Category: Uncategorized
-

ኢትዮጵያውያንን በሕገ ወጥ መንገድ በማዘዋወር የተጠረጠሩ አራት የኬንያ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
መርማሪዎች በሕገ ወጥ መንገድ የተዘዋወሩ 37 ኢትዮጵያውያንን ከኬንያ መዲና ናይሮቢ 16 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ በአንድ ቤት ውስጥ አግኝተዋቸዋል ተብሏል። አራቱ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር የዋሉትም ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እንዲፈፀም በመርዳት ተጠርጥረው ነው ። ኢትዮጵያውያኑ የተሻለ ሕይወትን ፍለጋ ወደ ደቡብ አፍሪካ እያቀኑ መሆናቸውን ለኬንያ ባለስልጣናት መናገራቸውን የግል ጋዜጣ የሆነው ዘ ስታር ዘግቧል። የቤቱን…
-

በትግራይ የተካሄደውን ጦርነት ተከትሎ በተከሰተው የምግብ እጥረት ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ መጋለጣቸውን የክልሉ ባለሥልጣናት ከመግለጻቸው በተጨማሪ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች እንደሞቱ ይናገራሉ።
በዚህም ሳቢያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታዳጊዎች ለእራሳቸው እና ለቤተሰባቸው ምግብ የሚሆን የዱር ፍሬ ለማግኘት ከትምህርት ቤት ይቀራሉ ወይም ትምህርት ያቋርጣሉ። Hundreds of thousands of people have starved to death due to food shortages following the war in Tigray, and the regional authorities have said that more than 100 people have died. As a result, a…
-

ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችው አወዛጋቢ ስምምነት ጦርነት ከማወጅ ጋር የሚስተካከል ነው ሲሉ በተባባሩት መንግሥታት ድርጅት የሶማሊያ አምባሳደር አስጠነቀቁ።
ሰኞ ምሽት ሶማሊያን በተመለከተ በመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በተካሄደ ስብሰባ ላይ አምባሳደሩ አቡካር ኦስማን ኢትዮጵያ ወታደራዊ ሰፈር ለማቋቋም ስትል የሶማሊያን ግዛት ለመጠቅለል ዕቅድ አላት ሲሉ የመንግሥታቸውን ክስ አሰምተዋል። በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ይዘት ለሕዝብ ይፋ ባይደረግም፣ ነገር ግን ሶማሊላንድ ለኢትዮጵያ ለንግድ መተላለፊያ የባሕር በር እና የተወሰነውን ደግሞ በኪራይ ለኢትዮጵያ ባሕር ኃይል…
-

ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ከነበሩ ሰዎች መካከል የተወሰኑት ወደ ምሥራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች መመለስ ጀመሩ።
ሰኞ የካቲት 11/2016 ዓ.ም. ኦሮሚያ ክልል የደረሱት የመጀመሪያ ዙር ተመላሾች፣ የቀድሞ መኖሪያቸው በሚገኙባቸው ወረዳዎች ውስጥ በተዘጋጁላቸው ጊዜያዊ መጠለያዎች ውስጥ ማረፋቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። በደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ የቆዩት ተፈናቃዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል መመለስ የጀመሩት እሁድ የካቲት 10/2016 ዓ.ም. መሆኑን ሁለት ተመላሾች እና አንድ የተፈናቃዎች አስተባባሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እሁድ ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ ጉዞ የጀመሩት ተመላሾችን የጫኑ…
-

የታንዛንያው የነጻነት ታጋይ ጁሊየስ ኔሬሬ በአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ አዲስ አበባ ሐውልት ቆመላቸው።
ጁሊየስ ኔሬሬ ታንዛንያ ወይም በቀድሞ አጠራሯ ታንጋኒካ ከብሪታንያ ቅኝ ግዛት ጭቆና እንድትላቀቅ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ታጋይ ነበሩ። አገራቸው ነጻነቷን ከተቀዳጀችም በኋላ ኔሬሬ ከአውሮፓውያኑ 1961- 1985 ድረስ መርተዋል። በስዋሂሊ ቋንቋ ምዋሊሙ (መምህር) በመባል የሚታወቁት ኔሬሬ በፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ላይ በነበራቸው ቁርጠኝነት ታሪክ ያወሳቸዋል። በደቡብ አፍሪካ ጨቋኙን የነጮች አገዛዝ፣ ወይም አፓርታይድ በመባል የሚታወቀውን ሥርዓት ይታገሉ ለነበሩ የነጻነት…
-

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ላይ ያሉትን ሶማሊያ እና ኢትዮጵያን ጉዳይ እንደሚያነሳ ተጠቆመ።
ኢትዮጵያ ነጻ አገርነቷን ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር በተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት ሳቢያ የተፈጠረውን ውዝግብ ዛሬ የካቲት 11/ 2016 ዓ.ም. ከሚያነሳቸውን ጉዳዮች አንዱ እንደሚሆን ምክር ቤቱ በድረ-ገጹ አስፍሯል። በአጠቃላይ የሶማሊያ ጉዳይን በአጀንዳነት የያዘው የፀጥታው ምክር ቤት ጉባዔ መጀመሪያ ሊካሄድ የነበረው የካቲት 8/2016 ዓ.ም. ነበር። ነገር ግን ‘አፍሪካን ስሪ’ (ኤ3) በመባል የሚታወቁት የፀጥታው ምክር ቤት ሦስቱ የአፍሪካ አገራት እና…
-

የቀድሞው የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲዔታ እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል፣ አቶ ታዬ ደንደኣ ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ።
አቶ ታዬ አባል የሆኑበት፣ የኦሮሚያ ምክር ቤት (ጨፌ) ያለመከሰስ መብታቸውን ያነሳው ዛሬ ሰኞ፣ የካቲት 11/2016 ዓ.ም. እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባዔ ላይ ነው። የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ዲዔታው፤ ከሁለት ወር በፊት ታኅሣሥ 2/2016 ዓ.ም ነበር ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ ከሽብር ድርጊት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸው የተገለጸው፡፡ የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አባል እና የኦሮሚያ ክልል ምክር…
-

ኔዘርላንድስ ሄግ ከተማ ውስጥ በሚገኙ በሁለት ኤርትራውያን ቡድኖች መካከል ቅዳሜ ምሽት በተከሰተ ግጭት የፖሊስ ተሽከርካሪዎች በእሳት መጋየታቸው ተነገረ።
የኤርትራ መንግሥት ደጋፊ እና ተቃዋሚ በሆኑት ቡድኖች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለመቆጣጠር የኔዘርላንድስ ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ መጠቀሙን እና መኪኖች መቃጠላቸውን የዐይን እማኞች ለቢቢሲ ትግርኛ ገልጸዋል። ግጭቱ በተካሄደበት ስፍራ በርካታ ሰዎች በጎዳና ላይ የታዩ ሲሆን፣ አንዳንዶችም ድንጋይ ሲወረውሩ እንደነበር እና በእሳት የተያያዙ መኮኖችም በታየታቸውን እማኞች ተናግረዋል። ቢሆንም ግን በግጭቱ ሰዎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱ የታወቀ ነገር የለም። አሲሺየትን…
-

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ እንዳይገኙ እንቅፋት ሆነውባቸው እንደነበር ከከሰሱ በኋላ የአዲስ አበባ ቆይታቸውን አቋርጠው ወደ አገራቸው መመለሳቸው ተዘገበ።
ኢትዮጵያ ነጻ አገርነቷን ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሟን ተከትሎ ሶማሊያ ተቃውሞዋን በማሰማት በሁለቱ አገራት መካከል ውዝግብ መፈጠሩ ይታወቃል። በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ከሻከረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ኅብረትን ስብሰባ ለመሳተፍ አዲስ አበባ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐሙድ በስብሰባው ላይ እንዳይገኙ በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ሙከራ ተደርጎባቸው እንደነበር ገልጸዋል። ይህንንም ተከትሎ ፕሬዝዳንቱ ለሁለት ቀናት…
-

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐሙድ የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ወደሚካሄድበት ስፍራ “እንዳልገባ ለመከልከል ሞክረዋል” በማለት ያቀረቡትን ክስ የኢትዮጵያ መንግሥት አስተባበለ።
ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 11/2016 ዓ.ም. በተጀመረው የአህጉሪቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመገኘት ትናንት አርብ አዲስ አበባ የገቡት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት፣ የፀጥታ ኃይሎች ተፈጸመብኝ ባሉት ክልከላ ኢትዮጵያን የኅብረቱ ጉባኤ “ባለማክበር” ከሰዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለቀረበበት ክስ በሰጠው ምላሽ፣ ለአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ለሚመጡ የአገራት እና የመንግሥታት መሪዎች እንደሚደረገው ሁሉ ለሶማሊያው ፕሬዝዳንትም በሙሉ ክብር ደማቅ አቀባበል እንደተደረጋለቸው ጠቅሶ፣ በሶማሊያ ልዑክ በኩል…