Category: Uncategorized
-

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ በቅርቡ በደቡባዊ ጋዛ፣ ራፋህ ከተማ ላይ አዲስ ወረራ እንፈጽማለን አሉ።
ናታንያሁ ይህን በራፋህ ላይ የታቀደው ዘመቻ “ከሐማስ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ብንደርስም ባንደርስም የማይቀር ጉዳይ ነው” ብለዋል። ሐማስና እስራኤል ከመጋረጃ ጀርባ እያደረጉ ያሉት ድርድር ተስፋ እያሳየ መምጣቱ በሚነገርበት ወቅት ነው ናታንያሁ ይህን ያሉት። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ጽኑ አቋማቸውን በሐማስ ቤተሰቦቻቸው የታገቱባቸው እስራኤላዊያን ጋር በነበራቸው ውይይት ነው ይፋ ያደረጉት። “ራፋህ ከተማን ከመውረር የሚመልሰን ምንም ስምምነት…
-

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የምትገኘው ላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የወረዳው ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ በታጣቂዎች በተፈፀመባቸው ጥቃት መገደላቸውን ምንጮች እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ዋና ከተማው ላሊበላ የሆነው የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው የጤና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ ጥቃት የተፈጸመባቸው ትናንት ማክሰኞ ሚያዝያ 22፤ 2016 ዓ.ም. እንደሆነ አራት ምንጮች ገልፀዋል። ባለስልጣናቱ ተኩስ የተከፈተባቸው በሰሜን ወሎ ዞን ዋና ከተማ ወልዲያ የነበራቸውን ስብሰባ አጠናቅቀው እየተመለሱ በነበረበት ወቅት እንደሆነ መስማታቸውን ለወረዳው አስተዳደር ቅርበት ያላቸው አንድ…
-

ከካንሰር ህመም ጋር እየታገለ ያለው የላኦስ ተወላጁ ስደተኛ በአሜሪካ 1.3 ቢሊዮን ዶላር የሎተሪ ጃክፖት አሸናፊ ሆነ።
የ46 ዓመቱ ቼንግ ሳፋን ፓወርቦል በተሰኘው የሎተሪ ጃክፖት ጨዋታዎች እድለኛ መሆኑን የውድድሩ ባለስልጣናት ገልጸዋል። ቼንግ ዕድለኛ ያደረገውን የሎተሪ ቲኬት የገዛው በኦሪጎን ግዛት በፖርትላንድ ከተማ ከሶስት ሳምንት በፊት ነበር። ግለሰቡ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ ግብር ተቀንሶ 422 ሚሊዮን ዶላር ያህል የሚደርሰው ሲሆን ይህንንም ከባለቤቱ እና ጓደኛው ጋር እኩል እንደሚካፈሉ አስታውቋል። “አሁን ቤተሰቤን አንበሻብሻለሁ። ለራሴም ጥሩ ዶክተር መቅጠር…
-

ላለፈው ሁለት ዓመት ከስምንት ወር ገደማ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን (አባሉ) አቶ ጣሂር ሙሐመድ “በግል ምክንያት” ከኃላፊነት መልቀቃቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።
በአቶ ጣሂር ቦታ ሌላኛው የአብን አባል አቶ መልካሙ ፀጋዬ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሾማቸውን የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን አስታውቋል። ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫን ያሸነፈው ገዢው ብልፅግና ፓርቲ መንግስት ሲመሰረት በተከተለው የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በመንግስት ኃላፊነት ላይ የማካተት ውሳኔ መሰረት ወደ ኃላፊነት የመጡት አቶ ጣሂር፤ የተሾሙት መስከረም 2014 ዓ.ም. ነበር። በወቅቱ የክልሉ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ለኃላፊነት…
-

በጎርፍ ከ80 ሰዎች በላይ የሞቱባት ኬንያ የትምህርት ቤቶች መክፈቻ ዕለትን በሳምንት አዘገየች።
አውሎንፋስ በቀላቀለ ዝናብ ምክንያት በጎርፍ የተጥለቀለቀችው ኬንያ ትምህርት ቤቶችን መክፈት ለተማሪዎቹ እና ሰራተኞቹ ስጋት መሆኑን ገልጻለች። መረጃዎች እንደሚያሳዩት በመላው አገሪቷ ያሉ ትምህርት ቤቶች በጎርፍ ምክንያት ጉዳት እንደደረሰባቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ኤዚኪየን ማሾጉ እሁድ እለት ባወጡት መግለጫ አስፍረዋል። “በከፍተኛ ሁኔታ እየጣለ ያለው ዝናብ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ላይ ያደረሰው ጉዳት እጅግ የከፋ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የጎርፍ አደጋን የመከላከል…
-

የዩናይትድ ኪንግደም ወግ አጥባቂ የፓርላማ አባል ቻይና ላይ ባቀረቡት ትችት ጂቡቲ ከመግባት እንደተባረሩ ተናገሩ።
ከቻይና ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያላት ጂቡቲ ከጥቂት ሳምንት በፊት እንዳባረቻቸው ቲም ሎውተን ገልጸዋል። የምስራቅ ዎርቲንግ እና ሾረሃምን ግዛቶችን በመወከል የፓርላማ አባል የሆኑት ቲም ሎውተን ጂቡቲ ሲደርስ ከሰባት ሰዓታት በላይ በእስር መቆየታቸውን እና ወደ ጂቡቲ እንዳልገባ ተከልክያለሁ ብለዋል። ከሶስት ዓመት በፊት በቻይና ማዕቀብ የተጣለባቸው ሎውተን በሁኔታው ብቸኝነት እንደተሰማቸው “በጣም አስፈሪ” እንደነበር ተናግረዋል። የቻይና የውጭ ጉዳይ መስሪያ…
-

ሐማስ ያወጣው ቪዲዮ አንድ አሜሪካዊ እና አንድ እስራኤላዊ ታጋቾች በጋዛ በሕይወት እንደሚገኙ ማረጋገጫ ሆኗል ተባለ።
ቪዲዮ መቼ እንደተቀረጸ የተባለ ነገር ባይኖርም በቪዲዮ ላይ የሚታየው እስራኤላዊው ኦማሪ ሚራን ለ202 ቀናት ተይዞ መቆየቱን ይናገራል። አሜሪካዊው ኪዝ ሲጂል ደግሞ ከሳምንት በፊት የተከበረውን የአይሁዶች በዓል በንግግሩ ስለሚጠቅስ ቪዲዮ በቅርብ የተቀረጸ ስለመሆኑ አመላካች ሆኗል። ሁለቱም ታጋቾች ሐማስ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. እስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት በፈጸመ ወቅት ነበር ታግተው ወደ ጋዛ የተወሰዱት። ቪዲዮውን ተከትሎ የታጋቾቹ ቤተሰቦች…
-

የአየርላንድ መንግሥት ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችለውን ሕጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ጀመረ።
የአየርላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሲሞን ሃሪስ የአገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችል ሕግ አርቅቆ ለአገሪቱ ካቢኔ እንዲያቀርብ አዘዋል። ዩናይትድ ኪንግደም በሕገ-ወጥ መልኩ ወደ አገሯ የሚገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እልካለሁ ማለቷን ተከትሎ ዩኬ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሩዋንዳ ላለመመለስ ሲሉ እንደ አየርላንድ ያሉ አገራትን አማራጭ መዳረሻቸው እያደረጉ ነው። የአየርላንድ የፍትሕ ሚኒስትር ሄለን ማክኤንቲ በቅርቡ ወደ አየርላንድ…
-

ቡርኪናፋሶ የጦር ሰራዊቷ በጅምላ ግድያ መወንጀሉን አስመልክቶ ባቀረቡት ዘገባ ቢቢሲ እና የአሜሪካ ድምጽን አገደች።
የሁለቱም ጣቢያዎች ስርጭቶች መቋረጣቸውን እንዲሁም የድርጅቶቻቸው ድረገጾች ለሁለት ሳምንታት መታገዳቸውን ባለስልጣናቱ ተናግረዋል። ሁለቱ ሚዲያዎች መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪው ሂውማን ራይትስ ዋች ያወጣውን ጦሩ ንጹሃን ዜጎችን መግደሉን ዋቢ በማድረግ ነው በዘገቦቻቸው የሸፈኑት። ሂውማን ራይትስ ዋች በሪፖርቱ የቡርኪናፋሶ ጦር በየካቲት ወር ቢያንስ 223 ንጹሐን ዜጎችን ጨፍጭፏል ብሏል። ጦሩ ከሁለት ዓመት በፊት በመፈንቅለ መንግሥት ስልጣን ከተቆናጠጠ…
-

ኢራቃዊቷ የማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ኦም ፋሃድ በባግዳድ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ውጭ በተተኮሰባት ጥይት ተገደለች።
የአገሪቷ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ጥቃቱ የተፈፀመው ከዋና መዲናዋ በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ዛይን ሰፈር አርብ ዕለት ነው። የኢራቅ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ዝነኛ የሆነችው ግለሰብ ‘ባልታወቁ ታጣቂዎች’ መገደሏን ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል። የግለሰቧን አሟሟት ለመመርመርም ልዩ የምርመራ ቡድን መሰማራቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል። በመዝገብ ስሟ ጉፍራን ሳዋዲ የተባለችውና በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቿ ፋሃድ በሚል መጠሪያ የምትታወቀው ሴት ብቻውን…