Category: Uncategorized
-

የቱለማ አባ ገዳ የሆኑት አባ ገዳ ጎበና ሆላ ኢሬሶ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል የሆነው ልጃቸው መገደሉን ከማኅበራዊ ሚዲያ መስማታቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።
ከአንድ ሳምንት በፊት በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን ኮሚዩኒኬሽን መንግሥት ‘ሸኔ’ የሚለው ቡድን አባል ነው ያለው የአባ ገዳ ጎበና ልጅ “ሰላማዊ ሰዎችን ለመግደል ሲንቀሳቀስ እርምጃ ተወስዶበታል” ብሎ ነበር። ይህን የዞኑ መግለጫን ተከትሎ በኦሮሞ ባሕላዊ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ ትልቅ ስፍራ በሚሰጠው ገዳ ከፍተኛ ኃላፊነት ያላቸው የአባ ገዳ ጎበና ልጅ የመገደል ዜና ብዙዎችን ሲያነጋግር ቆይቷል። የቱለማ አባገዳ…
-

ቴክሳስ ውስጥ በሚገኙ የድንበር መሻገሪያዎች በቀን እስከ 2ሺህ300 ስደተኞች ወደ አሜሪካ ድንበር ሲሻገሩ ቆይተዋል።
በሳን ዲዬጎ ደግሞ በቀን እስከ 1ሺህ ሰዎች እየገቡ እንደሆነ የአካባቢው ባለስልጣናት ለቢቢሲ ተናግረዋል። አሜሪካ በስደተኞች የመጥለቅለቋ ጉዳይ የመሠረተ ልማት ግልጋሎቶችን ከማጨናነቁ አልፎ የአካባቢው ባለስልጣናት እና ነዋሪዎችን እያመረረ ይገኛል። በቅርቡ ዎል ስትሪት ጆርናል የሰራው የሕዝብ አስተያየት በአሪዞና፣ ጆርጂያ፣ ሚሺጋን፣ ኔዛዳ፣ ኖርዝ ካሮላይና፣ ፔንስለቬኒያ እና ዊስኮንሲን ግዛቶች ለምርጫ የተመዘገቡ መራጮች ዋነኛ ጉዳያችን የኢሚግሬሽን ጉዳይ ነው ብለዋል። በአሜሪካ…
-

ምንም እንኳን የሰነዘረችው የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃት ጉዳት ባያደርስም፣ ኢራን ከርቀት በእስራኤል ላይ ጥቃት የመፈጸም ብቃት እንዳላት አሳይታለች።
ይህም ሁለቱ አገራት ለረጅም ጊዜ በእጅ አዙር ሲያደርጉት የነበረው ፍልሚያ ወደ ቀጥታ ግጭት ማምራቱን ያሳያል። ኢራን በምትደግፋቸው ቡድኖች እስራኤልን ስታስጠቃ፣ እስራኤል ደግሞ ከኢራን ጋር የሚገናኙ ዒላማዎችን ስትመታ በቀጥታ ከመጋጨት ተቆጥበው ነበር። ጋዛ ውስጥ ከሐማስ ጋር፣ ከሊባኖሱ ሂዝቦላህ ጋር ደግሞ ድንበር በሚሻገር ግጭት ውስጥ የምትገኘው እስራኤል፤ ከኢራን ጋር የቀጥታ ፍጥጫ ውስጥ ከገባች ቀውሱ የበለጠ ይባባሳል ተብሎ…
-

በአወዛጋቢዎቹ የራያ አካባቢዎች ባለው አለመረጋጋት ምክንያት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በቆቦ፣ በሰቆጣ፣ በወልዲያ እና በሐሙሲት ከተሞች መጠለላቸውን ተፈናቃዎች እና በአማራ ክልል የተሾሙት የወረዳዎቹ አስተዳዳሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ ከትግራይ ኃይሎች በተደረጉ የተኩስ ልውውጦች አለመረጋጋት ውስጥ የገቡት ስድስቱ የራያ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮች፤ በአማራ ክልል መንግሥት ስር በተመሠረቱላቸው መዋቅሮች ስር መተዳደር ማቆማቸውን አራት የወረዳዎቹ አመራሮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የትግራይ ኃይሎች በተለይም የገጠር ቀበሌዎችን መቆጣጠራቸውን የዛታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ካሳሁን መኮንን እና የወፍላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍሰሐ ሞላ ገልፀዋል። ይህንን…
-

የኬንያ ጦር አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞንዲ ኦጎላ በምዕራብ የአገሪቱ ክፍል ይበሩበት የነበረው ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ ሕይወታቸው ማለፉን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አስታወቁ።
ኦጎላ ከሌሎች 11 ወታደራዊ መኮንኖች ጋር ሆነው በሄሊኮፕተሩ ሲጓዙ ነው አደጋው የደረሰው። ከአደጋው የተረፉት ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸው። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ሐሙስ ምሽት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አደጋው ለአገሪቱ “ትልቅ ሐዘን” ነው ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ቀደም ብለው የአገሪቱ የፀጥታ ምክር ቤት አባላቶቻቸውን ለአስቸኳይ ስብሰባ ጠርተው ነበር። አደጋው የደረሰው ሐሙስ ሚያዝያ 10/2016 ዓ.ም. ከቀን 8፡20 ላይ መሆኑን ሩቶ…
-

እስራኤል ባለፈው ቅዳሜ ኢራን ለፈጸመችባት የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃት ዛሬ ማለዳ ላይ የአጸፋ ጥቃት መፈጸሟን የኢራን መገናኛ ብዙኃን እና የአሜሪካ ባለሥልጣናት አስታወቁ።
ዛሬ አርብ ጎህ ከመቅደዱ በፊት በማዕከላዊቷ የኢራን ከተማ ኢስፋሃን ፍንዳታዎች መሰማታቸውን የኢራን የመገናኛ ብዙኃን የዘገቡ ሲሆን፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናትም ይህን አረጋግጠዋል። እስራኤል በኢራን ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሟን የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ለሆነው ሲቢኤስ ቴሌቪዥን አረጋግጠዋል። የኢራን መገናኛ ብዙኃን ደግሞ ሦስት የእስራኤል ድሮኖች በኢራን የአየር መከላከያ ሥርዓት መውደማቸውን ዘግበዋል። ጥቃቱ ተፈጽሞባታል የተባለችው የኢራን ከተማ ኢስፋሃን…
-

ጀርመን ለዩክሬን የምትሰጠውን ወታደራዊ ድጋፍ ለማደናቀፍ ሲያሴሩ ነበር የተባሉ በስለላ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች ደቡባዊ ግዛቷ ባቫሪያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የጀርመን ዐቃቤ ሕግ እንዳስታወቀው የጀርመን እና የሩሲያ ጥምር ዜግነት ያላቸው ሁለቱ ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት ለሩሲያ እየሰለሉ ነው በሚል ጥርጣሬ ነው። ከሁለቱ ተጠርጣሪዎች መካከል አንዱ የሆነው የ39 ዓመቱ ግለሰብ የፈንጂ እና የእሳት ቃጠሎ ጥቃትን ለመፈጸም እንዲሁም ከሩሲያ የስለላ ተቋም ጋር ግንኙነት በመፍጠር እና በወረራ በተያዘው ምሥራቃዊ ዩክሬን ውስጥ ለሩሲያ ቅጥረኛ ቡድን ተሰልፎ ተዋግቷል በሚል ተከሷል።…
-

የባህረ ሰላጤው አገራት አውሎ ንፋስ በቀላቀለ ከባድ ዝናብ መመታታቸውን ተከትሎ በዓለማችን ሁለተኛ የሆነው የዱባይ አየር ማረፊያ በጎርፍ ተጥለቀለቀ።
በዚህም የተነሳ በመቶዎች የሚቆጠሩ በረራዎች ሲሰረዙ፣በርካታዎችም ተስተጓጉለዋል። የዱባይ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ “በጣም ፈታኝ ሁኔታዎች” እንደገጠመው አስጠንቅቆ መንገደኞች በጎርፍ የተጥለቀለቁ አካባቢዎችን እንዲያስወግዱም መክሯል። አንድ ግለሰብ መኪናው በጎርፍ በመወሰዱ ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል። በኦማን ሳሃም በተሰኘችው አካባቢ ነፍስ አዳኞች የአንዲት ታዳጊ አስከሬን ማግኘታቸው የተገለጸ ሲሆን በዚህም በአገሪቱ ከእሁድ ጀምሮ የሞቱ ሰዎችን ቁጥር 19 አድርሶታል። ረቡዕ ዕለት የዱባይ…
-

ካለፈው ሳምንት ቅዳሜ ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድባቸው በነበሩ የራያ አላማጣ አካባቢዎች አቅራቢያ የምትገኘው አላማጣ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኗን የከተማዋ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ ለቢቢሲ ተናገሩ።
የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው መገደላቸውን እና ሌሎች የወረዳው እና የከተማዋ ኃላፊዎች አካባቢውን ለቅቀው ወደ ሌሎች የራያ ወረዳዎች መሄዳቸውንም ገልፀዋል። ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶ በራያ አላማጣ ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች ለተከታታይ ቀናት በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ ስጋት ውስጥ ገብታ የነበረችው አላማጣ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የሆነችው ከትላንት ሰኞ ሚያዝያ 7/2016…
-

በኢትዮጵያ ላለው የከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት በኢትዮጵያ መንግሥት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች በተጠራው የገንዘብ ማሰባሰብ ሥነ ሥርዓት 610 ሚሊዮን ዶላር ተሰበሰበ።
ትናንት ሚያዚያ 8/2016 ዓ.ም. ጄኔቫ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ለ15.5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ሕይወት አድን ድጋፍ ለማድረግ 3.24 ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ ታቅዶ ነበር። ይሁን እንጂ ከ21 ለጋሾች ማሰባሰብ የተቻለው 610 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው። የገንዘብ መዋጮውን ሥነ ሥርዓት ያዘጋጁት የኢትዮጵያ እና የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የተለያዩ አካላት ለቀረበው የገንዘብ ድጋፍ ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ እንደሚሰጡ እንጠብቃለን…