅራቢያው ባሉ የህዝብ…
-

በከፍተኛ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ሳቢያ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።
በአገሪቱ ደቡባዊ ክፍል 56 ሰዎች እንደሞቱ የተገለጸ ሲሆን፣ በሪዮ ግራንድ ደ ሱል 67 ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀ ተገልጿል። ወደ 25,000 ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እና የንጹህ ውሃ አቅርቦት ተቋርጦባቸዋል። በቀጣይም ከፍተኛ ዝናብ ይጠበቃል። ይህ የአየር ንብረት ለውጥ የተከሰተው ከመደበኛው ጊዜ የከፋ ሙቀት፣ ወበቅ እና ንፋስ በመከሰቱ ነው። ከአጠቃላይ 497 ከተሞች…
-

በእስራኤል እስር ቤት ውስጥ ከአራት ወራት በላይ በእስር ላይ የቆዩት ፍልስጤማዊው ዶክተር ህይወታቸው ማለፉን የፍልስጤም እስረኞች ማህበር አስታውቋል።
የ50 ዓመቱ ዶክተር አድናን አልቡርሽ እስራኤል ለበርካታ ጊዜ ወረራ የፈጸመችበት የአልሺፋ ሆስፒታል የአጥንት ህክምና ኃላፊ ነበሩ። የእስራኤል እስር ቤት በደህንነት ምክንያት ተይዘው ስለነበሩት እና ኦፈር በተሰኘው እስር ቤት የሞቱት እስረኛ ዶክተር አልቡርሽ መሆናቸውን አረጋግጧል። የዶክተሩን የሞት መንስኤ በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ያልሰጠው የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ነገር ግን በምርመራ ላይ መሆኑን ገልጿል። የፍልስጤም እስረኞች ተሟጋች ቡድኖች በዚህ…
-

የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን አስመልከቶ ዲፕሎማቲክ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ 18 አገራት፣ አሜሪካን እና የአውሮጳ ሕብረት አባል አገራትን ጨምሮ “ሥራቸውን ሲሰሩ ፍትሀዊ ባልሆነ መልኩ የታሰሩ” ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ ሲሉ በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠየቁ።
ይህንን መግለጫም ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ኢትዮጵያ ከአጋሮቿ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ገንቢ የሆነ መስተጋብር እንዳላት ጠቅሶ “ እኔ አውቅልሀለሁ የሚል የጋራ መግለጫ ለሁለትዮሽ ግንኙነት የሚበጅ አይደለም፤ እንዲሁም በአገሪቱ ያለውን የሕግ የበላይነትን ማስከበር ዝቅ የሚያደርግ ነው” ሲል አጣጥሎታል። የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚህ መግለጫው ላይ “ [ኤምባሲዎቻቸው] በሚገኝበት አገር ጋር እንዲህ ያለ ግንኙነት ፍሬያማ ያልሆነ እና ከተለመደው…
-

በሐሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ገንዘብ ለማውጣት በመሞከር የተጠረጠሩት ቀሲስ በላይ መኮንን እና ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ የክስ መመሥረቻ 15 ቀናት በፍርድ ቤት መፈቀዱን ጠበቃ አቶ ቱሊ ባይሳ ለቢቢሲ ተናገሩ።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው ዛሬ ሐሙስ 24/ 2016 ዓ. ም. ረፋድ ላይ በነበረው የፍርድ ቤት ውሎው ነው። ቀሲስ በላይ እንዲሁም አብረው በቁጥጥር ሥር የዋሉት አጃቢያቸው እና ሹፌራቸው ዛሬ ለሦስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት፤ ባለፈው ሳምንት በነበረው ችሎት ፍርድ ቤቱ ለመርማሪ ፖሊስ ስምንት ተጨማሪ የምርመራ ቀናት በመፍቀዱ…
-

የሶቪየት ህብረት ናዚ ጀርመንን ማሸነፍ አስመልክቶ በሞስኮ ግዙፍ የድሉ መታሰቢያ ፓርክ ይገኛል። ቦታው አሁን አዲስ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሆኗል።
ኤግዚቢሽኑ ግን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ለዕይታ የቀረቡት ዩክሬን ውስጥ በሩሲያ ጦር የተያዙ የምዕራባውያን ወታደራዊ መሣሪያዎች ናቸው። መሣሪያዎቹ የጦርነቱ ዋንጫዎቿ ሲሆኑ አደባባይ ላይ ለዕይታ አብቅታ ጡንቻዬን ተመልከቱልን ብላለች። ከተማረኩት መካከል ለዩክሬን የተበረከተው የብሪታንያው ሃስኪ የተባለ ታክቲካል ድጋፍ ሰጪ መኪና ይገኝበታል። የፊት መስታወቱ በጥይት ተበሳስቶ ቀርቧል። ከሃስኪ ጎን ደግሞ ለዩክሬን ጦር የተሰጡ የምዕራባውያን…