Category: Uncategorized
-

የእስራኤል ጦር ካቢኔ ለኢራን ያልተጠበቀ የሰው አልባ (ድሮን) እና ሚሳኤል ጥቃት ምላሽ ለመስጠት በመከረበት ስብሰባው ወጥ ውሳኔ ላይ መድረስ ሳይችል ቀረ።
በ24 ሰዓታት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የተሰበሰው የጦር ካቢኔ ለጥቃቱ አጸፋዊ ምላሽ እንዴት እና መቼ ይስጥ በሚለው ላይ መከፋፈሉም ተዘግቧል። እስራኤል የጥቃቱን ምላሽ በተመለከተ ውሳኔ ላይ መድረሷን ለህዝብ ይፋ አላደረገችም። የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት የእስራኤል መንግሥት ሙሉ ጦርነት ሳይቀሰቀስ ኢራንን የሚጎዳ ጥቃት ማካሄድ ይፈልጋል። ይህንንም ጥቃት የእስራኤል ሚኒስትሮች ከአሜሪካ ጋር በመቀናጀት መፈጸም እንደሚፈልጉም ተዘግቧል። የአሜሪካ…
-

ታዋቂው አቡነ ማር ማሪ ኢማኑዔል ሲድኒ ከሚገኝ ቤተ-ክርስቲያን በቀጥታ ሥርጭት የሚተላለፍ ትምህርት እየሰጡ ሳለ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።
አቡነ ማር ማሪ ኢማኑዔል የአሲሪያን ኦርቶዶክስ ክራይስት ዘ ጉድ ሼፐርድ የተባለው ቤተ-ክርስቲያን ወግ አጥባቂ መሪ ናቸው። በአቡኑ ላይ ጥቃት ያደረሰው ታዳጊ በምዕመናን ቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ለፖሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል። የሲድኒ ፖሊስ አቡነ ማር ማሪ ኢማኑዔል እና አባ ኢሳክ የተበሉ ቄስ ጥቃት ቢደርስባቸውም “ሕይወታችን አደጋ ላይ የሚጥል አይደለም” ብሏል። የ53 ዓመቱ አቡነ ማር ማሪ ኢማኑዔል ጭንቅላታቸው…
-

የሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎች አግተን የነበረውን የባንግላዴሽ ባንዲራን የምታውለበልብ መርከብ እና ሠራተኞቿን ለማስለቀቅ 5 ሚሊዮን ዶላር ተቀበልን አሉ።
ኤምቪ አብዱላህ የምትባለው ዕቃ ጫኝ መርከብ የድንጋይ ከሰል ጭና ከሞዛምቢክ ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች እየተጓዘች ሳለች ነበር በሶማሊያ የባሕር ዳርቻ ላይ በባሕር ወንበዴዎች የታገተችው። መርከቧን አግተው የቆዩት የባሕር ላይ ወንበዴዎቹ መርከቧን እና 23 የመርከቧን ሠራተኞች ለማስለቀቅ 5 ሚሊዮን ዶላር ተቀብለናል ብለዋል። ይሁን እንጂ የመርከቡ ባለቤቶች በድርድር መርከቧን መለቀቋን ቢያምኑም ገንዘቡን ስለመክፈላቸው ያሉት ነገር የለም። ከቅርብ…
-

እስራኤል ልክ እንደ ኢራን ሁሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሚሳኤሎችን በመተኮስ ‘ትክክለኛው ሰዓት ላይ’ የበቀል እርምጃ እውስዳለሁ አለች።
ዓለም አቀፉ ማሕብረሰብ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ውጥረት ከሚያባብስ እርምጃ እንዲቆጠቡ አገራት ቢያሳስቡም እስራኤል ግን ትክክል ሆኖ ሳገኘው የአጸፋ እርምጃ እውስዳለሁ ብላለች። ኢራን ለመጀመሪያ ጊዜ በእስራኤል ላይ በፈጸመችው ቀጥተኛ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከ300 በላይ ሚሳኤል እና ድሮኖች ወደ እስራኤል ማስወንጨፏ ይታወሳል። ከ300 በላይ የሚሆኑት ሚሳኤሎች እና ድሮኖች ከኢራን፣ ኢራቅ እና ከየመን ወደ እስራኤል የተተኮሱ ቢሆንም አብዛኞቹ…
-

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እስራኤል ከኢራን የተቃጡባትን በመቶዎች የሚቆጠሩ ድሮኖችን እና ሚሳኤሎችን የመከተችው በአሜሪካ ድጋፍ ነው አሉ።
ፕሬዝዳንቱ ጥቃቶቹን በማምከን የተሳተፉ የአሜሪካ ጦር ኃይል አባላትን አሞካሽተዋል። ፕሬዝዳንቱ ባወጡት መግለጫ ከዚህ የኢራን ጥቃት አስቀድሞ አሜሪካ የጦር አውሮፕላኖችን እና መርከቦችን ወደ ቀጠናው ማስጠጋቷን ተናግረዋል። “እነዚህን ጥቃቶች እጥብቄ አወግዛለሁ” ያሉት ባይደን “ከጠቅላይ ሚንስትር ኔታኒያሁ ጋር በስልክ በተነጋገርንበት ወቅት አሜሪካ ለእስራኤል ደኅንነት ከብረት የጠነከረ ድጋፏ እንደማይለያት አረጋግጫለሁ” ብለዋል። እስራኤል በመቶዎች የሚቆጠሩ ድሮኖች እና ሚሳኤሎች ከኢራን እንደተተኮሱባት…
-

በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ውጥረት ወደ ከፍተኛ ደረጃ በወሰደ ጥቃት ኢራን በእስራኤል ላይ የሰው አልባ አውሮፕላን እና የሚሳኤል ጥቃቶችን ፈጸመች።
ኢራን ጠላቷ አድርጋ በምትቆጥራት እስራኤል ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ስትፈጽም ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ኢራን በጋዛ እስራኤልን እየተዋጋ ያለውን ሐማስን እንዲሁም በቀጠናው የእስራኤል ጠላት የሆኑትን ሄዝቦላህ እና የየመን ሁቲ አማጺያንን በመደገፍ እስራኤል ላይ በእጅ አዙር ጥቃት ስትፈጽም ቆይታለች። ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት የመክፈቷ ዜና ኢራናውያን ወደ አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን አንዲገልጹ አድርጓቸዋል። ይህ የኢራን ጥቃት ድንገት የተከሰተ…
-

የሩሲያ የፍትሕ ሚኒስቴር ሁለት ታዋቂ ጋዜጠኞችን፣ የቢቢሲ ሩሲያ ዘጋቢ ኢሊያ ባርባኖቭ እና የሳይንስ ዘጋቢ አስያ ካዛንቴሴቫን “የውጭ ወኪሎች” ሲል ፈረጀ።
የቢቢሲ ሩሲያዊ ጋዜጠኛ ባርባኖቭ ስለ ሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እንዲሁም ስለ ቅጥረኛው ተዋጊ ቡድን ቫግነር በሰፊው ዘገባዎችን ሰርቷል። ቢቢሲ ሚኒስቴሩ በጋዜጠኛው ላይ የፈጸመውን ፍረጃ አውግዟል። “ቢቢሲ ውሳኔውን አጥብቆ አይቀበለውም” ሲል የቢቢሲ መግለጫ አትቷል። “የውጭ ወኪል” የሚለው መለያ በሩሲያ ውስጥ የከፋ አሉታዊ ትርጓሜዎች አሉት። መንግሥት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችውን ወረራ የሚያወግዙትን ብቻ ሳይሆን የክሬምሊን ፖሊሲዎችን የሚተቹ…
-

በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ዳባት ወረዳ አንድ ኤርትራዊ የ12 ዓመት ስደተኛ ህጻን ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች መታገቱን ቤተሰቦቹ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ታዳጊው ከዘጠኝ ቀናት በፊት መጋቢት 26፣ 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ላይ ታፍኖ መወሰዱን ገልጸዋል። አማን መሐመድ የተባለው ታዳጊ ከሚማርበት ዳባት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወደ ቤቱ በመመለስ ላይ ድንገት ፊታቸውን የሸፈኑ ሦስት ሰዎች የአማንን ፊት በመሸፈን በባጃጅ መውሰዳቸውን ወላጅ እናቱ ወይዘሮ ራሕማ መሐመድ ተናግረዋል። ከትምህርት ቤት በሚመለስበት ወቅት መንገድ ላይ አግኝቶት የነበረው የ14 ዓመት ወንድሙ…
-

የኢትዮጵያ መንግሥት ፆታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን የሚመዘግብ ሥርዓት ሊጀምር መሆኑን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
ምዝገባው ፆታን መሠረት አድርገው የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል እና ለመቀነስ ያለመ ነው የተባለ ሲሆን፣ በተለይ “ወሲባዊ ጥቃቶች ላይ ትኩረት” እንደሚያደርግ ተነግሯል። በሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች መብት እና ጥበቃ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ስለሺ ታደሰ፣ የምዝገባ ሥርዓቱን ለመጀመር 10 ሚሊዮን ብር እንደሚፈጅ ለቢቢሲ የተናገሩ ሲሆን፣ ይህ በጀት በተለያዩ አካላት መዋጮ እንደሚሸፈንም ጠቁመዋል። ይህ ‘ብሔራዊ የፆታዊ…
-

ኬንያ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ለማርገብ ያስችላል ያለችውን ቀጠናዊ የባሕር ጠረፍ አገልግሎት አጠቃቀም ስምምነት አማራጭ አቀረበች።
ይህ ኬንያ ያቀረበችው አማራጭ በቀጠናው የሚገኙ የባሕር በር የሌላቸው አገራት በንግድ ስምምነት መሠረት የባሕር መተላለፊያ አገልግሎት እና ጥቅም የሚያገኙበትን ዕድል የሚፈጥር ነው ተብሏል። ከጥቂት ወራት በፊት ኢትዮጵያ እና ከሶማሊያ ተገንጥላ ነጻ አገርነቷን ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር የባሕር በር ለማግኘት የመግባቢያ ሠነደ መፈረሟ በአዲስ አበባ እና ሞቃዲሾ መካከል ከፍተኛ ውጥረትን ፈጥሯል። ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ታኅሣሥ 22/2016 ዓ.ም.…