Category: Uncategorized
-

ዶናልድ ትራምፕ በደቡብ ካሮላይና ኒኪ ሄሊ ላይ ትልቅ ድል ካስመዘገቡ በኋላ የሪፐብሊካን ፓርቲ ፕሬዚዳንታዊ ዕጩ ለመሆን አንድ እርምጃ መቃረባቸው ተሰምቷል።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ተቀናቃኞቻቸውን በግዛታቸው በ20 ነጥብ ልዩነት አሸንፈዋል። ይህም አራተኛ ተከታታይ ድላቸው ሆኖ ተመዝግቧል። ትራምፕ ድላቸውን ባበሰሩበት ወቅት ስለተቀናቃኛቸው ምንም አስተያየት አልሰጡም። ይልቁንም በሚቀጥለው ዓመት ኅዳር ወር በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ትኩረት አድረገዋል። “ጆ ባይደን ጋር ፊት ለፊት እንገናኛለን። አገራችንን እያፈራረሰ ነው። እኛ ደግሞ ‘ጆ ውጣ፣ ተባረሃል’ ልንል ነው” ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል። ትራምፕ ከቅዳሜው ውጤት…
-

በአማራ ክልል ከተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ ለወራት በቁጥጥር ስር የሚገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል የሆኑት ካሣ ተሻገር (ዶ/ር) ያለመከሰስ መብት ተነሳ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዛሬ በጀመረው የ3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሚያካሂድበት ጊዜ ነው የከተማው ምክር ቤት የአባሉን ካሣ ተሻገርን (ዶ/ር) ያለመከሰስ መብት በአብላጫ ድምጽ ያነሳው። ካሳ (ዶ/ር) የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ሆነው በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ውስጥ በመወዳደር ነበር ለከተማው ምክር ቤት እንደራሴነት የተመረጡት። ባለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ በአማራ ክልል…
-

አሜሪካ ሩሲያ በዩክሬን በፈጸመችው ወረራ እንዲሁም በቅርቡ እስር ቤት ሞቶ በተገኘው ተቃዋሚው አሌክሲ ናቫልኒ ጋር በተያያዘ ከ500 በላይ አዳዲስ ማዕቀቦችን እንደምትጥል አስታወቀች።
እነዚህ ማዕቀቦች በሩሲያ ዋነኛ የካርድ የክፍያ ሥርዓት፣ በፋይናንስ እና ወታደራዊ ተቋማት እንዲሁም በናቫልኒ እስራት ውስጥ የተሳተፉ ባለስልጣናት ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ያካትታል ተብሏል። የአውሮፓ ኅብረት በበኩሉ ከወታደራዊ ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ አዲስ ማዕቀብ እንደሚጥል አስታውቋል። ፕሬዚዳንት ፑቲንን በሰላ በመተቸት የሚታወቀው ናቫልኒ በታሰረበት አርክቲክ ሰርክል ከሞተ ከአንድ ሳምንት በኋላም ነው ምዕራባውያኑ አዳዲስ ማዕቀብ እንደሚጥሉ ያስታወቁት። ሐሙስ ዕለት በሳንፍራንሲስኮ…
-

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሁለት ዓመታት 94 ሰዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እና በታጣቂዎች ከሕግ ውጭ መገደላቸውን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ባለፉት ዓመታት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት እና በታጣቂ ላይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት እና በሚፈጸሙ ጥቃቶች ሰላማዊ ሰዎች ሰለባ መሆናቸውን አመልክቷል። በዚህም ሁለቱም ወገኖች ነዋሪዎችን ሌላኛውን ወገን በመደገፍ እና አባል በመሆን እንደሚከሱ እና በዚህም ሳቢያ ያለ ሕግ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም ግድያዎችን መፈጸማቸውን በአሃዝ አስደግፎ ይፋ አድርጓል። ኮሚሽኑ ይህን የገለጸው በክልሉ በመንግሥት…
-

ንብረትነቱ የዩናይትድ ኪንግደም የሆነች የዕቃ መጫኛ መርከብ በኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ በየመን ሁቲዎች ሚሳኤሎች ተመታች።
ሁለት ሚሳኤሎች የተወነጨፈባት መርከቧ መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰባትም የአሜሪካ ጦር አስታውቋል። ጥቃቱ የተፈጸመው በየመን ደቡባዊ ምስራቅ በምትገኘው የወደቧ ከተማ ኤደን ነው። የዩናይትድ ኪንግደም የባህር ኃይል ባለስልጣናት የተወነጨፉት ሚሳኤሎች በመርከቧ ላይ የእሳት ቃጠሎ እንዳስከተለባትም ተናግረዋል። የሁቲ ቃለ አቀባይ መርከቧን ዒላማ ማድረጋቸውን አረጋግጠው የአሜሪካ የጦር መርከብንም በድሮን መምታታቸውን አክለዋል። በኢራን የሚደገፉት እና አብዛኛውን የሰሜን ምዕራብ የመንን የሚቆጣጠሩት ሁቲዎች…
-

ወላጆች ልጆቻቸው ሥርዓት ለማስተማር አስከፊ አያያዝን እንዲከተሉ በዩቲዩብ በመምከር ታዋቂ ለመሆን የበቃችው አሜሪካዊቷ የዩታህ ግዛት እናት ልጆቿን በማሰቃየት ተከሳ የዓመታት እስር ተፈረደባት።
ልጆቿን በማስራብ እና በማሰቃየት ጥፋት መፈጸሟን ለፍርድ ቤቱ ያመነችው እናት ሩቢ ፍራንክ፣ የእስር ቅጣት ሲበይንባት እያለቀሰች ችሎቱ ይቅርታ እንዲያደርግላት ጠይቃለች። እናትየው ክስ ተመስርቶባት እስር የተፈረደባት ከቀድሞ የሥራ ሸሪኳ ጋር ነው። በዚህም ሁለቱም ተመሳሳይ የእስር ቅጣት ተላልፎባቸዋል። በዚህም በቀረበባቸው የተለያዩ ክሶች በተናጠል ከአንድ አስከ 15 ዓመታት የሚደርስ እስር በእያንዳንዳቸው ላይ ተፈርዷል። የእስር ቅጣቶቹንም በተከታታይ የሚፈጽሙ ሲሆን፣…
-

ለፈው ጥር ወር 737 ማክስ አውሮፕላን በበረራ ላይ እያለ መስኮቱ መገንጠሉን ተከትሎ ከፍተኛ ጫና ውስጥ የነበረው ቦይንግ ከአውሮፕላኑ ምርት ክፍል ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጋር ሊለያይ መሆኑ ተሰምቷል።
ለ18 ዓመታት በኩባንያው የሰሩት ኤድ ካላርክ ከቦይንግ እንደሚለቁ ኩባንያው ትናንት ይፋ ካደረገ በኋላ ከፍተኛ ግርምት ተከስቷል። ቦይንግ እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው የምርቱን ጥራት እና ደህንነት ለማሻሻል እንደሆነ አስታውቋል። የኃላፊው የመልቀቅ ዜና የተሰማው ኩባንያው ከተቆጣጣሪዎች ጋር ለመገናኘት ዝግጅት እያደረገ ባለበት ሰዓት ነው። ባለፈው ጥር ንብረትነቱ የአላስካ አየር መንገድ የሆነ አውሮፕላን በረራ ላይ ሳለ ችግር ከገጠመው በኋላ…
-

በአፍሪካ ቀንድ የዩኤስ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ በፕሪቶሪያ ስምምነት አፈፃፀም እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
የልዑካን ቡድኑን የሕወሃት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤልን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው በፕሪቶሪያ ስምምነት አፈፃፀም ላይ ተወያይተዋል። የፕሪቶሪያ ስምምነት በርካታ ጉዳዮች እስከ አሁን ተግባራዊ ቢደረጉም የትግራይ ሉዓላዊነት መመለስ እና ህዝባችንን ነጻ ማውጣት፣ የተፈናቀሉ ዜጎች መመለስ፣ ለተራበ ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ መስጠት እና ሌሎችም ተግባራዊ እንዳልሆኑ ለልዑካን ቡድኑ አስረድተዋል። የደኢህዴን ጉዳይ (የትግራይ ሰራዊት መልሶ መቋቋም እና ማቋቋም) ቅድሚያ ሊሰጠው…
-

የሶማሊያ ፓርላማ ከሳምንት በፊት ከቱርክ ጋር የተፈረመውን የመከላከያ እና የምጣኔ ሃብት ስምምነትን አጽድቋል። የዚህ ስምምነት ሙሉው ዝርዝር ይፋ ባይደረግም በተለይ በመከላከያ ዘርፍ ቱርክ የሶማሊያን ባሕር ኃይልን ለማጠናከር እና የአገሪቱን የባሕር ጠረፍ በጋራ ለመጠበቅ ከስምምነት መደረሱ ተነግሯል።
ቱርክ አንካራ ውስጥ የሁለቱ አገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች ስምምነቱን የተፈራረሙት ኢትዮጵያ ነጻነቷን ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርማ ከሶማሊያ ጋር ውዝግብ ከተቀሰቀሰ ከአንድ ወር በኋላ ነው። በሶማሊያ እና በቱርክ መካከል የተደረሰው ስምምነት ለአስር ዓመታት የሚቆይ ነው። ቱርክ የሶማሊያን የባሕር ኃይል በማሠልጠን የምታስታጥቅ ሲሆን፣ የሶማሊያን የባሕር ጠረፍን ለመጠበቅም የራሷን የባሕር ኃይል በአካባቢው እንደምታሰማራ ተነግሯል። ቢቢሲ ሶማሊኛ ባገኘው…
-

በስፔን የተገደለው አንድ ግለሰብ ሩሲያን ከድቶ ወደ ዩክሬን ኮብልሏል የተባለው ሩሲያዊ ፓይለት መሆኑ ተገለጸ።
ማስኪም ኩዝሚኖቭ ባለፈው ዓመት ነበር የጦር ሄሊኮፕተሩን እያበረረ ወደ ዩክሬን ግዛት ዘልቆ በመግባት እጁን የሰጠው። የስፔን ፖሊስ ባለፈው ሳምንት በአሊካንቴ ግዛት አቅራቢያ ስለተገደለው ሰው ማንነት በይፋ አልገለጸም። ሆኖም የዩክሬን ደኅንነት የተገደለው ግለሰብ ሩሲያዊው ፓይለት ኩዝሚኖቭ መሆኑን ሰኞ እለት አረጋግጧል። የደኅንነት ቃለ አቀባይ ለዩክሬን ጋዜጣ ዩክሬይንስካ ፕራቭዳ እንደተናገሩት” [ፓይለቱ] መሞቱን አረጋግጠናል… በዩክሬን ከመቆየት ይልቅ በስፔን ለመኖር…