Category: Uncategorized
-

እስራኤል በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) በፈጸመችው ጥቃት ሰባት ሰራተኞቹ የተገደሉበት የረድዔት ድርጅት ጉዳዩ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠየቀ።
የእስራኤል መከላከያ ኃይል በተፈጸሙ “ከባድ ስህተቶች” የረድዔት ድርጅቱ ወርልድ ሴንትራል ኪችን ሰራተኞች ዒላማ ተደርገው ለሞት ተዳርገዋል ብሏል። የእስራኤል ጦር ባደረገው ምርመራ ሁለት ከፍተኛ መኮንኖችን አባሯል። የረድዔት ተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በበኩላቸው የእስራኤል ጦር “በጋዛ ውስጥ የራሱን ውድቀት በታማኝነት መመርመር አይችልም” ብለዋል። ሥራ አስፈጻሚዋ ኤሪን ጎሬ “የእስራኤል መከላከያ ኃይል በባልደረቦቻችን ላይ በተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ይቅርታ መጠየቃቸው…
-

ከአንድ ወር በላይ ተዘግቶ የቆየው የደብር ብርሃን – ደሴ መንገድ ከዛሬ መጋቢት 28/ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚከፈት የዞኑ ኮሙኒኬሽን ገለጸ።
መሥሪያ ቤቱ የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስትን ጠቅሶ በማኅበራዊ ገጹ ላይ ባጋራው ጽሑፍ ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ከየካቲት 16/2016 ዓ.ም አንስቶ ተቋርጦ የነበረው ከደብረ ብርሃን ደሴ የሚወስደው ዋና መንገድ ከዛሬ ጀምሮ ለመንገደኞች ክፍት እንደሚሆን አስታውቋል። ኮማንድ ፖስቱ፣ መንገዱ እንዲከፈት የተወሰነው በአካባቢው ያለው የሰላም ሁኔታ በመሻሻሉ እና ኅብረሰተሰቡ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ነው ብሏል። ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምሥራቅ…
-

ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማቋረጥ በመወሰን በአገሪቱ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደር እና ዲፕሎማቶች ለቀው እንዲወጡ ስታዝ አዲስ አበባ ያሉትን አምባሳደሯን ጠርታለች።
የሶማሊያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስቴር ይፋ እዳደረገው በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ሞሐመድ ዋሬ በ72 ሰዓታት ውስጥ ሞቃዲሾን ለቀው እንዲወጡ አዛለች። በተጨማሪም ከሶማሊያ ነጻ አገርነቷን ባወጀችው ሶማሊላንድ እና በከፊል ራስ ገዟ ፑንትላንድ ውስጥ የሚገኙት ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች በሰባት ቀናት ውስጥ እንዲዘጉ መወሰኑን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ባወጣው…
-

የእስራኤል መከላከያ ኃይል ዛሬ አርብ መጋቢት 27/2016 ዓ.ም. ከኢራን በኩል ሊቃጣበት የሚችለውን ጥቃት ለመመከት በጠንቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ።
የእስራኤል ባለሥልጣናት ኢራን በመጨረሻው የረመዳን ሳምንት አርብ በሆነው ቁድስ (የኢየሩሳሌም ቀን) ጥቃት ልትፈጽም እንደምትችል ያምናሉ። እስራኤል ከጥቂት ቀናት በፊት በሶሪያ በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ጽህፈት ቤት ላይ የአየር ጥቃት ፈጽማ ከፍተኛ ጄኔራልን ጨምሮ 13 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ ስትዝት ቆይታለች። የእስራኤል መከላከያ ኃይሉ ሊቃጣ የሚችል የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃትን ለማክሸፍ በበርካታ የአገሪቱ አካባቢዎች የአቅጣጫ…
-

በጋዛ ሰራተኞቸቻው የተገደሉባቸው የወርልድ ሴንትራል ኪችን የረድዔት ድርጅት ኃላፊ የእስራኤል ኃይል “በታቀደ መልኩ በመኪኖቻቸው ላይ ጥቃት ፈጽሟል” አሉ።
በእያንዳንዱ መኪና ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተፈጽሞም ሰባት ሰራተኞቻቸው እንደተገደሉም የድርጅቱ ኃላፊ ሆዜ አንድሬስ ገልጸዋል። ሰኞ ዕለት የተፈጸመው ጥቃት በስህተት እንዳልሆነ የሚናገሩት ኃላፊው፣ ስለ ሰራተኞቻቸው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ለእስራኤል ኃይል ቀድመው ማሳወቃቸውንም በድጋሚ ተናግረዋል። እስራኤል የረድዔት ሰራተኞቹ ተሳፍረው ይሄዱበት በነበሩ መኪኖች ላይ በፈጸመችው ጥቃት አውስትራሊያዊ፣ ካናዳዊ፣ የዩናይትድ ኪንግደም፣ አሜሪካዊ እና ፍልስጤማዊ ዜግነት ያላቸው ሰራተኞች ተገድለዋል። እስራኤል ጥቃቱ…
-

የአማራ እና ትግራይ ክልሎች በሚወዛገቡባቸው አካባቢዎች ላይ ከሰሞኑ “በትግራይ ክልል በኩል የሚታየው አዝማማሚያ”፤ “ተገቢነት የሌለው ብቻ ሳይሆን የፕሪቶሪያውን ስምምነት የሚጥስ” እንደሆነ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ተናገሩ።
ዶ/ር ለገሰ፤ “ወሰንን በኃይል እናስከብራለን” የሚል አካሄድ “የትግራይ ሕዝብን ለሌላኛው ዙር ስቃይ እና እንግልት የሚዳርግ ነው” ሲሉም አሳስበዋል። የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። የዶ/ር ለገሰ ጋዜጣዊ መግለጫ “ባለፉት ስድስት ዓመታት የለውጥ ጉዞዎች”፣ ሰላም እና ደኅንነት እንዲሁም የበጋ ልማት ሥራዎችን የተመለከተ ነበር። የሰላም…
-

ታይዋን ረቡዕ ዕለት በሬክተር ስኬል 7.4 በሆነ ከፍተኛ ርዕደ መሬት ስትናጥ እስካሁን የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ታውቋል።
ርዕደ-መሬቱ በተለይ በሁዋሊየን ከተማ በርካታ ሕንፃዎችን የወዘወዘ ሲሆን የነብስ አድን ሠራተኞች ሕይወት ለመታደግ እየተሯሯጡ ነው። ደሴቷ ታይዋን እንዲህ ያለ ጠንካራ የሚባል ርዕደ-መሬት ባለፉት 25 ዓመታት አስተናግዳ አታውቅም። በዋና ከተማዋ ታይፔይ ሕንፃዎች በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት ሲነቃነቁ የሚያሳዩ ቪድየዎች ማሕበራዊ ሚደያዎች ላይ ተለቀዋል። “የርዕደ-መሬት ለምድር የተጠጋ ነው። በመላው ታይዋን እና በደሴቱ አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች ተሰምቷል። በ25 ዓመታት…
-

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ የመንግሥት ተቆጣጣሪ አካል በሚወስነው መሠረት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ እንዲተገበር የሚያደርግ አዋጅ አጸደቀ።
አዋጁ የቤት ኪራይ የክፍያ ሥርዓት “በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ በሆነ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ ብቻ” እንዲፈጸምም ያስገድዳል። ምክር ቤቱ ይህንን “የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ” ያጸደቀው ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 24/2016 ዓ.ም. በነበረው ውሎው ነው። በስድሰት ክፍሎች የተዋቀሩ ሰላሳ ሁለት አንቀጾችን የያዘው አዋጅ የጸደቀው ከዚህ በፊት ከነበረው ተሞክሮ በተለየ ሁኔታ ነው። ከዚህ በፊት የነበረው አሠራር አዋጆች…
-

በፊንላንድ ቫንታ ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት የ12 ዓመት ታዳጊ ሶስት ተማሪዎችን በጥይት ማቁሰሉን ፖሊስ አስታወቀ።
ፖሊስ ቪየርቶላ በተሰኘው ትምህርት ቤት ከጥዋቱ ሶስት ሰዓት በፊት ለተፈጠረው ክስተት ምላሽ ለመስጠት እንዳቀና እና የአካባቢው ነዋሪዎችም በቤት ውስጥ እንዲቆዩ አሳስቧል። ተጠርጣሪው የ12 ዓመቱ ታዳጊ መጀመሪያ ቢሸሽም በኋላ ግን በፖሊስ ቁጥጥር መዋሉ ተገልጿል። በትምህርት ቤቱ 800 ተማሪዎች የሚማሩበት ሲሆን 90 ሰራተኞችም አሉት። ከጥቃቱ በኋላም ተማሪዎቹ ከክፍሎቻቸው እንዳይወጡ እንደተነገራቸው ዋይ ኤልኢ የተሰኘው ሚዲያ ዘግቧል። ተማሪዎቹ የስቅለት፣…
-

በእስራኤል ያለው የፖለቲካ ልዩነት በድጋሚ አደባባይ ወጥቷል።
ሐማስ መስከረም 26 የፈጸመውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ በእስራኤል ብሔራዊ አንድነት የታየ መስሎ ነበር። ከስድስት ወራት በኋላ ግን እስራኤላውያን ለተቃውሞ ወደ ጎዳናዎች መትመም ጀምረዋል። ቤንያሚን ኔታንያሁ ለረዥም ዓመታት በጠቅለይ ሚንስትርነት እስራኤልን አስተዳድረዋል። የአሁኑ ጦርነት ግን ከስልጣን እንዲወርዱ የሚደረገውን ግፊት አቀጣጥሎታል። የእየሩሳሌም ፖሊስ መጥፎ ሽታ ያለው ውሃ በመርጨት ሰልፈኞችን ለመበተን ተገዷል። ሠልፈኞቹ በከተማዋ የሚገኘውን አውራ ጎዳን ዘግተው…